×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የእግዚአብሔር ህልዉና

ስላሴ

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ሦስት ዋና ክፍሎች የተከፈለ መሆኑን አስተውላችኋል፡፡ የመጀመሪያው ክፍል በእግዚአብሔር አብ ስለማመን ይናገራል፡፡ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ በአንድያ ልጁ፣ በጌታችን በኢየሱስ ስለማመን ይናገራል፡፡ ሦስተኛው ክፍል ደግሞ፣በመንፈስ ቅዱስ ስለማመንና ስለ እርሱ አገልግሎቶች ይዘረዝራል፡፡

በዚህ ስፍራ ግን፣ ሁሉም የጥንት የሃይማኖት መግለጫ ቅጂዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በተጻፉት አንቀጾች ላይ “እኔ … አምናለሁ” የሚሉትን ቃላት የማያስቀምጡ መሆኑን ማመልከት ይገባናል፡፡ በእነርሱ ምትክ፣ አብዛኞቹ “እና፣” የሚለውን ቃል የሚጠቀሙ ሲሆን በዚህም አውድ መሠረት ይህ ቃል “እኔ … አምናለሁ” ከሚለው ጋር እኩል ኃይል ያለው ነው፡፡ ሆኖም ግን በሁሉም ቢሆን፣ የእግዚአብሔርን ማንነት አስመልክቶ የሃይማኖት መግለጫው ክፍሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቤተክርስቲያን ተቀባይነትን ያገኘ ነው፡፡ ይህ ቀመር ስላሴአዊነት ነው፡፡ ያም፣ አንድ አምላክ አለ፣ እርሱም በሦስት ማንነቶች ይኖራል፣ እነርሱም እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

ይህም ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ በሰጠው ተልዕኮ በማቴዎስ 28፥19 ተመዝግቦ ከምናገኘው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው (ማቴ 28፥19)

በዚህ ስፍራ፣ ልክ በሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ ላይ እንደተቀመጠው ዓይነት፣ ሦስቱ ስሞች በእኩያ አገላለጥ በአንድነት መቀመጣቸው አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ስብእና ያላቸው አንድ አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡

የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ “ስላሴ” የሚለውን ቃል ለይቶ የማያስቀምጥ፣ ወይም ዝርዝርም የማይሰጥ መሆኑን እንቀበላለን፡፡ ነገር ግን የሃይማኖት መግለጫው የተመጠነ የእምነት መግለጫ እንጂ ዝርዝር የእምነት አንቀጽ አለመሆኑን ማስታወስ ይገባል፡፡ ከዚያም በቤተክርስቲያን ስርዓት ውስጥ አገልግሎት ላይ ሲውል፣ እነዚህን የእግዚአብሔር ሦስት ስብእናዎች በዚህ መንገድ መግለጡ የስላሴን ጽንሰ ሃሳብ እንደሚያነግብ በቤተክርስቲያን የሚገኝ ሰው ሁሉ ያውቃል፡፡

እንግዲህ አሁን፣ ሁሉም ክርስቲያን ስላሴ የሚለውን ቃል ፍቺ ሙሉ በሙሉ ሊረዳ ስለማይችል፣ ብዙ ማብራሪያ ለመስጠት ከመሞከር መታቀብ ይገባናል፡፡ ስላሴ በአብዛኛው (በተለምዶ) እንዲህ ይገለጣል፡

እግዚአብሔር አንድም ነው ሦስትም ነው፡፡

ንድ ነው ስንል መሠረታዊ ማንነቱን ማመልከታችን ሲሆን፣ ሦስት ነው ስንል ግን ራሳቸውን የቻሉ ማንነቶች ማለታችን ነው፡፡

እርግጥ ነው፣ የስላሴን ጽንሰ ሃሳብ በሰብዓዊ አዕምሮ ሙሉ በሙሉ መረዳት አዳጋች ነው፡፡ ምንም አንኳን፣ ስላሴ ክርስትና ከሚለይባቸው የእምነት አቋሞቹ ተቀዳሚና ዋነኛው ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር ኅላዌና ማንነት ከእኛ የልምምድ አድማስ እጅግ ሩቅ ነው ስለሆነ እኛ ሙሉ ለሙሉ ልንረዳው አንችልም፡፡ ግን እስኪ አንድ ጥያቄ እንጠይቅ ይህንን የመሰለው ውስብስብ አስተምህሮ በክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት ውስጥ ወሳኝ የማዕዘን ድንጋይ እንዴት ሊሆን ቻለ?

ስላሴ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በተቀደሰ መንገድ በምታነብበት ወቅት የምትረዳው ነገር ነው፡፡ አብ አምላክ እንደሆነ፣ ወልድ አምላክ እንደሆነ እና መንፈስ ቅዱስ አምላክ እንደሆነ ሁሉም የየራሳቸውን ማንነት ይዘው በግልጽ ትመለከታለህ፡፡ እናም ስለዚህ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት ከትምህርተ ስላሴ ጋር ማጣጣሙ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ [ዶ/ር ኤሪክ ኬ.ቲዮኔስ]

እንግዲያው ትምህርተ ስላሴ ለክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት የማዕዘን ድንጋይ ከሆነ፣ ከሁሉ አስቀድሜ ልረዳው ያስፈልገኛል ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነውና፡፡ ጽንሰ ሃሳቡ እንጂ ስ-ላ-ሴ የሚለው ቃል ፊደል በፊደል ተቀምጦ ስላማናገኘው እንዴት እንደምንረዳው መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ እንግዲያው ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እግዚአብሔር ማንነት የሚያስተምሩን ድምር ትምህርት እንደሚነግረን እግዚአብሔር አንድ ነው፣ ይህም አብ አምላክ ነው፣ ወልድ አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው- በአንድነትም፣ በጠቅላላው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ስንገልጠው እግዚአብሔር ስሉስ ቅዱስ ነው የሚለውን ድምዳሜ እንድንሰጥ ዋስትና ይሰጠናል፡፡ [ዶ/ር ሮበርት ጂ. ሊሰር]

እንግዲያው፣ እግዚአብሔር አንድ ነው ስንል፣ እግዚአብሔር አንድ አምላክ ነው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እያረጋገጥን (እየተሟገትንለት) ነው ማለት ነው፡፡ እናም እነዚህ ሦስት ኑባሬዎች እንዴት አንድ አምላክ እንደሆኑም ለማብራራት መሞከራችን ነው፡፡ ማንነት ወይንም ኑባሬ የሚለውን ቃል ስንጠቀም ሦስቱም ኅላዌ መለኮት የሚጋሩት እንድነት እንዳላቸው እያመለከትን ነው፡፡ ማለትም በእግዚአብሔር አብ ውስጥ ያለው እንደዚያው በወልድ ውስጥ አለ እንደዚውም በመንፈስ ቅዱስ ውስጥም አለ ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር በሦስትነትም ይኖራል ስንል፣ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው መለያ አላቸው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እየተሟገትንለት ነው፡፡ በራሳቸው ኅላዌ ያላቸው አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የሚዋሃዱ፣ አንዳቸው ከሌላቸው ጋር የሚጣጣሙ፣በቅርብ ግንኙነትም የተሳሰሩ ናቸው፡፡

በብዙ መንገዶች፣ የስላሴ ጽንሰ ሃሳብ ትልቅ ምስጢር ነው፡፡ ግን ደግሞ ስለ ልዕለተፈጥሮአዊው አምላካችን የተሰጡትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ሳያዛንፍ ጠቅለል አድርጎ የያዘም ነው፡፡

የስላሴ ነገር ለክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት ወሳኝ የሚሆነው በብዙ ምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል፣ በተጨማሪም ኢየሱስ እግዚአብሔር እራሱን በስውር የገለጠበት ብቻ ማለትም አይደለም፡፡ የአንድ አምላክ አማኞች ለምን እንደሆንንም ያብራራል፣ ምንም እንኳን ሦስቱን ስላሴ አብን፣ ወልድንና መንፈስ ቅዱስን ብናመልክና ወደ እነርሱ ብንጸልይም አንዱን ብቸኛ አምላክ እናመልካለን፡፡ ከዚህም ባሻገር፣ ለሦስቱም የስላሴ አካላት ተገቢ ክብር እንድንሰጥ ያስችለናል፡፡ በተጨማሪም ከሦስቱ ስላሴዎች የአንዱ ኅልውናና ረድኤት የራሱ የእግዚአብሔር እንደሆነ እንድናውቅም ይሞግተናል፡፡ በመሠረቱ፣ የስላሴ እምነት ለበርካታ ክርስቲያናዊ ሃሳቦች መሠረታዊና ታሪካዊ ክርስትናን ያለ እርሱ ማሰብ አዳጋች ነው፡፡

ከስላሴ አንጻር በሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ የተቀመጠውን ትምህርተ እግዚአብሔርን ከተመለከትን፣ አንዳቸው ከሌላቸው ተለይተው የሚታወቁበት የራሳቸው ማንነት ያላቸውን የስላሴ አካላትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ሃሳብ ለመገንዘብ ዝግጁ ነን ማለት ነው፡፡

ማንነት

ከአብ አንጻር፣ የሃይማኖት መግለጫው የሁሉን ቻይነትን የባሕርይ መገለጫ ይሰጠዋል፣ የሰማይና የምድር ፈጣሪነትንም ታሪካዊ ጭብጥ ይገልጣል፡፡ እግዚአብሔር ከሉዓላዊነቱና ከማይገደበው ኃይሉ እጅግ የሚልቅ የባሕርይ መገለጫ አለው፣ ፍጥረተ ዓለምንም ከመፍጠርም የዘለለ ዕፁብ ድንቅ ተግባር አለው፡፡ በሃይማኖት መግለጫው ላይ ስለ አብ የተቀመጠው መግለጫ በሉዓላዊና መለኮታዊ አምላክ እንደሚያምኑ ከሚገልጹ ሌሎች እምነቶች ክርስትናን ለየት በሚያደርግ መንገድ አላስቀመጠውም፡፡ ነገር ግን የቀደመችው ቤተክርስቲያን እነዚህ መግለጫዎች አንድ ሰው ስለ አብ ሊኖረው የሚገባውን እምነት አስመልክቶ ለመግለጥ የሚያስችሉት ብቁና ከክርስትና ጋር የሚጣጣሙ ናቸው በማለት አረጋግጣለች፡፡ እናም ክርስትናን በዙሪያው ካሉት ሃይማኖቶች ለመለየት በሃይማኖት መግለጫው በሌላ አንቀጽ ማስቀመጥን መርጠዋል፡፡

ለመጥቀስ ያህል፣ የሃይማኖት መግለጫው ስለ ወልድ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ይናገራል፡፡ ምንም እንኳን ከእርሱ የባህርይ መገለጫዎች አንዳቸውንም ባይጠቅስም፣ ስለ ምድራዊ ሕይወቱና አገልግሎቱ ብዙ ዝርዝሮችን ጠቅሷል፡፡ እነዚያም ከቤተክርስቲያን ውጪ ባሉቱ ዘንድ የሚካዱ ናቸው፡፡

የሃይማኖት መግለጫው፣ ስለ ኢየሱስ ትስጉት፣ እንደ ሰብዓዊ ሕፃን ወደ ምድር ስለመምጣቱ፣ እንደ ፍፁም ሰው ስለ መኖሩ ያወሳል፡፡ በተጨማሪም ስለ መከራው፣ ስለ ሞቱ፣ ስለ መቀበሩ፣ ስለ ትንሣኤው እና ወደ ሰማይ ስለ ማረጉ ይናገራል፡፡ እነዚህ መሠረታዊ እውነታዎች ከተከናወኑበት ጊዜ አንስቶ የማያምኑ ሰዎች ይከዱዋቸው እንደነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል፡፡

በዛሬውም ዘመን አንኳን፣ ለዘብተኛ የታሪክ እና የነገረ-መለኮት ምሁራን፣ በርካታ ክርስቲያናዊ የስህተት አስተምህሮዎችና የተሳሳቱ ሃይማኖቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ እነዚህን እውነታዎች ይክዳሉ፡፡ ለምሳሌ፣ እስልምና ኢየሱስ የእግዚአብሔር እውነተኛ ነቢይ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ሆኖም ግን እርሱ ፈጽሞ አልተሰቀለም ወይም ከሞት አልተነሣም ይላል ደግሞም መለኮትነቱንም ይክዳል፡፡

በመጨረሻም የሃይማኖት መግለጫው በመጨረሻው ቀን ኢየሱስ በሰው ዘር ሁሉ ላይ እንደሚፈርድ፣ ክፉዎችንም እንደሚኮንናቸው፣ አማኞችን ግን ዘላለማዊ የተባረከ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ይገልፃል፡፡

የሃይማኖት መግለጫው፣ ስለ መንፈስ ቅዱስም ድንግል ማርያም ኢየሱስን እንድትፀንስ ማድረጉን ይናገራል፡፡ ከዚያም ሌላ፣ ከስላሴ አንዱ መሆኑን በስሱ ገለጥ ያደርጋል፡፡ ሆኖም ግን፣ ለየት ባለ መንገድ፣ የሃይማኖት መግለጫው መንፈስ ቅዱስን ከቤተክርስቲያን ጋር ያቆራኘውና እኛም አሁንና ወደፊት ከምንለማመደው ድነት ጋር ያገናኘዋል፡፡

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More