×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የህይወት ጥያቄዎች

የካምፓስ ላይፍ ቴንሽን

የኮሌጅ ውጥረት - የአን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትምህርት ላይ ስለሚያጋጥማቸው ውጥረት (ቴንሽን) እንዲህ ይላሉ፡

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

“የደም ስሮቼን በዕፅ ና በጫት ማጨናነቅን፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የፍትወተ-ሥጋ ባልንጀሮች ማስተናገድን ወይም እድሜዬ ወደ ሃምሳው ሲደርስ የነርቭ ቀውስ የሚያስከትሉብኝን ችግሮቼን አንደሌሉ ማስመሰልን ከመሳሰሉ ምርጫዎች ጋር በተፋጠጥኩበት በኔው ዓለም፣ ተስፋዎቼን ሁሉ በአንድ ከመንደር የዘለለ እውቅና በሌለው አናጢና አምላክ በሚባል እርባነ ቢስ ምስቅልቅል ላይ ማሳረፍ ትርጉም ይሰጣልን?”

የቀለሙ ጫና ደብዛዬን ሊያጠፋና ሊደፈጥጠኝ በተቃረበበት በዚህ ወቅት፣ በፊቴ የቆሙ ተራሮችን ከፊቴ ከማንከባለል ባሻገር እኔን የመፍጠር አቅም በሌለው ጣዖት ጉያ መሸጎጥ ትርጉም ይሰጣልን? ጨርሶ አላደርገውም! ማገልገልም ካለብኝ እኔ የማገለግለው አምላክ ከእንጨት የተቀረፀን ጥጃ ሳይሆን፣ የማይገደብ ኃይል ያለው፣ አምሳያ የማይገኝለት ውበት፣ ሉዓላዊ ሥልጣንና የማይነጥፍ ጸጋ ምንጭ የሆነውን ነው ከዚያ ባሻገር ግን ውድ ጊዜዬን በከንቱ ማባከን ነው፡፡

ምንም እንኳን ኢየሱስን ከሰባት ዓመቴ ጀምሮ የማውቀው ቢሆንም፣ ወኔ ቢስ፣ የማልረባና ባዶ የሓይማኖት ጀሌ መሆኔ እስካታከተኝ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እስከሆንኩበት ጊዜ ድረስ እምብዛም አልነበርኩም፡፡ እግዚአብሔር የሰዎች ትውፊት/ወግ ወይንም አስተሳሰብ ውጤት አሊያም እርባነቢስ የልማድ አምልኮ ውጤት አለመሆኑን ለመረዳት ይህንን ያህል ረጅም ጊዜ ወስዶብኛል፡፡ እርሱ ከእኛ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረን ይሻል፡፡ (እውነተኛው አምላክ ከእኛ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረው የሚፈልግ አምላክ ነው፡፡) ከትናት ዛሬም ከእርሱ ጋር የበለጠ እንድቆራኝ አድርጎኛልና ዛሬ፣ ስሙን እጅግ ከፍ አድርጌ አመሰግናለሁ ምክንያቱም በነዚህ ሁሉ ሻካራ ሁኔታዎቼ ውስጥ በድንቅ ሁኔታ እንደተሸከመኝ አይቻለሁ ፍቅሩንም አጣጥሜአለሁ ፡፡

በሁኔታችሁ በማያላግጥ፣ በማይስቅባችሁና ጀርባውን በማይሰጣችሁ ፊት ሁሉን ነገራችሁን ዝርግፍ ማድረግ ምንኛ የሚያጓጓ እፎይታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ፍፅምናን አይጠብቅም፤ እርሱ ከእኔ የሚፈልገው ኀጢአቴን እንድናዘዝና እንድታዘዘው፣ ስለ እርሱም የእውነት ምስክር ሆኜ እንድኖር ብቻ ነው፡፡

በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት መመሥረት፣ ከሁሉ ልቆ እንዲወጣ ያደረገው ምኑ ነው? እፎይታው ድነት የአድርግ አታድርግ ዝርዝር ዶሴ ወይንም የማይቀረው የዘላለም ፍርድ ወይንም ኩነኔ ማስፈራሪያ አለመሆኑ ነው፡፡ በእኔም ላይ የተጫነ አሰቃቂ ሸክም አይደለም፡፡ ኢየሱስ ያለው፡

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”

ታዲያ ይህ ሁለንተናን የሚያድስ አይደለምን? ታዲያ ይህ ነፍስን የሚያስፈነድቅ አይደለምን?

ለደካሞች ምርኩዝ? እምብዛም ችግር የለበትም፣ ችግሮቹንም ያለ አንዳች እንከን ብቻውን ይወጣቸዋል የምትሉት አንድ ሰው ካለ አሳዩኝ፤ ሸክም ያላጎበጠው፣ የማያለቅስ፣ ጭንቀትና ውጥረት ያልከበበው አንድ ሰው ካለ እስኪ አምጡልኝ እንዲህ ዓይነት ሰው ካለ… ራሱን በገና አባት የማታለያ ቀልዶች ወይንም የፋሲካ ሰሞን ተረቶች የሚሸነግል ሰው ነው፡፡ የደካሞች ምርኩዝ? ኦ አዎን!

እርካታ የሞላበት ሕይወት በመጠጥ፣ በግሩም ውጤት፣ በመልካም ሥራ ወይንም በበጎ አድራጎት እንደማይገኝ አይቻለሁ፡፡ እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም መጣሁ ብሎ (ኢየሱስ) ተስፋን ሲሰጥ ምን ማለቱ እንደሆነ የገባኝ ኀጢአቴን ስናዘዝ እና ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወቴ ጌታና አዳኝ አድርጌ ስቀበል ነው፡፡ አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር ሕይወቱን ሊሰጥና ሌላውን ሰው ደስ ስለማሰኘት መጨነቅን ሊቆም የተገባ ነው፡፡ ሕመም እጅግ የምጠላው አላርጅኬ የመሆኑን ያህል፣ አንድ እምነት ሊሞትለት የሚገባ መሆኑን ራሱ ካላረጋገጠ በስተቀር እሞትለታለሁ ብዬ አልናገርም፡፡ እኔ፣ በዚህ በፕሪንስተን ኮሌጅ እንደሚገኙ እንደበርካቶች ሁሉ፣ ይህንን መሳዩን እምነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በጀመርኩት ኅብረት ውስጥ አግኝቼዋለሁ፡፡

ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ በቀኜ ነውና አልታወክም።
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች
(መዝሙር 16፥8-9)

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More