×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የእግዚአብሔር ህልዉና

የእግዚአብሔርን መኖር ለማረጋገጥ ትችላለህ?

ፈላስፋዎችና የእግዚአብሔርን መኖር/ሕልውና የሚክዱ ሰዎች የሚወዱት ጥያቄ

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በጂሪጆሪ(Gregory E. ganssle, Ph.D.)

ኢማኑኤል ካንት የእውነት ምክንያታዊ ትችት(Critique of Pure Reason) የሚለውን መጽሐፍ ከጻፈ ወዲህ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን መኖር አሳማኝ በሆነ መንገድ ማረጋገጥ እንደማይቻል መግለጻቸው የተለመደ ነው፡፡ ይህ ማስረጃ የማይገኝለት አቋም(dogma) የምሁራን ባሕል እየሆነ ነው፡፡ ይህን ማወቅ የቻልሁት በዚህ ጉዳይ ዙርያ ሐሳቦችን ሳነሳ ከሰዎች በማገኘው ምላሽ ነው፡፡ አንድ ሰው “የእግዚአብሔርን መኖር በአመንክዩ ለማረጋገጥ አትችልም” ሲል “እንዴት ታውቃለህ? እኔን አሁን ነው ያገኘኸኝ! ምን ማድረግ እንደምችል እንዴት ታውቃለህ? ብዬ እጠይቀዋለሁ፡፡

አብዛኛው ሕዝብ ይህን ዓይነት አቋም ይዞ ሲቀርብ ምን ማለቱ ነው? ብዙዎቹ በፍልስፍና የተደገፈ ስለ እግዚአብሔር መኖር ለሁሉም አሳማኝ የመከራከሪያ ነጥቦች ማቅረብ አለመቻሌን ለመጠቆም ይፈልጋሉ፡፡ በስፋት የሚነገረው አሳማኝ ምክንያት ወይም ክርክር ማቅረብ እንደማይቻል ነው፡፡ ግትር አቋም ያለው ከሀዲ ወይም በእግዚአብሔር መኖር የማያምነውን ሰው ካላሳመንሁ ስለ እግዚአብሔር መኖር ማረጋገጫ እንዳልሰጠሁ ይናገራሉ፡፡ የማቀርብላቸውም ሃሳቦች ፋይዳ እንደሌላቸው ይቆጥራሉ፡፡

ሁሉንም ፈላስፋ ማሳመን የሚችል ሀሳብ ማቅረብ እንደማልችል አውቃለሁ፡፡ ታድያ ይህንን አለማድረጌ ከእግዚአብሔር መኖርና አለመኖር ጋር ይያዛል? በጭራሽ፡፡ ይልቅ የሚነግረኝ ስለ ማስረጃው ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር መኖር ሁሉም ሰው ሳይጠራጠር መቀበል የሚችለው ማስረጃ ማቅረብ አልችልም፡፡ በእርግጥ አንድ የፍልስፍና ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ምንም አይነት ማስረጃ ለምንም ነገር ማቅረብ አይቻለኝም፡፡

በእርግጥ በፍጹም በማያወላዳ ሁኔታ ፈላስፋዎችን ሮኪ ማውንቴንሰ (Rocky mountains) አዕምሮ የፈጠራቸው ነገሮች ሳይሆኑ በውን ያለ እነደሆኑ ማስረዳት አልችልም፡፡ ጠፈርና ሥነ-ፍጥረት (universe) ውስጥ ያሉ ሁሉ ከአምስት ደቂቃዎች በፊት ብቅ እንዳላሉ የእኛም ትውስታ ቅዠት እንዳልሆነ በማስረጃ ለማረጋገጥ አልችልም፡፡ በዩንቨርስቲ ግቢ ያሉ ሰዎች አእምሮ እንዳላቸው ማረጋገጫ ላቀርብ አልችልም፡፡ ምናልባትም ቀልጣፋ ሮቦቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

በፍልስፍና ያለምንም ጥርጣሬ ድምዳሜ ላይ የሚያስደርስ ምንም ነገር የለም፡፡ እንዲሁ በሂሳብ ስሌት ማስረጃ ማቅረብ አለመቻል የእግዚአብሔርን ሕልውና በተመለከተ የሚያቀርቡትን የመከራከሪያ ነጥቦች አያዳክምም፡፡ የእግዚአብሔር ሕልውና ጥያቄ ቀደም ብዬ ስለ ጠፈር፡ ስለ ባለአእምሮ ሰዎች እነደጠየቀኩዋቸዉ ጥያቀዎች መታየት ይችላል፡፡

ታዲያ ይህ ማለት ስለ እግዚአብሔር ሕልውና የሚነሱትን ክርክሮች ፋይዳ ቢስ ያደርጋቸዋል? ፈጽሞ አያደርጋቸውም፡፡ ሌሎችን የሚያሳምን ምክንያት አለማቅረብ ማለት ለራሴ በእግዚአብሔር ለማመኔ ምክንያት የሉኝም ማለት አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ያሳመኑኝ ምክንያቶች በአንተም ላይ ግፊት ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ በእግዚአብሔር መኖር ባታምንም ያንተ እምነት ወይም አቋም የኔን ምክንያቶች ፋይዳ ቢስ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ተራሮች እውን መሆናቸውን፣ ትውስታ፣ ባለአእምሮ የሆኑ ፍጡራን መኖራቸውን መቀበል ምክንያታዊነት ነው፡፡ በማስረጃ ባናረጋግጥም መኖራቸውን መቀበሉ አንድ ነገር ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሕልውና የሚቀርቡ ምክንያቶች ምናልባት ያሳምኑህና በእግዚአብሔር ማመን ትክክል መሆኑን ትቀበል ይሆናል፡፡

ለመሆኑ ስለ እግኢአብሔር መኖር እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሚበጀው ምንም የማያጠራጥር ማረጋገጫ ከመፈለግ ያሉትን ማስረጃዎች ከአማራጮች ጋር ማስተያየት ነው፡፡ የትኛው አማራጭ ነው የሚሻላው ብሎ መወሰን ይበጃል፡፡

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More