×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
እግዚአብሔርን ማወቅ

በኢየሱስና በሌሎች ኃይማኖቶች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌሎች በዓለም ያሉ ኃይማኖቶች ጋር ያለውን ልዩነት የሚያሳይ አጭር መግለጫ

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በቅድሚያ ከሌሎች በዓለም ላይ ካሉ ኃይማኖቶች ተለይቶ በማንጸባረቅ ልዩ የሚያደርገውን የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ዋና ዋና የሚባሉ የእርሱን ባሕርይዎቹን አጠር አድርገን እንመልከት ።

1. ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ግንኙነት ለመመስረት በፈቃዱ ይጠብቀናል።

በራሳችሁ ፍቃድና ፍላጎት ተነሳስታችሁ ከአንድ ሰው ጋር ግንኙነት ለመመስረት ጥረት አድርጋችሁ ታውቃላችሁ? እጀግ አድካሚና ዘላቂነት የሌለው ነው። ውድ ጓደኘነት ግንኙነታቸውን በሁለቱም ወገን በኩል ፈልገውና ተሳስበው የተቀራረቡ እንደዚሁም ያንን ግንኙነት እኩል ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን ሰውተው የመሰረቱት ነው። በሌሎች ኃይማኖት ግን አምላካቸውን ለማግኘት ሰዎች ናቸው ጥረት የሚያደርጉት ፤ ኢየሱስን ስንመለከት ግን እርሱ ነው እኛን ለማግኘት እስከመጨረሻ ጥረት ሲያደርግ የሚታየው። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ለምን እንደመጣ የገለጸው እንዲህ በማለት ነው፤- « እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲሁም እንዲበዛላችሁ መጣሁ ።» በማለት ነው የገለጸው። እርሱ የመጣው ለሚያምኑ ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወትን ሊያጎናጽፋቸው ነው።

2. ኢየሱስ ራሱን እግዚአብብሔር አምላክ እንደሆነ ገልጿል።

ማንኛውም በዚህ ምድር ላይ ያለን ኃይማኖት የመሰረቱ ሰዎች ራሳቸውን አምላክ አድርገው አልተናገሩም። የበለጠ ይህን ለማወቅ ይህን ሊንክ ይክፈቱ ኢየሱስ እርሱ አምላክ እንደሆነ ተናግሯልን?

3. ኢየሱስ ፍፁም ሕይወትን በመኖር ነው ያለፈው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም የሆነ ሕይወትን ከመኖሩም በላይ፣ በሰራቸው ተዓምራትና ድንቆች መለኮትነቱን አሳይቷል። ዕውራንን አብርቷል፤ ኃይለኛ የባህር ማዕበልን ጸጥ አሰኝቷል፤ የሞቱ ሰዎችን አስነስቷል፤ በተዓምር ትንሽ ምግብን አትረፍርፎ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን መግቧል፤ በምድር ላይ ያሉ ሌሎች ኃይማኖቶች ደስ የሚያሰኝ መልዕክት በማስተላለፍ ተከታዮችን አፍርተው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እንደ ጌታ ኢየሱስ ተዓምራትንና ድንቆችን አላሳዩም። ኢየሱስም እንዲህ አለ ፡- « እናንተን በእኔ እመኑ ስል አብ በእኔ ውስጥ ስላለ እኔም በአብ ውስጥ ስለምገኘ ነው። እኔን ባታምኑ ለምን ሥራዬን አታምኑም?» በማለት ነው ለሰዎች የተናገረው። ተዓምራቱና ድንቆቹ ማንነቱንና መለኮትነቱን በሚገባ ያሳያሉ።

4. ኢየሱስ ክርሰቶስ ይቅርታን ሰጠን፤

በምድር ላይ በሚገኙ ብዙዎቹ ኃይማኖቶች ለኃጢዓታቸው ሥርየት ለማግኘት እራሳቸውን በከባድ ሥቃይና ጭንቀት ውስጥ ያሳልፋሉ። ራሳቸውን ይገርፋሉ፤ በእሳት ፍም ውስጥ ያልፋሉ፤ በምስማር ራሳቸውን ይቸነክራሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እንደ አምላክነቱ የእኛን ኃጢዓት ዋጋ በራሱ ሞት ስለከፈለ እንደገና እርሱ እንደ አምላክነቱ እኛን ይቅር አለን። « የእግዚአብሔር የራሱ ፍቅር በእኛ ተገለጠ ፤ ኃጢዓተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለእኛ ሞተልን ። » ክርስቶስ ኢየሱስ እኛን ለማዳን ኃጢዓታችንን ሁሉ ተሸክሞ በመስቀል ላይ በመሞት ቅጣታችንን ከፈለልን።

5. ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከሞተና ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ።

ብዙ ኃይማኖቶች ስለ ዳግም መነሳት ያስተምራሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በምድር ላይ በመመላለሰ ሲያስተምር ሳለ ደጋግሞ እርሱ በመስቀል ሞት እንደሚሞትና ከዛም በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሳ ደጋግሞ ተናግሮ ነበር። ጌታ ኢየሱስ የርሱን መለኮትነት ከጥርጥር ባለፈ በተጨባጭ ዓለም ሁሉ እንዲያውቅ ፈልጓል። በዘመኑ ዓለምን ሲገዙ የነበሩት የሮማውያን ባለሥልጣናት ይህንን መልዕክቱን ደጋግመው ሰምተው ስለነበር ፥ ጌታ ኢየሱስ ሞቶ ከተቀበረ በኋላ መቃብሩን እንዲጠብቁ ከአሥራ አንድ እስከ አሥራ አራት የሚሆኑ ወታደሮች መቃብሩን እንዲጠብቁ ተደርጎ ነበር። ማንም ሰው ወደ መቃብሩ እንዳይቀርብ የሚያስጠነቅቅ የሮማውያን ማህተም ተደርጎበት ነበር። ይህ ሁሉ ጥንቃቄ ቢደረግም ጌታ ኢየሱስ ግን እርሱ እንዳለው በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። ከዚያም ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ሰዎች በይፋ ታየ። በምድር ላይ ያሉት ሁሉም ኃይማኖቶች መሪዎቻቸው አንዳቸውም በአካል ሞተው እንደሚነሱ አስቀድመው አልተናገሩም አልተነሱምም። ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

6. የመጽሐፍ ቅዱስ መልዕክት እጅግ በጣም ልዩ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ሃሳባቸው የማይገጣጠሙ ተራ የግጥምና የልብ ወለድ ታሪኮች መድበል አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለአኛ ሕይወት ያቀደውን የደህንነት ዕቅድ የተገለጸበትና እንዴት እንደተፈጸመ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው። የእኛና የእግዚአብሔር መልካም የነበረው ግንኙነት እንዴት እንደተበላሸ እንዴት እንደሆነ በሚገባ የሚተርክልን መጽሐፍ ነው። እንደዚሁም ይህ ተበላሽቶ የነበረው ግንኙነት እንዴት እንደሚታደስ በሚገባ ያሳውቀናል። ስለዚህ ጉዳይ በበለጠ ለማወቅ ከፈለጋችሁ ፥ እግዚአብሔርን በግል ማወቅ የሚለውን ጽሑፍ እንድታነብቡ እንመክራችኋን።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More