×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
FAQ

እግዚአብሔር አለምን የፈጠረው በስድስት ቀን ነውን?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ብዙ ሰዎች እንዲህ ያስባሉ፡-

  • ዓለም በቢሊዮን በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ ተፈጥሮ እንዳለቀ ሳይንስ አረጋግጧል፤
  • መጽሐፍ ቅዱስ ዓለም በስድስት ቀናት ውስጥ ተፈጥሮ እንዳለቀ ይናገራል።
  • ስለዚህ ከሁለቱ አንዱን ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን ወይንም ሳይንስን መርጣችሁ ማመን ይኖርባችኋል ማለት ነው። ትክክል አይደለም?

ይህን መጣጥፍ ለሚያነቡ ሰዎች አስደናቂና ያልጠበቁት ሊሆን ይችላል። ያለን መልስ « አይደለም » የሚል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ዓለም በስድስት ቀናት ውስጥ ተፈጥሮ እንዳለቀ እንድናምን አይጠይቀንም። በዘፍጥረት ላይ የተጠቀሰው ቃል እግዚአብሔር በቢሊዮን ዓመታት ውስጥ ዓለምን እንደፈጠረ አድርጎ ለማሰብ የሚያስችል ክፍተት እንዳለ እርግጥ ነው። የሚከተለውን ጥቅስ እስቲ እንመልከት፡-

መጽሐፍ ቅዱስ የሚጀምረው ከዚህ በታች ባለው አረፍተ ነገር ነው።

« በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ፤ » ዘፍጥረት . 1፥1

ከምንም ነገር ተነስቶ በአንድ አፍታ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ። ይህ ለዓለማቸን ፍጹም የሆነ አጀማመር ነበር። ሳይንሲስቶች «ቢግ ባንግ ቲዎሪ» የሚሉት ዓይነት መሆኑ ነው።

ከመጀመሪያው ቁጥር ቀጥሎ በዘፍጥረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ እንዲህ ተጽፏል፡- «ምድርም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም። » ዘፍጥ. 1፥2 ይልና የምዕራፉ ቀሪው ቁጥሮች እግዚአብሔር አምላክ ሌሎችን ፍጥረታት በቅደም ተከተል ሲፈጥር እንመለከታለን፤ የምድርን ከባቢ አየር፣ ጸሐይንና ጨረቃን በየሥፍራቸው ማስቀመጥ ፣ ከመሬት ላይ ውሃውንና የብሱን መለየት፣ ዕጽዋቶችን ተክሎችንና አዝርዕቶችን እንዲሁም በባህርና በምድር ላይ የሚኖሩ እንስሶችንና ነፍሳትን ፣ በመጨረሻም ሰዎችን ፈጠረ።

ዋናው ጥያቄ ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ዓለምን ማለትም ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ፈጥሮ ጨረሰ ይላልን?

ታዲያ ክርክሩን ምን አመጣው?

የዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ የሰፈረው እግዚአብሔር በስድስት ቀን ውስጥ ተፈጥረው እንዳለቁ የሚገልጽ ቢመስልም፡-«እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፤ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ ስድስተኛ ቀን። ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ። » ዘፍጥረት. 1፥31 - 2፥1

«ስድስተኛ ቀን» ይላል፤ ማስተዋል ያለብን ነገር ዘፍጥረት የተጻፈው በዕብራይስጥ ቋንቋ ነው። የዕብራይስ ቋንቋ ከእንግሊዝኛ ቋንቋና ዛሬ ከሚነገሩት ሌሎች ቋንቋዎች ጋር ሲነጻጸር የቃላት ሃብቱ አነስተኛ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለዚህ አንዳንድ አገላለጾች ለዘመኑ አንባቢዎችና ለተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች፥ ግልጽ ላይሆኑ ይችላሉ፧ ወይም አሻሚ ትርጉም ይዘው ሊገኙ ይችላሉ። ለምሣሌ;- በዕብራይስጥ «መሬት» የሚለውን ቃል፣ አገር ክልል፣ ምድር፣ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

እንደዚሁም « ቀን » (በእብራይስጥ «ዮም» የሚለው ቃል ) 24 ሰዓትን ፣ ወይም ብርሃንማውን ቀን ፣ ወይም ዛሬ ፣ ወይም ዘላለም፣ ወይም ቀጣይነት ያለው ቀን ፣ ወይም ያልተወሰነ ቀን ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ስለዚህ ስድስት ቀን ርዝመቱ ያልታወቀ ቀን ነው ማለት ነው። የግድ ስድስት ቀን እያንዳንዱ 24 ሰዓታት ያሉት ቀናት ማለት ላይሆን ይችላል።

ምናልባትም ቀጥሎ የሚገኘው ሐረግስ ምን ትርጉም ይኖረዋል? ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ። «ማታም ሆነ ቀንም ሆነ ስድስተኛ ቀን » ዘፍጥ.1፥31 ይህ ማለት ደግሞ ማታም ሆነ ጥዋት በአንድ ላይ የ24 ሰዓት ስፍር አንዳላቸው የሚገልጽ ነገር አለ? በፍጹም አይገልጽም ! «ማታና ጥዋት » ይህ አገላለጽ በሴማውያን ቋንቋ ውስጥ እንደ ዘይቤ የሚጠቀሙበት አገላለጽ ነው። እንደሌሎችም ዘይቤያዊ አገላለጾች ይህ ነው የተባለ ቀጥተኛ ትርጉም አይገኝለትም። «ዮም» የሚለውን የዕብራይስጥ ቃል በዕማሬያዊ ትርጉሙ በብዙ ቅርንጫፍ በመመልከትና ትርጉሙ ረጅምና ያልተወሰነ ጊዜን ለማመልከት እንደሚጠቀሙበት ማለት ነው። (ይህ ትንታኔ የተወሰደው ዶ/ር ኦቶ ጄ. ሄልዌግ ሪዝን ኦርግ በሚለው ዌብ ሳይት ከጻፉት ጽሑፍ የተወሰደ ነው። ፤)

ግልጽ ያልሆኑ የጊዜ አቀማመጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታዎች ተጠቀሶ እናገኛለን። የነገሥታትና የመንግሥታትንም ዘመን እንዲሁ ለጊዜ ማሳያ ሲጠቀምበት እንመለከታለን። «በንጉሥ ኢዮስያስ ጊዜ» ሲል ፣ ይህ ጊዜ በቀናት የሚሰፈር ሳይሆን በዓመታት የሚሰፈር ነው።

እንደዚሁም በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተቀመጠም ነገር አለ፤ “እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት ፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።» ይህም አገላለጽ፣ ዘይቤአዊ አገላለጽ ቢሆንም ቃል በቃል ተተርጉሞ፣ 1000 ዓመት በቀጥታ አንድ ቀን ይሆናል ማለት አይደለም። ዋናው ነጥቡ ግን የእግዚአብሔር የጊዜ አመዳደብና ጽንሰ ሐሳብ ከእኛ ጋር የተለያየ እንደሆነ ነው። በእኛ የቀን ብያኔ መሬት በራሷ ዛቢያ የምታደርገውን የዙረት ዑደት ተከትሎ 24 ሰዓት ነው። በዘፍጥረት የነበረውም የጊዜ ቀመርና ብያኔ እንደዛ ለመሆኑ የተቀመጠ መረጃ አለን?

በዘፍጥረት መጽሐፍ ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ እንዲህ ተጽፏል፡-

«እግዚአብሔር ዓምላክ ሰማይና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና ምድር ልደት ይህ ነው። » ዘፍጥ 2፡4

ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በስድስት ቀን ሳይሆን በአንድ ቀን ውስጥ ፈጠረ ማለቱ ነውን? አይደለም። አስቀድመን እንደተመለከትነው « ዮም » የሚለው ቃል ጊዜን የሚያመለክት ቢሆንም ከቶም የተወሰነ ጊዜን ብቻ ለይቶ የሚያመለክት ቃል አይደለም። ስለዚህ የዕብራይስጡ ቋንቋ ትርጉሙ እኛ እንደምንተረጉመው ግልጽና የተወሰነ ጊዜን የሚያመለክት ቢሆን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ይህ ቃል በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ እንዳለ ትርጉሙን መውሰድ እንችል ነበር። በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ መዝጊያ በትክክል እንዲህ ብለን መተርጎም ያስችለን ነበር ይኸውም ፡- ማታም ሆነ ቀንም ሆነ ስድስተኛው ቀን ስለዚህ ሰማይና ምድር ተሰርቶ ተፈጸመ።» ማለት እንችል ነበር።

ቀናትን በቢሊዮን ዓመታት ልክ መሰፈር እንችላለን፡

በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተጻፈው እግዚአብሔር ፍጥረትን እያንዳንዳቸው 24 ሰዓታት ባላቸው ስድስት ቀናት ውስጥ ሰርቶ ፈጸመ ብለን እንድናምን አያስገድደንም። ወይንም በዘፍጥረት መጽሐፍ ላይ ያለው የሥነፍጥረት ታሪክ በሳይንስ ባለው መረጃ ሰማይና መሬት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ ተሰርተው እንደተፈጸሙ የሚያስቀምጠውን መላምት የግድ የሚቃወም ተደርጎ መውሰድም አንችልም። ምናልባትም ሁለቱ ሃሳቦች የግድ ላይቃረኑ ይችላሉ።

የዕበራይስጡ ቋንቋ የጊዜ አመዳደብና ብያኔ ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ ፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተጠቀሰውን ቀን የጊዜውን ርዝመት ከአንድ አሰፋፈር ጋር ከምናያይዘው፥ ትልቁና አስፈላጊው መልዕክት በሆነው ምን ተፈጸመ ? በሚለው ነገር ላይ ብቻ ብናተኩር የበለጠ የሚጠቅም ይሆናል።

ለምሣሌ የአንድ ሚሊዮን ብር የሎቶሪ ዕጣ ባለዕድል ሆናችሁ ብትገኙ፥ የዕጣው አሸናፊ ከመሆናችሁና የዕድሉ ተጠቃሚ ከመሆናችሁ ባለፈ፥ ሎቶሪውን መቼ እንደገዛችሁትና ወይም ሎቶሪውን ለመግዛት የያዛችሁት ወረፋ ስንተኛ እንደነበር ማወቅ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

እንደገናም ዋናውና ትኩረት የሚገባው ቁምነገር የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብብሔር ዓምላክ መሬትን፣ ጸሐይን ፣ ከዋክብትንና ጠቅላላ ሕዋዉን ፣ ውቅያኖሶችንና ዕጽዋቶችን በባህር ውስጥ ሚኖሩትን ነፍሳትን ፣ በምድርም የሚርመሰመሱትንና ሚንቀሳቀሱትን እንስሳትን፥ ሰዎችን የመፍጠሩን ታሪክ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦልናል። እግዚአብሔር አምላክ በማያሻማ ሁኔታ ጥርት ባለ መንገድ በምንረዳው እውነት የሁሉ ነገር ፈጣሪና ጀማሪ ነው።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More