×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
FAQ

መንግስተ ሰማይ ምን ተመስላለች? ለመሆኑ አለች እንዴ?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ጥያቄ. « ለመሆኑ መንግሥተ ሰማይ አለችን? » መንግሥተ ሰማይ ምን ትመስላለች? የትስ ትገኛለች? የሞቱትን ቤተሰቦቼንና ወዳጆቼን እዚያ አገኛቸዋለሁ?

የኛ መልስ፡  አዎ መንግሥተ ሰማይ አለች።

ብዙ ሰዎች መንግሥተ ሰማይ ብለው የሚጠሯት ዘላለማዊዋን ከተማ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ «አዲሲቷ ኢየሩሳሌም»1 ብሎ የሚጠራት ማለት ነው። ዘላለማዊቷ ከተማ የተገለጸችው እንዲህ ተብላ ነው።

« እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል። እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ። እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል። እንባዎችንም ሁሉ ከአይኖቻቸው ያብሳል። ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም ፥ ኃዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርአት አልፎአልና። ብሎ ሲናገር ሰማሁ። በዙፋንም የተቀመጠው ፡- እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ፤ ለእኔም እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ ። »2

አዲሲቷ ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ዘላለማዊ መኖሪያ ነች። ስለዚህች ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል።

« ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈው በቀር ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኲሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደእርስዋ ከቶ አይገባም። »3

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን የሞቱት ሁሉ የማይሞት አካል ለብሰው ይነሳሉ፤ ከዚያም በኢየሱስ ክርስቶስ ዙፋን ፊት ለፍርድ ይቀርባሉ።4 ምንም እንኳ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሞ አዳኝ ሆኖ ወደ ምድር የመጣ ቢሆንም በዚህ ጊዜ ግን ፈራጅ ሆኖ በፍርድ ወንበር ላይ ይቀመጣል። ሥማቸው በሕይወት መዝገብ ላይ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ።5

ሁሉም ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባል ፣ በዚያም ዘመዶቹንና ወዳጆቹን ያገኛል የሚል ሃሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ኢየሱስ በርሱ የሚያምኑ ብቻ የዘላለም ሕይወት እንዳለቸው ነው የሚገልጸው። ምክንያቱም በዮሐ. 14፥6 ላይ እንደተጻፈው ጌታ ኢየሱስ « በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። » ብሎ ተናግሯል። በራዕይ 7፥9 ላይ ደግሞ መንግሥተ ሰማይ ከዘር ፥ከነገድ፥ ከቋንቋ ፥ ከብሔራት የተሰበሰቡ ሕዝቦች በክርስቶስ በማመናቸው የተነሳ የዘላለም ሕይወትን አግኝተው በዚያ እንደሚኖሩ ያስገነዝበናል። ስለዚህ ዛሬ ሊቀበሉትና የእርሱን የደህንነት መንገድ ለመከተል ያልፈለጉ ሁሉ በዛ ከእግዚአብሔር ጋር አይኖሩም።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) ራዕይ 21፥2 (2) ራዕይ 21፥ 3-5 (3) ራዕይ 21፥27 (4) ራዕይ 20፥ 11-13 (5) ራዕይ20፥ 14-15


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More