×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
እግዚአብሔርን ማወቅ

ሕይወቴ በምሽት ክበብ ውስጥ አበቃ

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በካማል ኬ.

ሕይወቴ በምሽት ክበብ ውስጥ አበቃ። ነገር ግን መጀመሪያ ወደ ሆነው ልመለስ።

የምንኖረው በመካከለኛው ምስራቅ ሀገር ነበር፤ ሙስሊም ሆኜ ነበር ያደኩት። እናቴ በቤተሰባችን ውስጥ የመጀመሪያዋ ክርስቲያን ነበረች፥ እናም ትልቅ ችግር ፈጠረ። ሃይማኖቷ ስለቀየረች አባቷ ሊገድላት አስፈራራት።

ልትጠመቅ መሆኑን በማስረዳት በኢየሱስ ላይ ስላላት እምነት ለአባቷ ነገረችው። ወዲያውም “ያንን ካደረግሽ በዚያው በተጠመቅሽበት ስፍራ እቀብርሻለሁ” አላት።

እርሷም “በአንተ ላይ ምንም አላደርግም፣ ግን እግዚአብሔር አንድ ነገር እንደሚያደርግ አውቃለሁ።” ብላ መለሰች።

በዚያ ምሽት በቤተክርስቲያን ውስጥ በአምልኮ ስብሰባ ውስጥ ነበረች። በስውር አባቷ ያንን ፓስተር ለመጉዳት እቅድ ይዞ ወደዚያ ቤተክርስቲያን መጣ።

አባቷ ከቤተክርስቲያኑ በር አጠገብ በመጠበቅ ላይ እያለ እነዚህ እብዶች የሚናገሩትን መስማት ጀመረ። እናም ሲያዳምጥ እግዚአብሔር ልቡን ነካው።

ከስብሰባው በኋላ ወደ እርሷ ቀረበና “መቼ ነው የምትጠመቂው?” ሲል ጠየቃት።

እርሷም ነገረችው። እርሱም “እሺ፣ ስሜንም አስገቢው” አላት። እናቴ እና አያቴ በተመሳሳይ ቀን ተጠመቁ።

ሁሉም ወንድሞቼ እና እህቴ በክርስቶስ ወደ ማመን መጡ። በቤተሰቤ ውስጥ ጥቁር በግ ሆንኩ። “ለምን ክርስትና ትክክል ሆነ?” እያልኩ ራሴን በመጠየቅ በጣም ተጠራጣሪ ነበርኩ።

ሁለት ነገሮችን እፈልግ ነበር። ደስታን እፈልግ ነበር። እናም እውነታው የት እንደሆነ ለማወቅ እፈልግ ነበር። በክርስትና ውስጥ ነው፣ በእስልምና ውስጥ ነው ወይስ በሌሎች ሃይማኖቶች?

በመጀመሪያ እስልምናን የበለጠ በጥልቀት እና በታማኝነት ለመለማመድ ወሰንኩ። ይህንን ከሦስት ዓመት በላይ አደረግኩ። ሁሉንም ጸሎቶች፣ ሁሉንም መስፈርቶች።

አሁንም የምፈልገውን ነገር አላገኘሁም ነበር፥ ስለዚህም አንዳንድ ጓደኞቼ አደንዛዥ ዕፅ መውሰድ አስተማሩኝ።

የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኛ ሆንኩ እናም የተወሰነ ደስታ አገኘሁ። ግን አሁንም ትግል ላይ ነበርኩ። ስለዚህ መጠጣት ጀመርኩ። ግን ውስጣዊው ግጭት፣ ንዴት፣ ባዶነት አልተወኝም። አሁንም ምንም ደስታ አልነበረኝ። በሕይወቴ ምንም የተለወጠ ነገር አልነበረም።

እናቴ ስለ እኔ እንደምትጸልይ አውቅ ነበር። አያቴም ስለ እኔ ትጸልይ ነበር። አያቴ ብዙ ጊዜ ትነግረኝ ነበር፣ “ልጄ … ክርስቲያን ከመሆንህ በፊት አልሞትም። ከዚያ እሞታለሁ።”

“እባክህን ክርስቶስን ተቀበል፤ ጌታዬን ናፈቀኝ። ወደ ቤት መሄድ እፈልጋለሁ። ወደ ቤት መሄድ እፈልጋለሁ።" ትለኝ ነበር።

ነገር ግን እውነቱን በክርስትናም ሆነ በእስልምና አላገኘሁም።

እኔ ሙዚቀኛ ነኝ እና ሙዚቃን እወዳለሁ። አንድ ቀን አንድ ጓደኛዬ ወደ ዮርዳኖስ ወደ ትልቁ የምሽት ክበብ ወስዶኝ “እዚህ በሕይወትህን ትደሰታለህ” አለኝ። እዚያ ስሄድ “ዋው ... ይህ ገነት ነው ... ይህ ሰማይ ነው ... ይህ ሰማይ ነው” ብዬ አሰብኩ።

እዚያ በሙዚቀኛነት ለብዙ ዓመታት ሠራሁ። እናም ትልቅ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች እንኳን ደስተኛ እንዳልሆኑ የበለጠ እየገነዘብኩ መጣሁ።

ስለዚህ አሁን ምን ማድረግ አለብኝ? በሕይወቴ ውስጥ በጣም እየታገልኩ ነበር። ደስታ የለኝም። ብዙ ገንዘብ አገኝ ነበር፣ ግን ገንዘብ አይረዳኝም። ክርስትና አይደለም። እስልምናም አይደለም።

ምን ላድርግ? ብቸኛው ምርጫዬ ራሴን ማጥፋት ነው። ስለዚህ ሶስት ጊዜ ራሴን ለመግደል እና ይህን ህይወት ለማብቃት ሞከርኩ።

አንድ ቀን በደንብ የማውቀው አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ “ካማል አንተ ብትሞት እና እኔም ብሞት የት እንሄዳለን ብለው ታስባለህ? አንተ ወዴት ትሄዳለህ?"

በየቀኑ ይጠይቀኝ ነበር። አሰልቺ ነበር። በፊት “ለምን ትጠይቀኛለህ?” እለው ነበር።

በእውነቱ ግን ጥያቄው ጥሩ ነበር እና አስፈራኝ። ስለዚህ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። እዚያም እያለሁ “አምላኬ ሆይ! የናፈቀኝ ይህ ነው። የናፈቀኝ ይህ ነው። ሰዎች ደስተኞች ናቸው፣ እኔ ግን አይደለሁም። ምንም የላቸውም፣ እኔ ሁሉም ነገር አለኝ ግን ደስተኛ አይደለሁም።” አልኩ።

በዚያ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ሰው ኢየሱስ “አለብ ያልህ ብቻ እንጂ ትኵስ ወይም ቀዝቃዛ ስላልሆንህ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው።” ያለውን ከመጽሐፍ ቅዱስ አነበበ። ያ ደግሞ እኔ ነኝ። እኔ እንደዚህ አይነት ሰው ነበርኩ፣ በሁለቱም መካከል እየታገልኩ፣ ምናልባት በኢየሱስ ማመን ወይም አለማመን።

ከአፉ ሊተፋኝ መሆኑን በሰማሁ ጊዜ ቃል በቃል ወስጄ ኢየሱስ እንደማይቀበለኝ ተሰማኝ። ከዚያ ቦታ ወጣሁና “ከእግዚአብሔር ወዴት ማምለጥ እችላለሁ? ወዴት እሸሻለሁ?” ብዬ አሰብኩ።

ታውቃላችሁ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር። ሌላ መፍትሔዎች የሉኝም።

በዚያ ምሽት ወደ ምሽት ክበቡ ስሄድ አንድ ነገር ሆነ። አንድ ሰው ወንድሜ ራምዚ በሞተር ብስክሌቱ ላይ እንዳለ በአደጋ እንደሞተ የሚገልጽ ጽሁፍ ሰጠኝ።

“እኔ ብሞተ እና አንተም ብትሞት ...” ብሎ ያንን ጥያቄ የጠየቀኝ እርሱ ነበር እናም ዛሬ ብሞት ወደ ገሃነም እንደምሄድ ያንን ምሽት አውቅ ነበር።

ያደረግኩት ይህንን ነበር። በምሽት ክበብ ውስጥ እያለሁ እንዲህ አልኩ፣ “እሺ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንድ ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነኝ። ከአፍህ አውጥተህ ተፍተኸኛል? እርግጠኛ አይደለሁም። የምትቀበለኝ ከሆነ በሕይወቴ ሙሉ አገለግልሃለሁ። ኃጢአተኛ ነህ ካልከኝ፥ አዎ እውነት ነው። ከዚያ በላይ እፈልግሃለሁ።”

እናም በዚያን ጊዜ ማስረዳት የማልችለው አንድ ነገር በእኔ ላይ ሆነ። አሁን ግን ማስረዳት እችላለሁ…

መንፈስ ቅዱስ ሰውነቴን፣ ልቤን ሞላው። ሰዎች በዚያ የምሽት ክበብ ውስጥ ሲጨፍሩ እኔ ደግሞ ጠረጴዛዬ አጠገብ እጨፍር ነበር። ሰዎች እብድ ነው ብለው ያስቡ ነበር። ኢየሱስ ስለተቀበለኝ በጣም ተደንቄ ነበር።

በዚያው ምሽት ከምሽቱ ክበብ ለቀቅሁ እናም “በመጀመሪያ ለማን እነግራለሁ?” አልኩ።

ከዚያ የምሽት ክበብ ስወጣ ጥዋት 1 ሰዓት ሲሆን ወደ ቤቴ ስገባ በጣም በደምብ ማየት የማትችለው በሰማኒያዎቹ እድሜ ላይ የነበረችው አያቴ በክፍሉ ውስጥ ተቀምጣ ነበር። ስገባ ባየችኝ ጊዜ “ና ልጄ። ና ልጄ፣ ና እዚህ ተቀመጥ” አለችኝ። “ለምን?” አልኩ። እርሷም “ና እዚህ ተቀመጥ” አለችኝ። “ምን ትፈልጊያለሽ?” አልኩ። እርሷም “ክርስቲያን ሆነሃል” አለችኝ።

እኔም “ኦ አምላኬ! አንዴት አወክሽ?" አልኳት። እርሷም “ስትገባ በፊትህ ላይ አየሁት” አለችኝ። እኔም “አዎ አደረግኩት” አልኳት። እቅፍ አድርጋኝ “አሁን ወደ ቤት መሄድ እፈልጋለሁ። አሁን ሥራዬን ጨረስኩ።” አለችኝ። እናም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሞተች፥ ወደ ቤቷም ሄደች።

ያ የእኔን እና የእናቴን ልብ ነካ። የጠፋሁ መሆኔን እና አሁን እኔ ክርስቲያን መሆኔ ብዙ ደስታን አመጣ።

ኢየሱስ ወደ ምሽት ክለቦች እንደሚሄድ አላውቅም ነበር፣ ግን ከእርሱ ጋር የተገናኘሁት እና ሕይወቴን የሰጠሁት እዚያ ነበር። ፈጽሞ ጸጽቶኝም አያውቅም። ኢየሱስ “እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ”1 ሲል እውነቱን እየተናገረ ነበር።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) ዮሐንስ 10:10


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More