×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
ወሲብ እና የፍቅር ግንኙነት

ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ስህተት ነውን? ከወሲብ በመጠበቅ አሰልቺ ሕይወት እንኑርን?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ጥያቄ. ቅድመ ጋብቻ የወሲብ ልምምድ ስህተት ነውን? እናንተ ክርስቲያኖች ይህ የደስታ ምንጭ ፣ ጨዋታና መዝናኛ የሆነውን ወሲብ ለምን ስህተት ነው ትላላችሁ? እግዚአብሔር መልካም ነው ያለውን እናንተ ለምን አትደሰቱበትም ?

የኛ መልስ፡  ግልጽ ለማድረግ አንድ ምሣሌ እናንሳ፤ መኪና መንዳት ስህተት ነውን? በፍጹም ስህተት አይደለም። ለአሥራ ሦስ ዓመት ልጅ መኪና እንዲነዳ መፍቀድና መስጠት ስህተት ነውን ? አዎ ስህተት ነው። ለልጁ ጨዋታና ደስ የሚያሰኘው ልምምድ ሊሆን ቢችልም የእርሱንና የሌሎችን ሕይወት አደጋ ውስጥ መጣል ስለሆነ ፈጽሞ ስህተት ነው።

ወሲብ በባልና በሚስት መካከል የሚያስደስት ልምምድና ጨዋታ ሆኖ ቢፈጸም ስህተት ነውን ? ፈጽሞ ስህተት አይደለም። ወሲብ ካልተጋቡት ከሌላ ሰው ጋር እንደ ጫወታና እንደ መዝናኛ ወስዶ መፈጸም ስህተት ነውን ? አዎ ስህተት ነው። ደስ የሚያሰኛና የሚያዝናና ጨዋታ ሊሆን ይችላል። ሆኖም በዚህ ለምምድ ውስጥ በሚያልፉት ሰዎች መካከልብዙ ጊዜ ልብን የሚሰብርና አስደንጋጭ አጋጣሚዎችን ይዞ ይመጣል።

ፍቅር የተሞላው አምላካችን እግዚአብሔር ሕይወትን በተመለከተ አስደናቂ ጥበቡን እንድናውቅ በሚገባ ገልጾልናል። ኃጢዓት ለጊዜው የሚያስደስትና ጣፋጭ ነው ብሎናል። ስለዚህ ሲሰሩት በወቅቱ የማያስደስት ኃጢዓት ላይኖር ይችላል)። ነገር ግን ደስታ ብቻ ለውሳኔአችን የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ግብዐት መሆን የለበትም። ታናናሽ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ስንመታቸው ከነርሱ ጋር እንደጨዋታ የምናሳልፈውና የሚሰጠን ጊዜያዊ ደስታ ዋንኛ ጉዳያችን አድርገን እነርሱን ስንደበድብ አንገኝም።

እግዚአብሔር እኛ በማንአለብኝነትና በልበ ደንዳናነታችን ወስነን ከምናመጣው እጅግ የሚያስፈራ አደጋና ችግር ሊጠብቀን ይፈልጋል። የእርሱ ፍቅር ፍፁምና ንጹህ ስለሆነ በተሳሳተ ውሳኔ አልፈን የኛን ሕይወትና የሌሎችንም ሕይወት እንድናጠፋና እነዳናበላሽ ሊጠብቀን ይፈልጋል።

ወሲብን የፈጠረው እግዚአብሔር አምላክ በጋብቻ ኪዳን ውስጥ ብቻ እንዲፈጸም ለምን ወሰነ? « መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው ፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን። ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። » ዕብራ.13፥4

እግዚአብሄር የቅድመ ጋብቻ ወሲብን የከለከለውእንድንዝናና ስለማይፈልግ ነውን? ወይስ በጋብቻ ውስጥ ለሚገኙ ባልና ሚስቶች ብቻ እርስ በርሳቸው በመዋሃድ ጥልቅ ደስታ እንዲያገኙ ነው? እግዚአብሔር አምላክ ምሪት ሲሰጠን ያነሳሳው ፍጽም ፍቅሩና ርህራሄው ነው።)

ሰዎች ለጊዜያዊ ደስታና ተዝናኖት ወሲብን ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ፤ ከጊዜያዊ ደስታ የበለጠ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ቢኖሩስ? እነደ በራስ መተማመን፤ ለራስ ዋጋ መስጠት፤ ለሌሎች ዋጋ እንደምንሰጥ ማወቅ ያሉትን ማለቴ ነው። ምናልባትም እግዚአብሔር ግንኙነት ከወሲብ በላቀ ነገር ላይ ሲገነባ የበለጠ አስተማማኝና ጠንካራ ይሆናል ብሎ አስቦም ይሆናል። ምንም ይሁን ምን የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ከእኛ እንደሚበልጥ ማወቅና የታመነም እንደሆነ መገንዘብ አለብን። ከዚያም ተቀብለነው በተከተልነው መጠን ዕውነቱ የበለጠ እየተገለጸልን ይሄዳል።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More