×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
ወሲብ እና የፍቅር ግንኙነት

የወሲብ ህግ ማን ያውጣልን?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ጥያቄ፡ «ስለተለያዩ ወሲባዊ ተሳትፎዎች እግዚአብሔር አምላክ የሚለው ነገር ምንድነው? ወሲብን በተመለከተ እግዚአብሔር ያስቀመጠው የሞራል እሴቶች ምንድናቸው? »

የኛ መልስ፡  ብዙ ሰዎች ዛሬ ወሲባዊ ተሳትፎአቸውን እያንዳንዱ ሰው በራሱ በሚያወጣው ምደባና እሴት መሠረት መፈጸም ይችላል ብለው ይወስናሉ። በእርግጥም ይህ ውሳኔ አግባብ ይመስላል ምክንያቱም ወሲብ እያንዳንዱ ግለሰብ የግሉ ኃላፊነት ስለሆነ በግሉ ሊወስንበት የሚገባው ጉዳይ ነው። በሌላ በኩል ስንለመለከተው ወሲብ የሁለት ሰዎች ተሳትፎን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ እንደ ግለሰብ ውሳኔ በግል ብቻ ደረጃ ሊወጣለት ይገባል የሚለው አካሄድ ደግሞ ብዙ አያስኬድም፤ ያስኬዳል እንዴ?

አንዳንዶች የምትወደው ወይንም የሚወዳት ከሆነ ወሲብ ምንም ችግር የለበትም፤ ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ወሲብ መልካም የሚሆነው ሁለቱም እንዳቸው ለአንዳቸው ራሳቸውን ሰጥተው በፍቅር ሲከውኑት ነው ይላሉ።ብዙዎች ግን ከጫወታና ከመዝናኛነት ባለፈ ወሲብ ፍቅርም መሰጠትም አያስፈልገውም ይላሉ።

በጣም የሚገርመው ግን በወሲብ ጉዳይ ማንም ቢሆን መመርያ ማውጣት የለበትም ፤ከማንም ሰው ወሲብ መፈጸም ምንም ችግር የለበትም ፤ የሚሉ ወገኖች ደግሞ ቁጥራቸው አየበረከተ መምጣቱ ነው።

እናንተስ ምን ታስባላችሁ? ለመሆኑ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሲከሰቱ ፣ ወሲብ ምንም ችግር የለውም ብላችሁ ታስባላችሁ።

  • በመጀመሪያው ቀን ትውውቅ ወሲብ ቢፈጸም ትክልል ነው ? አዎ አይደለም
  • ከአራት ወር ትውውቅ በኋላስ ? አዎ አይደለም
  • ከተመሳሳይ ጾታ ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • በቡድን ሆኖ ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከአባትና ከእናት ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከሰከረ ወይም በዕፅ ከደነዘዘ ሰው ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ካለበት ሰው ጋር ግን ሳይነግራችሁ ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • የኤይድስ በሽታ ካለበት ሰው ጋር ግን ሳይነግራችሁ ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከእህት ወይም ከወንድም ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከአሥራ አምስት አመት ልጅ ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ካገባ ሰው ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ካገባ ሰው ጋር ግን ለመፋታት በዕቅድ ላይ ካለ ሰው ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከሦስት ዓመት ሕጻን ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከፈቃዱና ከፍላጎቱ ወይም ከፈቃዷና ከፍላጎቷ ውጭ ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ያገባ ሰው ካላገባ ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም
  • ከአስከሬን ጋር ወሲብ መፈጸም ትክክል ነው? አዎ አይደለም

ይህን መጠይቅ በሚገባ መርምረን ስንመለከተው ብዙ የሚያደናግሩ ነገሮች በውስጣችን ይፈጸማሉ። መጠይቁን ካያችሁ በኋላ ከማንም ጋር ወሲብ መፈጸም ምንም ማለት አይደለም የሚለው አመለካከት ምንያህል ትክክል ነው? ብለን መጠየቅ እንጀምራለን። ብዙዎቻችን በተከለከሉና ባልተከለከሉ መካከል አንድ መለያ መስመር ማስቀመጥ እንፈልጋለን። « እኔ የራሴ የምመዝንበት ደረጃ አለኝ። ምናልባት ሀ. ለ. እና መ. ልክ አይመስሉኝም፤ የተቀሩት ግን ችግር አለባቸው ብዬ አልገምትም፤ እንላለን።” ዕውነቱን ለመናገር ማንኛችንም ብንሆን ወሲብን በተመለከተ የራሳችን የሆነ እኛን ማዕከል ያደረገ መመዘኛ ነው ያለን። ወሲብን አስመልክቶ ያለን አቋም እኛን ሳይሆን ሌላውን ወገን ያማከለ የሆንን ስንቶች ነን?

ወሲብን አስመልክቶ እግዚአብሔር ያወጣውን ድንጋጌ ያለምንም ማቅማማት አንድንከተል የሚያስችሉን ቢያንስ ሁለት በቂ ምክንያቶች አሉ። የመጀመሪያው እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ ይጠነቀቅልናል፤ እንዲሁም ከእኛ ጋር ለሚቀናጀውም ሰው ይጠነቀቃል። ሁለተኛ የእርሱ ጥበብና ፍቅር ምንም የማይደረስበትና ጥልቅ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር የሰጠን ድንጋጌዎች ምንድናቸው?

1. ወሲብን አስመልክቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመጀመሪያው ክፍል ውስጥ ነው የተነሳው፤ አግዚአብሔር የወሲብን ስሜት ሲፈጥር በወንድና በሴት መካከል ደስታን እነዲያገኙና የአንድነታቸው መገለጫ እንዲሆን ነው። ይህንንም አንድነት የገለጸው «ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ » በማለት ነው። ይህንን በአንድ ሥጋነት የተመሰለውን አንድነታቸውን ማንም ሰው ከነርሱ ሌላ ገብቶበት አንድነታቸውን ሊያበላሽባቸው አልተፈቀደለትም።

2. ዛሬ በተግባር የዋሉት የወሲብ ልምምዶች አብዛኛዎቹን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው። ከእንስሳ ጋር የሚደረግ ወሲብ፣ በጋብቻ ቃልኪዳን ካልተሳሰሩት ሰው ጋር ወሲብን መፈጸም ፣ ትዳር ካለው ሰው ጋር ወሲብን መፈጸም ፣ እነዚህ ሁሉ የወሲብ ግንኙነቶች እግዚአብሔር ያልፈቀዳቸው ግንኙነቶች ናቸው። እግዚአብሔር ኃጢዓት ብሎ የገለጻቸው ቅድስና አልባ ወሲብን አስመልክቶ የሚደረጉትን ብቻ አይደለም። ለምሣሌ ከአስነዋሪ የፍትወት ልምምድ፣ ከርክስና፣ ከሥጋ ምኞት፣ ከክፉ ምኞት፣ ከዓይን አምሮት ከንፉግነት፣ ጣዖትን ከማምለክ፣ ከቁጣ ፣ ከጥላቻ ፣ ከውሸትና አስነዋሪ ቋንቋ ከመጠቀም . . . እንድንርቅ አዘዞናል። እግዚአብሔር ሁላችንም ኃጢዓት እንደምንሰራ ተናግሯል፤ ሆኖም የእርሱ ፍላጎት በአስነዋሪ የፍትወት ልምምድ፣ በርክስና፣ በሥጋ ምኞት፣ በክፉ ምኞት፣ በዓይን አምሮት በንፉግነት፣ ጣዖትን በማምለክ፣ በቁጣ ፣ በጥላቻ ፣ በውሸትና አስነዋሪ ቋንቋ ከመጠቀም ሕይወታችን እንዳንበላሽ ነው። በዚህ ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር እንደምትስማሙ እርግጠኛ ነኝ።

የእግዚአብሔር ፍላጎት ወደ እያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ በመምጣት ከኛ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖረው ነው። ከዚህም የተነሳ በውስጣችን ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግስትን፣ ቸርነትን፣ መልካምነትን፣ ራስን መግዛትን፣ ሊገነባ ይሻል። ከእርሱ ጋር ግንኙነትን ስንጀምር በቀጥታ እነዚህ ሁሉ ፍሬዎች በውስጣችን ማፍራት ይጀምራሉ። ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖረን አስቀድመን እኛ የፍቅር ሰዎች፣ ደስተኞች፣ ሰላም የተሞላን ፣ ትዕግስተኞችና ቸሮች ሆነን እንድንገኝ አልጠበቀም። ከዛ ይልቅ የርሱን ጥልቅ የሆነውን ፍቅር ሰጥቶን ፣ በኛ ላይ ተጽዕኖ ካሳደረ በኋላ የተቀበልነውን ፍቅር ለሌሎችም እንድናካፍል ነው የሚፈልገው። ስለዚህ ከሌሎች ጋር በመፈቃቀርና በመከባበር በሰላምና በደስታ እንድንኖር ከተፈለገ አስቀድሞ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ማድረግ ይገባናል።

ወሲብን አስመልክቶ የእግዚአብሔርን ድንጋጌዎችንና ምሪቶችን መከተል አስፈላጊ እንደሆነ ሲገልጽ አንድ ሰው እንዲህ አለ።

«አኔና ባለቤቴ ከመጋባታችን በፊት በእጮኝነት ሦስት ዓመት ወጥተናል ገብተናል፤ ሆኖም ምንም ዓይነት የወሲብ ልምምድ ውስጥ አልገባንም። በዚህ ሁሉ ጥብቅ ሥነ ሥርዐታችን ውስጥ አንድ መልካም ነገር ተለማምደናል። ይኸውም ለሃያ ዓመት የጋብቻችን ዘመን እኔም ሆነ እርሷ አንድም ቀን ከሌላ ተቃራኒ ጾታ ጋር በወሲብ አንሶላ መጋፈፍ ፈተና ውስጥ እንወድቃለን ብለን ለቅጽበት ያህል እንኳ ተጨንቀን አናውቅም። የሥራዬ ባህርይ ስለሆነ ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማለትም ወደ ማሌዥያ ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ ተዘዋውሬአለሁ አንድ ቀንም ባለቤቴ እኔን ቁባት አስቀምጦ ይሆን ወይንም በዳንስ ቤት ወይም በጭፈራ ቤት ከሴት ጋር ይኳሸማል ብላ የጠረጠረችበት ጊዜ የለም። እርስ በርሳችን ፍፁም ስለምንተማመን ለአንዲት ቅጽበት እንኳን በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ አስጨንቆን አያቅም።
ለምን ?
ምክንያቱም አግዚአብሔር እንድንሆን የጠየቀንን ነው የሆነው። በዚህም ምንም ቢሆን ጸጸት የሚባል ነገር በሕሊናችን ውስጥ የለም። »

በጣም የሚያስደንቀው ነገር እግዚአብሔር ከቶም ቢሆን እኛን በፍቅር ከመመለስ ባሻገር ጥብቅ የሆነ ሕግ በመሃከላችን አላስቀመጠም። እርሱ ይህን የሚያደርገው በአስነዋሪ ፍትወት የተነሳ ከሚመጣው አስከፊ ውጤትና በዚያም ምክንያት ከሚደርስብን አሰቃቂ የልብ ስብራት ሊጠብቀን ነው። በግብረ ሥጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ በሽታዎች፣ ካልታቀደ እርግዝና ፣ የሚመጡት ታማኝነትን ከመናድና ከአንዱ የወሲብ ጓደኛ ወሌላው በመባዘን የሚመጣ ነው። ስለዚህ ራስን ለመጠበቅ ታማኝ ሆኖ መኖርን የተሻለ እንደሆነ እግዚአብሔር ሚመክረን እንዲህ ብሎ ነው።

«ከዝሙት ሽሹ ፣ ሰው የሚያደርገው ኃጢዓት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሰራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ፣ ኃጢዓትን ይሠራል። » 1ኛ ቆሮ. 6፥18

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More