×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የህይወት ጥያቄዎች

ኮሮናሻይረስ (ኮቪድ- 19) ጭንቀቱን እንዴት መቋቋም ይቻላል?

የሚከተለው የኮሮናቫይረስን አስጨናቂነት እንዴት መቋቋም እንደሚቻልና ከስጋት ነፃ ወጥተው በታላቅ ሰላም መኖር እንዲችሉ የሚያሳይ አስተማማኝ መንገድ ነው።

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በሜሪልን አዳምሰን

ለብዙዎች ቫይረሱ ወደሚያስፈራ ደረጃ አድጓል። በሽታውም አዳዲስ ሀገራትንና ተጨማሪ ሞቶችን እያስመዘገበ ነው።

ነገር ግን እርሶ ጭንቅ የሆነቦት ሌሎች ነገሮች ይሆናሉ። በየቀኑ በብዙ አስጨናቂ ነገሮች እንጠቃለን። የተወሰኑትን ለመዘርዘር እንኳን፦ ሽብርተኝነት፣የአየር ፀባይ ለውጥ፣ዘረኝነት፣ጦርነት፣የመንግስታት መቃወስ፣ድህነት፣ፆታዊ ጥቃቶች፣ባርነት፣የተፈጥሮ አደጋዎች፣የግል ገንዘብ አያያዝ፣በሽታ፣ስራ ማጣት፣ጎጂ ግንኙነቶች፣ሱስ...ወዘተ

ከነዚህም መሀል አይመለከተኘም የምንለው ላይኖር ይችላል።

በዚህ ዘመን በግል ጉዳያችን ብቻ አይደለም የተያዝነው። የኢንተርኔት መግዘፍ የአለምአቀፍ ዜጎች አድርጎናል። በየትም ስፍራ ስለተፈጠሩ ችግሮች በየቀኑና በየደቂቃው እየተነገረን ነው።

ዜና ዘጋቢዎችም አስፈሪ ነገሮች ላይ ማተኮር የሚወደውን የሰው ልጅን ባህርይ በደምብ ይምግባሉ።
ነገር ግን ብዙ አስጨናቂ ነገሮች መነሻቸው ግላዊ ነው፤በህይወታችን የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው።
የመስመጥን ስሜት የሚሰጡ፤ ነገሮቻችን መቆጣጠር እንድማንችል የሚያሰማን። በአደጋ ውስጥ እንዳለን፣ ሃይል እንደሌልን፣ ማምለጥ እንደማንችልና ነገሮችን መለወጥ የማንችል እንደሆንን የሚያሰማን ፍርሃት ነው።

ታድያ በዚህ ሁሉ መሃል ሰላምን ማግኛ መንገድ አለ ወይ ልትሉ ትችላላችሁ፣ መልሱም አዎ ነው።

በኮሮናቫይረስ ወሬ መሃል ሰላም

ይህ ጽሁፍ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እናም ሌሎች አስጭናቂ ሁኔታዎች ፊት ስላምን ለማግኘት እውነተኛና አስተማማኝ የሆኑ መንገዶችን ይሰጣቿል።
በመጀመሪያ ስለ መድሃኒት እናውራ። በተከታታይ በጭንቀት የምትጠቁ ከሆነና ጭንቀቱ ወደ ሃዘንና ራስን መጉዳት የሚያዘቅጣችሁ ከሆነ እባክዎትን ወደ ሃኪም ሄደው ያማክሩ። አንዳንዴ በሰውነትዎ ውስጥ የኬሚካል አለመመጣጠን ሲፈጠር መድሃኒት መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል። አንዳንድ ጎጂ የአስተሳሰብ መስመሮች በህክምና አዲስ ቅያስ እንዲወጣላቸው ያስፈልጋል።

ልክ የዲያቢቲስ በሽታ ኢንሱሊን እንደሚያስፈልግው፣ነገሮችን በተረጋጋ አእምሮ መመልከት እንዲችሉ የሚያግዙ መድሃኒቶች አሉ። በጭንቀት የሚሰቃዩ ሰዎችን ህይወት በደምብ ማሻሻል እንደሚችሉ መድሃኒቶች አሳይተዋል።
ነገር ግን ተረጋግቶ ማሰብ ሙሉ መፍትሄው ሳይሆን የመፍትሄው አንድ አካል ነው። ይረዳናል ነገር ግን ሙሉ ሰላምን አይሰጠንም። እግሩ እንደተሰበረ ሰው ነው፣ መራመድ ቢያቆም ይረዳዋል ግን እግሩ እንደተሰበረ ነው የሚቀረው።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሃገሬ ተዳከመ የሚል ዜና ሊረዳዎት ይችላል ነገር ግን ሌሎች ብዙ የጭንቀት ምንጮች አሉ። ህይወት ብዙ እንቅፋቶች አሏት። የሚያስፈልጋቹህ ሁሉንም የሚያልፍ፣ በከባድ ሁኔታዎች መሃል ልባችሁንም አእምሮአችሁን ማሳረፍ የሚችል ሰላም ነው።

በአስጭናቂ ሁኔታዎች ውስጥ አስተማማኝ የሆነ አካሄድ ለብዙ አመታት በእግዚአብሄር የማላምን ሰው እያለሁ፣ ሁሌም አስተማማኝ የሆነና በህይወቴና በስራዬ ሁሉ የሚመራኝ አንድ ፍልስፍና እፈልግ ነበር።እነ ሳርትረ፣ፕሌቶ፣ሶቅራጠስ፣ዶስቶዬቭስኪ፣ኒቼ፣ሁመ የመሳስሉትን ፈላስፋዎች አጥና ነበር።
በኋላ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ፍልስፍና ጎዶሎ ነው።ችግሮቼ ሁሉ ሳይነኩ ቁጭ እንዳሉ ቀሩ።
አንዳንደ ሰዎች "ነገሮችን ለየት አድርገሽ ተመልከቺ፣ ነገሮች ያን ያህል አልከፉም” ይሉኛል።ነገር ግን ኮሮናቫየረስን፣ብዙ ሺ ሰዎች እየታመሙ ሳሉና የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሳለ ለየት ባለ አመለካከት መመልከት ከባድ ነው።

በሁኔታዎች ያልተገደበን ሰላም በመፈለግ ላይ ሳለሁ ሃይማኖት ባዶ አማራጭ ነበር የሚመስለው።መንፈሳዊ ስርአተ፣ እምነቶችን፣ተመስጦ ወይም ደግሞ ሀግጋት እየፈለግኩኝ አልነበረም።እንደ ተራ ጊዜ ማሳለፊያዎች ነው የታዩኝ።ተጨባጭነት የሌላቸው አዎንታዊ አመለካከቶች ወይም ጥሩ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርጉ ብቻ ነው የመሰሉኝ።

ህይወት በእውነት ከባድ እንደሆነች አውቅ ነበር። ስለዚህ ህይወት ምንም ፈተና ብትወረውርብኝ እንድጋፈጠው የሚረዳኝ አስተማማኝ መንገድን ነው የፈለግኩት።

ብዙ ሰዎች ሳይንስ ለቫይረሱ ፈውስም መከላኪያ እንደሚያገኝ ተስፋ ያደርጋሉ።ነገር ግን የቫይረሶች ባህሪ የሚያሳዩን ነገር ቢኖር ለብዙ አመታት እየተቀየረና ውስብስብ እየሆነ ለብዙ አመታት ገና እንደማይጠፋ ነው።ሳይንስ ሁሉን አወቅ ወይም ሁሉን ቻይ አይደለም።

ታዲያ ማይደበዝዝና ማይጠፋውን ሰላም በመፈለግ ላይ ሳለሁ፣ከአንዲት ከምደነቅባት አንዲት ሴት ጋር ጓደኝነት ጀመርኩ።በጣም ብዙ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ታወራ ነበር፤ “እውነት እግዚአብሔር አል?" ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ።

እግዚአብሔር ሊኖር ይችላል የሚለው አማራጭ ረጅም ወደሆነ የመጠየቅ፣የመመርመርና ብዙ አእምሮአዊ መከላከያዎችን ሙጥኝ ብሎ የመያዝ መንገድ ላይ መራኝ።እውነተኛ ያልሆነን ነገር ወደማመን መታለል በፍጹም የማልፈልገው ነገር ነበር።

ሳይንስ ወደ መፍትሄ ጠቆመኝ

ከአንድ አመት ተኩል ምርምር በኋላ ስለ እግዚአብሔር የነበሩትን ማስረጃዎች ማለፍ በጣም ከባድ ሆነብኝ።ሳይንስ ነበር ስለ እግዚአብሔር መኖር ያሳመነኝ፤የምድር ከጸሃይ ጋር በፍጹም መጣመሯ፣የውሃ ውስብስብ አቀማመር፣የሰው ልጅ አካል አቀራረጽ...ወዘተ።

በምድር ላይ ህይወት እንዲኖር የሚያስፈልጓቸው ሳይንሳዊ ቅድመሁኔታዎች ብዛት የአጋጣሚ ውጤቶች ነን የሚለውን ሃሳብ ፍጹም ውሸት እንደሆነ አሳየኝ።ስለዚህ ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖረኝ ወደ ህይወቴ እንዲመጣ እግዚአብሔርን ጋበዝኩት።
በእውነትም “እግዚአብሔር መጠጊያችንና ሃይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው።"1

ፍርሃት ባለበት በሰላም መኖር

እግዚአብሔር እንዳለና ስለኛ እንደሚያስብ ማወቅ በማንኛውም ሁኔታ በሰላም ለመሆን ያለንን ብቃት በጣም ይለውጠዋል።ላስረዳችሁ፦
አንድ የ8 አመት ልጅ በአንድ ጎረምሳ ይጠቃል።ምሳውን ይቀማዋል፣ይገፈታተረዋል እናም ያዋርደዋል።ይሄንን ጨቋኙን ሊያናግረው ይሞክራል ሊያመልጠው ይሞክራል፤ ምንም ለውጥ አይፈጠርም።ለአስተማሪው ቢነግርም ምንም አያደርጉለትም።

ታድያ አንድ ቀን ከዚያ አስጨናቂ የሚገዝፍ አንድ ተማሪ ያ ትንሹ ልጅ አሳዝኖት መጥቶ፣ጨቋኙን ትንሹን ልጅ ማሰቃየት ማቆም እንዳለበት ያሳውቀዋል።ስለዚህ ይህ ትንሽ ልጅ በሰላም መሆን ይችላል። ጨቋኙ እንዳለ ሆኖ ግን ከአስጨናቂው የሚበልጥ ጠባቂ ስላለው ማረፍ ይችላል።

እኛም በህይወታችን ተመሳሳይ እርዳታን ታድለናል። እግዚአብሔር ይህንን ቫይረስ ጨምሮ ከሚያጋጥመን ከማንኛውም ችግር ይበልጣል።ልክ እንደፈጠረን ሊንከባከበን ይፈልጋል እናም ይችላል።

በዚህ ቫይረስ መሃል ሰላም

በህይወት ጭንቆች መካከል እየሱስ በፍቅር እንዲህ ይላል፤ "ሽክማችሁ የከበዳችሁ እናንተ ደካሞች ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ እኔም እረፍት እሰጣችኋለው።”2

ይህ ሰማይና ምድርን፣ከዋክብትና ጠፈርን፣በቢልዮኖችና ትሪልዮኖች የሚቆጠሩ ፍጥረቶችን እናም የሰው ልጅን የፈጠረ አምላክ ነው።”የሚሳነው አንዳች የለም"3 ።እገዛውን ፍለጋ ወደ እርሱ እንድንመጣ ይጋብዘናል።

እየሱስ ሁሌ እግዚአብሔርን በሰማይ ያለው አባታችን እንደሆነ ነው የሚገልጽልን።

መልካም አባት ሁሌም ቢሆን ልጆቹን ይጠብቃቸዋል፣የሚያስፈልጋቸውን ያዘጋጅላቸዋል፣ያስተምራቸዋል፣ይወዳቸዋል፣ ይንከባከባችዋል፣ሁሌም ያስቀድማቸዋል። ምንም ቢሆን ስለ ፍቅሩ ሊያሳውቃቸው ይፈልጋል።

ከእንደዚህ አይነት አፍቃሪ ወላጅ ወይም አባት ጋር ካላደጋችሁ ታድያ “አባት" የሚለው ቃል ብዙም ልባችሁን ላያሳርፍ ይችላል።እንደወም የአንዳንድ ሰዎች ጭንቀት የሚምጣው ወላጆቻችው ወይም አኗኗራቸው ፍርሃትንና በራስ አለመተማመንን ስለከትቧቸው ይሆናል።ምናልባት በወላጆች ወይም አሳዳጊዎቻችሁ ጉዳትን፣መረሳትንና መጣልን አይታችሁ ሊሆን ይችላል።

እንዲህ አይነት ተለምዶዎች ስለ አለም፣ስለ ራሳችንና ስለሌሎች ያለንን አመለካከት ሊያጣምም ይችላል።ነገር ግን ከእግዚአብሔር ግንኙነት ሲኖረን አዲስ ህይወትን ይሰጠናል።እንደውም እየሱስ እንደ አዲስ እንደምንወለድ ይገልጸዋል።ከእርሱ ጋር ግንኙነት ስትጀምሩ ህይወት ልዩ ናት፤አዲስ ናት።

ከኮሮናቫይረስ ፍርሃቶቻችሁ መካከል ብቻችሁን መጋፈጥና ለራሳችሁም ሆነ ለሌሎችም ለምትወዷቸው በርትታችሁ መገኘት ዋነኞች ናቸው።

ፈተናዎችን እየተጋፋችሁ ሳለ የሚመጣ ብርታት

የፈጠራችሁ እግዚአብሔር ስለእናንተ ሁሉንም ነገር ያውቃል።ታሪካችሁን፣ድሎቻችሁን፣ህልሞቻችሁን ሆነም ህልም አልባነታችሁን፣ጉዳቶቻችሁን፣የፊተኛ ህይወታችሁን፣ግንኙነታችሁንና በአጠቃላይ ሁሉንም ነገር።እየሱስ ስለ ህይወታችሁ ጥቃቅኗን ነገር እንኳን ያውቃል።"የእናንተም የራሳችሁ ጸጉር ሁሉ እንኳ የተቆጠረ ነው።”4

“እግዚአብሔር ሆይ!መረመርከኝ አወቅከኝም።አንተ የማደርገውን ሁሉ ታውቃልህ፤አሳቤን ሁሉ ከሩቅ ሆነህ ታስተውላለህ። የምሰራ ወይም የማርፍ መሆኔን ታያለህ፤ ተግባሬን ሁሉ ታውቃለህ።ገና ከመናገሬ በፊት ምን ለማለት እንደማስብ ታውቃለህ።”5

በጨለማ ውስጥ ምሪት

እግዚአብሔር መቼም ቢሆን ህይወትን ብቻችን ሆነን እንድናሳልፋት አልፈለገም። ደግሞም እግዚአብሔር በምሪቱ ልዩ ወደሆነ ህይወት ሊመራን ይፈልጋል።በጨለማ ውስጥ በአለማወቅ እየተደናቀፍን መሄድ የለብንም።

“እንደገናም ኢየሱስ "እኔ የአለም ብርሃን ነኝ፤እኔን የሚከተል ሁሉ የህይወት ብርሃን ያገኛል፤በጨለማም አይመላለስም።”6

“እርሱ ለእናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን አሳብ ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”7 ይለናል ቃሉ።ምንም የሚያጋጥመንን ነገር (ኮሮናቫይረስን ጨምሮ) ብቻችን እንድንሸከም አይጠበቅብንም።ለሚያስፈልገን ነእር ሁሉ እርሱን መጠየቅ እንችላለን እርሱም ደግሞ በፍቅሩ እና በጥበቡ እንደ አፍቃሪ አባት ጸሎታችንን ይመልስልናል። ከፈተና ሁሉ እንጠበቃለን ማለት አይደለም።አፍቃሪ አባት ከሁሉም ነገር ሽፍኖ አያኖርም።

ዋናው ነገር ግን፣ እግዚአብሔር ሊንከባከበን ይችላል እናም ፈቃደኛ ነው።

እግዚአብሔር ልቆጥር ከምችለው ጊዜአት በላይ ጸሎትን ሲመልስ አይቼዋለው እናም ጠይቄ ገና ያልተሰጡኝ ነገሮች አሉ፤ግን የወደፊት ነገራችንና ትክክለኛውን ሰአት ስለሚያውቅ እንደዚህ ብሎ ያሳስበናል፤ “እግዛብሔርን ለሚወዱና እንደፈቃዱም ለተጠሩት ሠዎች እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለጥቅማቸው እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።”8

ለከባድ ውሳኔዎች በህይወቴ ምሪት ሲያስፈልገኝ እግዚአብሔር በግልጽ ምሪትን ሰጥቶኛል።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ስቸገር ወይም ስበሳጭ፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ስፈልገው፤ቀስ ብሎ ተናግሮኝ እያረመኝ ወደ ሃሳቡ መርቶኛል። ምሪቱም ዳግም እግሮቼን በአለት ላይ አቁሞ ለልቤ ሰላምን ስጥቶታል።

የእግዚአብሔር ፍቅር ከጉድለት ስሜት አውጥቶኝ ለሰዎች በተለምዶ ካለኝ በላይ ሩህሩህነትን ሰጥቶኛል። ከእግዚአብሄር ጋር ወዳጅ መሆን ማለት እንደዚህ ነው፤ወዳጅነቱንም ለማንም በነጻ ይሰጣል። መጽሃፍ ቅዱስም እግዚአብሔርን ድንቅ መካር፣የዘለአለም አባት፣የሰላም አለቃ እናም ሁሉን ቻይ አምላክ ብሎ ይገልጸዋል፤እርሱም ደግሞ ነው።

ከጥፋት ነጻ መውጣት

በድጋሚ ማጥበቅ ምፈልገው ነገር፤ከጌታ ጋር መሆን ማለት የህይወትን ፈተና ሸወድን(ዝም ብለን እናልፋለን) ማለት አይደለም።

በህይወቴ ውስጥ አንድ ያጋጥመኝን ነገር በፍጹም መወጣት ያልቻልኩበት ጊዜ ነበር።የአራት ወር እርጉዝ ሳለሁ ጽንሱ ችግር እንዳለበት ተነገረኝ። ታድያ እኔ፣ ምንም ቢሆን እግዚአብሔርን በዚህ ነገር ማመን እችላለሁ ባዬ አሰብኩ።ነገር ግን ልጃችን ሲወለድ ሞቶ ነበር።

እግዚአብሔርን በዚህ ነገር ማመን ስለቻልኩ ምንም ባዝንም፤ ከቁጭት፣ብስጭት፣ወይም ሃዘን ጋር አልታገልኩም።
ነገር ግን አንድ ያስደነገጠኝ ነገር፣ ስለባለቤቴ መፍራት ጀመርኩኝ እርሱም እንዳይሞትብኝ ብዬ።ስለዚህ እግዚአብሔር ይህንን ፍርሃት እንዲናገረው እናም ለኔም እንዲያጋልጥልኝ ጠየቅኩት።

መልሴንም በዚህ ጥቅስ ሰጠኝ፦
“እግዚአብሔርን መሸሽጊያ ልዑልንም መጠጊያ አድርገኸዋልና ክፉ ነገር አያገኝህም መቅሰፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም።”9

እግዚአብሔር ማንም አይሞትም ብሎ ቃል አልገባም። እንደዚያ አይነት ቃልም አይገባም።ነገር ግን አግዚአብሔር የማታመነው መጠጊያዬ ስለሆነ ባለቤቴ ቢሞት እንኳ ለክፉ አንዲሆንብኝ አይፈቅድም ነበር።እግዚአብሔር ነገሩ አንዲያሸንፈኝ ወይም እንዲያጠፋኝ አይፈቅድም ነበር።

“ምንም ክፋት እንዲወድቅባችሁ አልተፈቀደም" እግዚአብሔር ለነገሮች ወሰን አስቀምጧል። እርሱን ከታመንን ከማንኛውም ሁኔታ በሰላም መውጣት እንችላልን።

ማንኛውም ችግር ኮሮናቫይረስን ጨምሮ እግዚአብሔርን አያቅተውም።

ኢየሱስ እንዲህ ሲል አጽናንቶናል “በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ነገር ግን አይⶋችሁ፤እኔ አለምን አሽንፌዋለው።”10

አሁን ያለንባት ምድር ወደ 1600 ኪሎሜትር በሰከንድ በሚሆን ፍጥነት ትሽከረከራለች። ነገር ግን ፍጹም ሳንረበሽ ይህ እሽክርክሪት ያመጣውን የጸሃይ መውጣትና መግባትን እንታደማለን።

ምድርም ጸሃይን እጅግ ታላቅ በሆነ ፍጥነት ትዞራለች።ነገር ግን በዚህ ፍጥነት አንዴም በጣም ሳትርቅም ሳትቀርብ ትሄዳለች።ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር ሙሉ የጠፍርን ቅምር ያውቀዋል እስከ ጥቃቅኗ እስከኛ ህይወት ድረስ።

ግድ የሚለው አለ

እግዚአብሔር ይወዳቹሃል፤ስለተጋባችሁ ሳይሆን ማንነቱ ፍቅርና የሚያምኑትን መንከባከብ ነው።እግዚአብሔር “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤አምላክህ ነኝና አትደንግጥ።አበረታሃለው፤እረዳሃለው፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለው።”11

“አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዝለአለም አምላክ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው። አይደክምም፤አይታክትም፤ማስትዋሉም በማንም አይመረመርም።ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ለዛለው ጉልበት ይጨምራል።ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፤ይታክታሉም፤ጎበዛዝትም ተሰናክለው ይወድቃሉ።እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ሃይላቸውን ያድሳሉ፤እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ይሮጣሉ፤አይታክቱም፤ይሄዳሉ፤አይደክሙም።”12

"ሰላምን እተውላችኋለው፤ሰላሜን እሰጣችኋለው፤እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም።ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፈራም።”13 ብⶀል እየሱስ። ከሚገጥመን ማንኛውም ችግር ይበልጣል።

ስለ ኮሮናቫይረስ(ኮቪድ-19) ወይም ሌላ ምንም ከባድ ነገር ከመጨነቅ ነጻ የሚያወጣው፤እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደሆነና ስለናንተ ግድ እንደሚለውና እንደሚሰራ ማወቅ ነው።

እግዚአብሔርን ማወቅና ከእርሱ ጋር ግንኙንት መጀመር ከፈለጋችሁ ይህንን ጽሁፍ አንብቡ፦ እግዚአብሔርን በግል ማወቅ

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) ምዝሙር 46፡1 (2) ማትዮስ 11፡28 (3) ኤርሚያስ 32፡17 (4) ሉቃስ 32፡17 (5) መዝሙር 139፡1-4 (6) ዮሃንስ 8፡12 (7) 1 ጴጥሮስ 5፡7 (8) አልተጻፈም (9) መዝሙር 91፡9-10 (10) ዮሃንስ 16፡33 (11) ኢሳያስ 41፡10 (12) ኢሳያስ 40፡28-31 (13) ዮሃንስ 14፡27


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More