×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
እግዚአብሔርን ማወቅ

እግዚአብሔር ፀሎት ይመልሳልን?

ምላሽ ማግኘት የሚችል ፀሎት እንዴት መፀለይ እንችላለን?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በማሪሊን አዳምሰን

በጣም በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው አጋጥሞህ ያውቃል? ኤቲስት የነበርኩ ጊዜ ዘወትር የምትፀልይ መልካም ጓደኛ ነበረችኝ ሁልጊዜ በየሳምንቱ እግዚአብሄር ነገሮቹዋን እንደሚሰራ እንደሚያስተካክል በጣም እንደምታምነው ትነግረኝ ነበር። እኔም በየሣምንቱ ያልተለመደን ነገር እግዚአብሔር ሲያደርግላትና ፀሎቷን ሲመለስ እመለከት ነበር። ዓለማዊ ለሆነ ሰው ሁልጊዜ በየሣምንቱ ይህንን እውነት ማየት እንዴት ከባድ እንደሆነ ታስባለህ? ከጥቂት ጊዜ በኋላ የነገሮቹ መደጋገም ጥያቄ ይፈጥርብኝ ጀመር።

እግዚአብሔር የጓደኛዬን ጥያቄ ለምንድን ነው የሚመልሰው? ብዬ መጠየቅ ስጀምር የተረዳሁት ትልቁና ዋናው ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ያላት ግንኙነት ነው። በአእምሮዋ እግዚአብሔር ህይወቷን የመምራት መብት እንዳለው አውቃለች ደግሞም ይህንን እንዲያደርግ ጋብዛዋለች። ለተለያዩ ጉዳዮች ስትፀልይ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር ካላት ግንኙነት አንዱ ተፈጥሮአዊ አካል ነው። ጥያቄዎቸንና የሚያስፈልጓትን ነገሮች እንዲሁም ማንኛውንም የህይወቷን ጉዳይ ይዛ ወደ እግዚአብሔር ስትመጣ በጣም ደስተኛ ትሆናለች። በተጨማሪም ከመፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር በእሱ ላይ እንዲህ መደገፍ እንደሚገባት ባነበበችው እውነት ተስማምታለች። ህይወቷ መፅሐፍ ቅዱስ፡ “በእገዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውም ነገር እነደፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል፡:”1 “የጌታ ዓይኖች ፃድቃንን ይመለከታሉና ጆሮዎቹም ፀሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው”2 የሚለው ቃል ይገልፀዋል።

ለምንድን ነው እግዚአብሔር የሁላችንም ፀሎት ያልመለሰው?

ምክንያቱ ምናልባት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የለን ይሆናል። ምናልባት እግዚአብሔር እንዳለ የምናምንና በየጊዜውም የምናመልከው ልንሆን እንችል ይሆናል፡ ነገር ግን ፀሎታችን ፈፅሞ ያልተመለሰ የሚመስለን ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ስለሌለን ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ፍፁም የሆነ የሀጢአት ይቅርታን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደተቀበልን አላመንም ማለት ነው። የሀጢአት ይቅርታ ከፀሎት መልስ ጋር ምን ያገናኘዋል ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። ጉዳዩ እንዲህ ነው፡ "እነሆ የእግዚሰብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፤ ጆሮውም ከመስማት አልደነቆረችም፤ነገር ግን በደላችን በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፤እንዳይሰማም ሀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።" ኢሣ 59፤1-2

እንዴት እንደምንፀልይ፤ መሰረታዊ ሀሳቦች

አንድ ሰው የእግዚአብሄር ልጅ ሲሆንና ከእግዚአብሄር ወገን ሲሆን እግዚአብሄር ያውቀዋል ፀሎቱንም ይመልሳል። ጌታ ኢየሱስ ሲናገር፤ " መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን አውቃለሁ እነርሱም ያውቁኛል ... በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ.. እነርሱም ይከተሉኛል፤ እኔ የዘላለም ህይወት እሰጣቸዋለሁ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄ ሊነጥቃቸው ሚችል ማንም የለም።"3

በውኑ እግዚአብሄርን ታውቀዋለህን? እሱስ አንተን ያውቅሀልን? ለፀሎትህ መልስ ዋስትና የሚሆን ግንኙነት ከእግዚአብሄር ጋር አለህን? ወይስ ለአንተ እግዚአብሄር ማለት በጣም በርቀት ላይ ያለ ህሳቤ ነው? ላንተ እግዚአብሄር የራቀ እና እንደምታውቀው እርግጠኛ ካልሆንክ፤ ከእግዚአብሄር ጋር አሁኑኑ ግንኙነት መጀመር ትችላለህ

እግዚአብሄር ፀሎታችንን በእርግጥ ይማልሳልን?

ለሚያውቁትና ለሚደገፉበት ጌታ ኢየሱስ በሥጦታው ባለጠጋ ነው። "በእኔ ብትኖሩ፤ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፤ የምትፈልጉትን ማነኘውም ነገር ለምኑ ይሰጣችሁል"4። በእርሱ መኖርና በቃሉ መኖር ማለት በእግዚአብሔር እውቅና ውስጥ ህይወትን መምራት፤ በእሱ ላይ ራስን መጣል እና እሱ የሚለውን መስማት ማለት ነው። ይህ ሲሆን ሰው የሚፈልገውን ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅ ያስችለዋል። እንዲሁም፡ “ በእገዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውም ነገር እነደፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል፤የምንለምነውን ሁሉ እነደሚሰማን ካወቅን፤ የለመነውንም ነገር እነደተቀበልን እናውቃለን፡:”5 እግዚአብሔር እንደ ፍቃዱ፤እንደ ጥበቡ፤ እንደ ፃድቅነቱ እና እንደ ፍቅሩ የሆነውን ፀሎታችንን ይመልሳል።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ እየተጓዝን ከሆነ ለፀሎታች አንድ ትክክለኛ መልስ እነዳለ ይኸውም "የእግዚአብሔር ፈቃድ"እነደሁነ ልናውቅ ይገባል። ይህ ለሰው ልጆች ከባድ የሆነ ጉዳይ ነው ምክንያቱም የሰው ልጆች በጊዜና በእውቀት ውስን ስለሆነ እንዲሁም በነገሮች ላይ ያለው መረጃ እና ወደፊት ምን ሊሆን እንደሚችል የነገሮችን ነገ በማየት ላይም ውስን ስለሆነ ነው። የእግዚአብሔር ማንነት ግን ገደብ የለውም። በሰው ህይወት ውስጥ ወይም በታሪክ ውስጥ ነገሮች እንዴት እንደሚሆኑ ያውቃል እኛም ከምናውቀውና ከምንገምተው ያለፈ ዓላማ ሊኖረው ይችላል። ስለዚህ እግዚአብሔርን ይህ ጉዳይ ያንተ ፈቃድ መሆን አለበት ብለን ስለፀለይን ማንኛውም ፀሎት ዝም ብሎ አይመለስም።

ከእኛስ ምን ይጠበቃል? የእግዚአብሔርስ ዝንባሌ ምንድን ነው?

የእግዚአብሔር አመለካከት ለእኛ ምን እንደሆነ በዝርዝር ልንገነዘበው ይገባናል። መፅሃፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት እና ሊሰጠን የሚፈልገው የህይወት ዓይነት የተፃፈበት ቅዱስ መፅሐፍ ነው።

ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹን ስንመለከት፡ "እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሳል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሳል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና"6 ይህ አንድ ሰው ከወንበሩ ብድግ ብሎ በመነሳት አንተን ለመርዳት እንደመፍጠን ማለት ነው። "ርህራሄውን ሊያሳየን ከሙታን ተነስቷልና!" እንዲሁም መፅሐፍ ሲናገር “የአምላክ መንገድ ፍፁም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያድረጉት ሁሉ እርሱ ጋሻ ነው።”7 ሆኖም የእግዚአብሔር ትልቁ ፍቅርና የመውደዱ ጥልቀት የተገለጠው፡ "ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፤ በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።"8

ትልቁ የ እግዚአብሔር የፍቅር ማሳያ ግን ህ ነው። ኢየሱስ “ስለወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም” አለ9 ስለዚህ "እግዚአብሔር ከኛ ጋር ከሆነ ማን ያቃወመናል!" ይላል እንዲሁም "እግዚአብሔር ሳይራራ አንድያ ልጁን ከሰጠን ከእሱ ጋር ሁሉን ነገር እንዴት አብልጦ አይሰጠንም?"10

ያልተመለሱ ፀሎቶቻችን

ሰዎች በምድር ላይ ይቸገራሉ፤ ይጨነቃሉ፤ ገንዘብ ያጣሉ፤ ይታመማሉ፤ ይሞታሉ እና የመሳሰሉ ችግሮች ያጋጥማቸዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን እግዚአብሔር ሀሳባችንን ሁሉ በእሱ ላይ እንድንጥል ይፈልጋል። ምናልባት ነገሮችህ የሞተ፤ የተቆረጠ ቢመስልም በእሱ ላይ ጣለው ምክንያቱም እሱ ስለአንተ ያስባል ይጠነቀቅልህማል። አንዳንድ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ሊመስሉ ይችሉ ይሆናል ግን አይደሉም። ዓለም በአጠቃላይ የጠፋ ቢመስልም እንኳ እግዚአብሔር ግን እኛን ይጠብቀናል። ምክንያቱም “እርሱ ስላናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃን ሁሉ እርሱ ላይ ጣሉት"11 ይላል።

እግዚአብሔር ከምንገምተው በላይ በሆነ መንገድ መፍትሄን ለችግሮቻችን ሊሰጠን ይችላል ለዚህም የእያንዳንዱ ክርስቲያን ህይወት ምስክር ሊሆን ይችላል። ኢየሱስም እንዲህ አለ፡ "ሰላሜን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን አሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም፤ ልባችሁ አይታወክ አይፍራም!"12

ነገሮች በጣም ከባደና አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ ላይ እግዚአብሔር እሱን በመተማመን እንድንቀጥል በማየት ሳይሆን በእምነት እንድንራመድ ይጠይቀናል መፅሀፍ ቅዱስም ይህንን ይመሰክርልናል። ሆኖም ይህ እምነት እውር አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር ባህሪ ላይ የተመሰረተ ነው። በጎልደን ጌት ድልድይ ላይ የሚሽከረከር መኪና ሙሉ በሙሉ በድልድዩ ጥራት ላይ የተመሰረተ ነው። መኪናው በሰላም ወዳሰብክበት ስፍራ እንዲያደርስህ የሚያደርገው የሾፌሩ ስሜት ወይም ሾፌሩ ስለአንተ ያለው አመለካከት ወይም ከተሳፋሪው ጋር የሚያወራው ጉዳይ ሳይሆን የድልድዩ ጥራት እና አሽከርካሪው ድልድዩን ለማመን መፍቀዱ ነው።

እንዲሁ እግዚአብሔር በማንነቱ፤ በባህሪው፤ በርህራሄው፤ በፍቅሩ፤ በጥበቡ፤ በፅድቁ እንድንተማመንበት ይፈልጋል። እንዲህም አለ፡ "በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህም በርኅራኄ ሳብኩሽ።"13 እንዲሁም "ሰዎች ሆይ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ እግዚአብሔር መጠለያችን ነውና!"14

በአጠቃላይ እንዴት እንፀልይ

እግዚአብሔር የልጆቹን፣ የተቀበሉትንና ፍለጋውን ሊከተሉ የወደዱትን ፀሎት ይመልሳል። የሚያስጨንቀንን ጉዳያችንን ሁሉ ይዘን ወደ እሱ እንድንመጣ ይጋብዘናል ጌታ ደግሞ እንደ ፈቃዱ የሆነውን ፀሎታችንን ይመልሳል። በነገሮቻችን ዙሪያ ከእሱ ጋር ስንነጋገርና ስንወያይ ነገሮቻችንን በእርሱ ላይ እንጥላለን ከእሱ ደግሞ ከሁኔታዎቻችን በላይ የሆነን ሠላም እንቀበላለን። የተሰፋችንንና የእምነታችን መሰረት ደግሞ የእግዚአብሔር ባህሪ ነው። የበለጠ ስናውቀው የበለጠ እንታመነዋለን። የእግዚአብሔርን ለማወቅ “እግዚአብሔር ማነው?” የሚለውን ፅሁፍ በዚህ ድህረ-ገፅ ላይ ያገኛሉ።

ከሁሉ በላይ የመጀመሪያ ፀሎት እግዚአብሔር የመለሰልን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትና ወዳጅነት ለመፍጠር የፀለይነው ፀሎት ነው።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) 1ዮሐ 5፡14 (2) 1ጴጥ 3፡12 (3) ዮሐ 10፡14 27-28 (4) ዮሐ 15፡7 (5) 1ዮሐ 5፡14 (6) ኢሳ 30፡18 (7) መዝ 18፡30 (8) መዝ 147፡11 (9) ዮሐ 15፡13 (10) ሮሜ 8፡32 (11) 1ጴጥ 5፡7 (12) ዮሐ 14፡27 (13) ኤር 31፡3 (14) መዝ 62፡8


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More