×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የህይወት ጥያቄዎች

ከሱስ መላቀቅ

የሱስ ምንነት እና ሱስን የመላቀቀያ ኃይል፤ እውነተኛ ታሪክ፡

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

የአንድ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ ሰው ህይወት የትያትር ቤት መድረክ ይመስላል። ተቀምጬበት ከነበረው ወንበር ላይ ተንሸራትቼ መሬት ላይ ከተነጠፈው ምንጣፍ ላይ እስከነሲጋራዬ እወድቃለሁ፤ 14 ፌርማታ ያህል በእግሬ ከተጓዝኩ በኋላ መኪናዬን ካቆምኩባት ስፋራ ሳጣውና የት እንደማገኘው መገመት ሲሳነኝ እንደማለት ነው።

አንድ ቀን ማታ ደግሞ ወደ ቤተሰቦቼ ቤት እየነዳሁ ስሄድ የፓሊስ መኪና መብራት በመስኮቴ ውስጥ ተመለከትኩና መኪናዬን ከነበረበት ፍጥነት በቀስታ አቆምኩት። የዚህን ጊዜ ሳስታውል ለካ ለብሼ የነበረው ጋዋን እና አረንጓዴ የመኝታ ልብስ ሱሪ ብቻ ነበር። ወዲያውኑ ላለፉት ጥቂት ሰዓታት ምን ያህል መጠጥ እንደጠጣሁ፣ ኪሴ ውስጥ ያለውን ግማሽ ኪሎ አደንዳዥ ዕፅና በመኪናዬ ውስጥ ተበትኖ የሚገኘውን ይህ ነው የማይባል ቆሻሻ ማስተዋል ጀመርኩ።

ብዙ ጊዜም እሁድ ጠዋቴ ከ3-5 ሰዓት ቤተሰቦቼን እየሄድኩ እጎበኛቸው ነበር። እቤት መሄዴ ግን ከቤተሰቦቼ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ሳይሆን ብር ሲቸግረኝ እንዲሰጡኝ ነበር። ነገር ግን የዛን ማታ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ቢሆንም ቤተሰቦቼ ቤተክርስቲያን እስኪሄዱ መጠበቅ አልቻልኩም ነበር።

ሰማያዊ ልብስ ለብሶ የከተማውን አውራ መንገድ ለመጠበቅ ቃል የገባውን ፖሊስ መጥቶ የመኪናዬን መስኮት ሲያንኳኳ ግራ አጋባኝ አፌ ላይ የነበረውን ሲጋራ ስጠጣው ከነበረው የቆርቆሮ ጣሳ ውስጥ ከተትኩትኝ መስኮቴን ዝቅ አደረግኩ። ስለአለባበሴም ሆን ስለምሽቱ እንዲሁም ስለሚንቀጠቀጠው እጄ ምንም ሳይል ሚዳቆዎቹ መንገድ ሲያቋርጡ በአሽከርካሪዎች ላይ ሊያደርሱ ስለሚችሉት አደጋ ያወራልኝ ጀመር ይቅር ባይ ሆነና የመቅጫ ወረቀት ሳይሰጠኝ ወደመኪናው ተመለሰ። ሲያየኝ የደከመኝ እንጂ ጠጥቼ ማሽከረክር እንዳልመሰለው ተረዳሁ። በጣም ጠጪ ከመሆኔ የተነሳ በአንድ ጊዜ ብዙ ብላንዲ መጠጥ ጠጥቼ የሰከርኩ አልመስልም ነበር። እንዲያውም ብዙ ከመጠጣቴ የተነሳ ሰክሬ እንኳን የጤነኛነት ስሜት ይሰማኝ ነበር። ፖሊሱ መኪናውን አስነስቶ ሲሄድ እኔ የተረጋጋ ስሜት ውስጥ ብሆንም በጣም እያዘንኩ መኪናዬን አስነስቼ ጉዞዬን ቀጠልኩ።

ሱሰኝነት ምን ይመስላል? ግለኝነት

እራሴን ስለማላምነው ለትንሽ ሰዓት እንኳን ብቻዬን ቢተውኝ ምን እንደማደርግ አላውቅም ነበር። ለትንሽ ጊዜም ወደ መዝናኛ ቤቶች እየሄድኩም ራሴን ለማዝናናት እሞክርና አንዳንድ የማውቃቸውን ሰዎች ለማናገር ይደብረኝና ለአንድ አስር ደቂቃ ያህል ቆይቼ ሲጋራ ለማጨስ የምወጣ መስዬ ወደ ውጪ እወጣና መኪና ውስጥ ገብቼ እሄድ ነበር። ጓደኞቼም እየደወሉ የት እንደሄድኩ ይጠይቁኝ ነበር። ከጊዜ በኃላ ግን እነርሱም ሰልችቷቸው መደወል አቆሙ።

በፊልም ላይ ሰዎች ጠዋት ሲነሱ የማያውቁት አልጋ ላይ ወይም ሶፋ ላይ ተኝተው ራሳቸውን ሲያገኙት የሚያዝናና ይመስላል። እኔ ግን ጠዋት ስነሳ ራሴን መኪናዬ ውስጥ ሁኜ የተሳሳተ ቤት ጋር ቆሞ ሳገኘው እንዲሁም የሌላ ሰው ቤት መሬት ምንጣፍ ላይ ተኝቼ ሳገኘው በጣም ይደብረኝና እናደድ ነበር።

ቤቴ መቀመጥን እመርጣለሁ የምወጣውም ለማጨስ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ለመውሰድ ስፈልግ ብቻ ነበር። ምክንያቱም ምን አጠፋሁ ምን አደረኩ የሚሉትን ሀሳቦች ይቀንስልኝ ስለነበር ነው። ስለዚህም ራሴን ከሌላው አለም ለይቼ እና አግልዬ ክፍሌን ቆልፌ መጋረጃዎቹንም ሁሉ ዘግቼ ጨለማ ውስጥ ለብዙ ቀናት እቀመጥ ነበር።

የሱስ ዋና መሠረቱ ምንድነው? የአእምሮ ችግር

በእኔ አስተሳሰብ በአልኮል ጠጪ እና በአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ ብዙም ልዩነት ባይኖረውም እንደነዚህ አይነት ሰዎች ጋር መነጋገር ግን ከአንድ ህፃን ጋር እንደማውራት ነው። እነኚህ ሰዎች በማንኛውም የአካላዊ ስሜት ውስጥ ይገኛሉ። ነገር ግን በአእምሮ የአለመብሰል ሁኔታ ይታይባቸዋል። ለሚያዳምጠን ሰው ሁሉ ስለ ህይወትና እና ስለ እግዚአብሔር ክፉነት የሚያሳይ ረጅምና ልብ አርድ ንግግሮችን ማድረግ ያስደስተኝ ነበር። ንግግሬም በጨመረና የሚያሳዝን በሆነ ቁጥር አድማጮቼ እየቀነሱ ይሄዳሉ።

ጨለማ ለእኔ የሚመች ቦታ ነበር። እንደፈለኩ እጠጣለሁ አጨሳለሁ እንዲሁም ራሴን በስለት የተለያዩ የሰውነት አካሌ ላይ እወጋ ነበር። ነፃነት ማወቄ፣ የአእምሮ እረፍትና ግዴለሽ መሆኔ ለችግሬ ሁሉ መፍትሄ መስለው ይታዩኝ ነበር። የማመልጥባቸው ነገሮች ብዬ ያሰብኳቸው ሁሉ ግን እስር ቤት ሆኑብኝ። እግዚአብሔር መጥፎ ሁኔታዎችን ወስዶ ወደ ጥሩ ነገር መለወጥ እንደሚችል አውቅ ነበር። በህይወቴም የማየው እውነታ ነው። ሆስፒታል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስለምጀምረው አዲስ ሕይወት ስላለፍኩባቸው አስር የባከኑ ዓመታትና በቀሪው ህይወቴ ላይ ምን አይነት ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አስብ ነበር። ላለፉት ጥቂት ዓመታት እግዚአብሔር በእኔ ህይወት ውስጥ የት ጋር ሥራ እንደሰራ አሰላስል ነበር። ብቻዬን የሆንኩ ሲመስለኝና ሰዎች ጥለውኝ ሲሄዱ አብሮኝ ነበር። ያንን ሁሉ ጊዜስ በሌሊት ሰክሬ ስነዳ አብሮኝ ነበር። ጠዋትስ የማላውቀው ቦታ ራሴን ሳገኘው አብሮኝ ነበር።

በብዙ ማለፍ ውስጥ ግን የእግዚአብሔር ጥበቃውና መሪነቱ አሁን ይታየኛል። የዛን ጊዜ ግን ባስተውለው ኖሮ ለምን ብዬ መጠየቄ አይቀርም ነበር። እኔን በራሴ ላይ ጌታ እድርጌ ሾሜ ለአለም እንኳን አንድ ነገር አላበረከትኩም። ምን ያህል ዋጋ ቢኖረኝ ነው እግዚአብሔር ሊያድነኝ የፈለገው? በውስጤ ይህ ሁሉ መጠጥና መድሃኒቶችን መውሰድ ከዛ ጨለማ ምሽት እንደማያስመልጠኝ እያወኩ ለመተው እንኳን አልሞከርኩም ምክንያቱም በምንም አልረካም ነበርና ነው።

የሱሰኝነት ውጤት ምንድነው ?

እግዚአብሔርን ከዚህ ሁሉ ነገር እንዲያወጣኝ እያለቀስኩ እለምነው ነበር። ሁል ጊዜ ለእኔ የስልኩ ጩኸት፣ የበሩ መንኳኳት ትምህርት፣ ሥራ . . . ወዘተ አስፈሪ ነበር ። በተለይ ግን ራሴን በጣም እፈራው ነበር። ብዙውን ጊዜ ምን እንደማደርግ አላውቅም ነበር። የምበላው ዳቦ ላይ ቅቤ መቀባት እጀምርና በያዝኩት ቢላ እራሴን እንድገል እገፋፋ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ሞትን እመርጣለሁ። ግን ደግሞ አሟሟቴን ሳሰስበው ምን አይነት አሳዛኝ እንደሚሆን መገመት አያቅትም። ምን አድርጌ እንዳለፍኩ ሳይሆን ምን ማድረግ እችል እንደነበር ያወሩልኛል። ቤተሰቦቼ እራሳቸውን እንደተጠያቂነት አስበው በሀፍረት ይኖራሉ። ለወንድሞቼም መጥፎ አሻራን ትቼ ከመሄድ ሌላ አልጠቀምኳቸውም። የክፍል ጓደኞቼም ያለፈውን አመት እያስታወሱ ይኖራሉ። የወደፊት ሚስቴም ልትሆን የምትችለውም አታውቀኝም። ልጆቼም አይወለዱም ህይወቴ በዚህ ሁኔታ እንዲያልቅ አልፈልግም። ግን መውጫ መንገዱ አልታይህ አለኝ። ጠጪ፣ አጫሽ፣ ትምህርቱን ያቋረጠ፣ ያልተሳካለት ልጅ፤ ለቤተሰቦቼ ሸክም፤ እሆናለሁ ብሎ ገምቶ የማያውቀውን የሆነ ሰው እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር።

ቆራጥ መሆን ከሱስ ለመላቀቅ መፍትሔ አይደለም

ከሁለት ወር ህክምና እና ከምንም አይነት ለውጥ በኋላ ከመቼውም ይልቅ በጣም ተዳከምኩ። ለ60 ቀናት ምንም ዓይነት መጠጥም ሆነ መድሃኒት መጠቀም ባቆምም ጤነኛ ሰዎች ግን መሆን አልቻልኩም። ድሮ ጠጪ ሆኜ ሳለሁ በሃሳቤም ሆነ በሕይወቴ ላይ ከማልማቸው ግቦች ጭንቀት ማስታገሻ ነበረኝ። አሁን ግን ደካማ እና ረዳት የሌለኝ ሆንኩ። መፍትሄ ይሆኑኛል ብዬ ያሰብኳቸው መጠጥና አደንዛዥ እጽ የለኝም።

ብዙ ጊዜም ህመምና ስቃይ በተሞላበት ጩኸት በእግዚአብሔር ፊት ወድቄ እርዳኝ ብዬ አለቅሳለሁ። ይሁን እንጂ ሙሉ በሙሉ ራሴን ለእግዚአብሔር አሳልፌ መስጠት ግን አልቻልኩም። አንድ ማታ ግን ክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብዬ በእውነትና በመንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጀመርኩ። ምን ያህል መለወጥና መቀየር እንደምፈልግ ሱሰኛ ማንነቴን ለእርሱ ማስገዛት እንደምፈልግና በእራሴ ላይ ትክክለኛውንና አስፈላጊውን እርምጃ እንደምወስድ ነገርሁት ለመጀመሪያም ጊዜ ሰላም ያለው እንቅልፍ ተኝቼ አደርኩ።

የዛን ቀን ፀሎት ከሌሎች ሁሉ የሚለይ የነበረው በአንድ ነገር ብቻ ነበር። እምነት የተሞላበት ነበር። በመጥፎ እና አስፈሬ ጊዜዎች እንኳን እግዚአብሔር ነፃ እንደሚያወጣኝ እያወቅኩ ችግሬን ለእግዚአብሔር አሳልፌ ሰጥቼ የእርሱን ምሪትና ብልህነት እንደመጠየቅ እኔ ባሰብኳቸው መንገዶች እንዲሆኑ እፈልግ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ግን ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን አምኜ ነገሬን ሁሉ እርሱ እንዲሰራልኝ እጅ ሰጠሁ።

ብዙ ሰዎች ሱሰኝነት ቆራጥ በመሆን ማለፍ ይቻላል ብለው ያስባሉ። ለሱሰኞች ግን ያለመጠጥና ያለ እፅ መኖር ማለት በጣም አዳጋች ነገር ነው። ሱሰኝነት ውድቀታቸው ቢሆንም ያላቸው አንድ ጓደኛ ግን እርሱ ብቻ ነው። በዚህ ሁሉ ቅዠት ህይወት ውስጥ ግን ቆራጥ ሆኖ መገኘት በጣም ይከብዳል።

ከሱሰኝነት የበለጠ ነገር አለ?

ሱሰኝነት የሚፈልገውን ነገር እስከሚያገኝ ድረስ ማቆም የማያስችል ውጫዊ ሀይል እንደማለት ነው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሀይል ቁጥጥር ውስጥ ሲገባ በጣም ቀላል ነው። ልክ የእኔ ቆራጥነትና ሀይል በሱሰኝነት ውጊያ ውስጥ ደካማ እንደሆነ ሁሉ ሱሰኝነትም በእግዚአብሔር ሀይል ሲታይ እንዲሁ ነው። ሱሰኝነት የሰይጣን ዋነኛውና ጠንካራ መሳሪያ ሲሆን ይህ በሽታ ልክ በአጋንንት እስራት ስር እንደመሆን ነው ብዬ እገምታለሁ። ከሱሰኝነት መዳን ማለት ትክክለኛ የመንፈስ ውጊያ እንደማሸነፍ ነው።

አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው ስላለፈው ህይወቴ ምንም ቅር አልሰኝበትም። ለማስታወስ የማልፈልጋቸው ብዙ መጥፎ ትዝታዎች ቢኖሩኝም ጥሩ ነገር ግን ወደ ህይወቴ ሊያመጡ ችለዋል። በእነዚህ ነገሮች ውስጥ ደግሞ የእግዚአብሔር ክብር ተገልጦበታል። በእንደዚህ አይነት ጉዳት እና ሀይል ማጣት ውስጥ ባላልፍ ኖሮ ይህ ግትር እና ራስ ወዳድ ማንነቴ እግዚአብሔርን ወደማወቅ አይመጣም ነበር። የእኔ እግዚአብሔርን ወደማወቅ መምጣት በግዳጅም ነበር ብዬ አስባለሁ።

ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ ግንኙነትም ቀስ በቀስ ማደግ ጀመረ አንዳንድ ጊዜ የማልበገር እና እምነት የለሽ ብሆንም ሱሰኝነቴ እግዚአብሔርን እንዳውቅ እንደረዳኝ ሁሉ እነዚህ ነገሮችም ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝን ቅርርብና እምነት ሊጨምሩልኝ ችለዋል። የእኔ የማገገም ፕሮግራም ቀላል ነው። ወደድኩም ጠላሁም እግዚአብሔርን መፈለግ ነው።

ጳውሎስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለጓደኞቹና ለኢየሱስ ተከታዮች ለነበሩት እንዲህ ብሎ ፅፏል

‹‹በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንፁህ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ምስጋና ቢሆን እነዚህን አስቡ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።››

በመጠጥና በአደንዛዥ እፅ ላይ ከመደገፍ ይልቅ በእነዚህ ቃሎች ላይ መደገፍ ለእኔ በጣም ያስደስተኛል።

ከሱሰኝነት ምን አገኘሁ?

የድሮ ማንነቴ አስቀያሚ ቢሆንም በውስጤ ግን የማልጥለው ውድ ቅርስ ሆኗል። አሁን ደግሞ ሌሎችን እኔ ከወጣሁበት ማውጣት ትልቅ ሃላፊነት ሆኗል። የተለማመድነውና ያለፍንበት ነገር በመሀከላችን ትልቅ መቀራረብና መጣመርን ፈጥሯል። በየሳምንቱ ከሱሰኝነት ለመላቀቅ የሚፈልግ ሰው ወደ እኔ መጥቶ ያጋጠመውን ነገር ያወራኛል። ይህም እንዴት ወደ መጠጥ እጁን እንዲያነሳ እንደገፋፋው ሲያጫውተኝ በፍርሃት ነበር። ምክንያቱም በዚህች ነገር መገመትን ስለሚፈራ ሲጨርሱም አይን ለአይን ላለመተያየት አንገታቸውን ይደፋሉ። እኔም ሳቅ ብዬ እኔም እንደሱ አደርግ ነበር እላቸዋለሁ። ወዲያውኑም የፍርሃትና የመገለል ስሜታቸው ከላያቸው ላይ ይነሳል። ከዛም ግን አሁን ያለሁበትን ጥሩ ቦታ እነግራቸዋለሁ። ለአንተ ተአምር ሲደረግልህ አንድ ነገር ነው። በሌላ ሰው ተአምራት ላይ ግን አንተ ትልቅ ሚና ስትጫወት በጣም ያስደስታል።

እንዴት ሰካራም ሱሰኛና ህግን የማያከብር የነበረ ሰው ለእግዚአብሔር መልእክተኛ ይሆንለታል? ድሮ ሱሰኛ እያለሁ በዚች ምድር ኖርኩ አልኖርኩ ምንም ጥቅም ያለኝ የማይመስለኝ ሰው አሁን እንዴት የእግዚአብሔርን ስራ እሰራለሁ? የእግዚአብሔር ሥራ እጅግ አስገራሚና ለሰው የሚያስደንቅ ስለሆነ ለዚህ ሁሉ ጥያቄዎች የምመልሰው የለኝም። እግዚአብሔርም ሰው አይን በማይገቡ ሰዎች መጠቀም ስለሚችልበትና ስለሚወድ እንደነዚህ አይነት ጥያቄዎችንም እያነሳሁ ጊዜዬን አልፈጅም።

ወደ ትምህርት ቤት ተመልሼ በክብር ተመርቄ በመውጣት አልሜው የማላውቀውን ነገር አየሁ። ያቺ ሌሊት በጉልበቶቼ ወድቄ እግዚአብሔርን የለመንኩበት ቀን ካለፈች 3 ዓመታትን አስቆጠረች። እስካሁንም ድረስ እንደዚያን ጊዜ ይሰማኝ የነበረው የተስፋቢስነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም።

ህይወቴም ጥሩ ከሚባል በላይ ሆነልኝ። ሀብታም ነኝ ወይም በዚህች ምድር ላይ ምንም ማድረግ የሚያቅተኝ የለም ማለቴ ሳይሆን ሁል ጊዜ ጠዋት ተነስቼ የራሴን ፈቃድ ለእግዚአብሔር አሳልፌ ሰጥቼ በእርሱ ፈቃድ መመላለስና በእኔ እንዲሰራ ስፀልይ የሚመለስልኝ ፀሎቴ ሆነ እነዚህም እድሎች ከአጠገቤ የማይጠፉ ሆኑ ።

ድሮ እንቅልፌን እንድተኛ በጣም ብዙ መጠጥ እጠጣና እራሴን ስቼ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ተነስቼ ደግሞ መልሼ ይህንኑ እደግም ነበር። አሁን ግን ለትልቁ እግዚአብሔር ቀኑን ሙሉ ምን እንደሰራሁለት እያሰብኩኝ እተኛለሁ። እንግዲህ እንደነዚህ ያሉ ቀናት በእርካታ የሚታለፉ ከሆኑ ከዚህ በላይ ምን ሊገኝ እንደሚችል አላውቅም።

በአሁኑ ጊዜ በአንድ ኮሌጅ የማገገሚያ ፕሮግራም ውስጥ ሌሎች ህይወታቸውን ለመቀየርና በሱሰኝነት ውስጥ ያጡትን ነገር ለማግኘት እንደሚችሉና ምን አይነት የሚያስደስትና ያልተጠበቀ ባርኮት እግዚአብሔር በፊታቸው እንዳስቀመጠላቸው እንዲያውቁ በመርዳት ላይ እገኛሁ።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More