ፈላስፋው የእርሱን ህልው መሆን አስመልክቶ መነሻ የሚሆነውን ሀሳብ እንዲህ ሲል አስቀመጠ። «አሰብኩ፣ እናም ሆንኩ።» አለ("I think; therefore, I am.")። « በምናቤ አሰብኩ ማለት አይችልም። ልክ ባዘጋጀው የመነሻ ሃሳብ ላይ «እኔ» የሚለውን እንደጨመረ፣ የእኔነት ህልውና በውስጡ እንዳለ አረጋግጧል ማለት ነው።
በዚህች ምድር ላይ የአንድ ሰው የራስ ማንነት ብዙ አፈላሳፊ የሆነ መነሻ ነገር ነው። ይህ ሃሳብ ራሳችንን ከሌሎች ተለይተን እንደምንገኝና እኔነታችን ገዝቶን እንድንኖር እንደሚያደርግ በግልጽ ያሳየናል። እኛ በብዙ መንገድ ልክ አንድ ደሴት በባህር ተከብቦ ከሌሎች የብሶች ተነጥሎ እንደሚገኝ ሁሉ እኛም እንደዚያ ነን። ማንም ሰው ልክ እናንተ እንደሚሰማችሁ ስሜት ዓይነት አይሰማውም። ወይንም ልክ እናንተ የምታስቡትን ዓይነት ሃሳብ አያስብም። እነዚያ ስሜቶችም ይሁኑ ሃሳቦች የራሳችሁ ብቻ ናቸው። እነርሱ ከናንተ በማይነጠሉበት ሁኔታ የናንተው በናንተው ብቻ የሆኑ ናቸው።
እንደሰብዐዊነታችን አካል ይህ እኔነት እግዚአብሔር እጅግ በጣም ትኩረት የሚሰጠው ነገር ነው፤ የእኛን ፍቃድ። ፍቃዳችን ትክክለኛ ማንነታችንን የሚገልጸው ዋናው ክፍላችን ነው። እስቲ የህይወታችንን ክፍል እንደ ዙፋን አድርገን እንውሰድ። በውስጣችን ባለችው ትንሿ ግዛታች ውስጥ ፈቃዳችን ዙፋኑ አናት ላይተሰይሟል። ውስጣችን አንድ መረጃ ከውጭ ሲያገኝና የእኛን ውሳኔ የሚጠይቅ ሃሳብ ከሆነ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እኔነታችን ደስ ባለው መንገድ ይወስናል። ይኼ ነው እንግዲህ የተሰጠን የምርጫ ነጻነት። ውስጣችን ያለችው ዓለም የምትገዛው ፈቃዳችን ነው። ፈቃዳችን በሕይወታችን ዙፋን ላይ ተቀምጧልና። የእርሱ ምርጫ የመጨረሻ ነው።
በአንድ በሆነ አጋጣሚ ሕሊናችን ከውጭው ዓለም እግዚአብሔርን በተመለከተ መረጃን ያገኛል። እንግዲህ ስለእግዚአብሔር ያለን ዕውቀት አጀማመሩ ይህን ይመስላል ማለት ነው። ስለዚህ ሕሊናችን በሕይወታችን ዙፋን ላይ ለተቀመጠው እኔነት « ንጉሥ ሆይ ስለእግዚአብሔር ያገኘሁትን መረጃ ለእርስዎ ለውሳኔ እንዲረዳዎት እንዳቀርብልዎ ይፈቀድልኝ ይህ እግዚአብሔር የሚባለው ወደ እረሶ አለም ለመግባት ፈልጓል» በማለት ይገልጻል። በተጨማሪም ስላገኘው መረጃ ዘርዘር አድርጎ ሲያቀርብ እንዲህ በማለት ይቀጥላል። «ይህ እግዚአብሔር ምድርና ሰማይን የሚገዛ ቢሆንም ፣ የፈለገውን ማድረግና መፈጸም ቢችልም፣ እርስዎ ወድደውና በደስታ ግብዣ እስካላቀረቡለት ጊዜ ድረስ ወደርስዎ ግዛት አይገባም።”
«እንደዚሁም ምናልባት እርስዎ ግብዣ አድርገውለት የሚመጣ ከሆነ በዙፋንዎ ላይ ሆነው በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ሁሉ ተጽዕኖ የማድረግ ኃይል እንዳለው በተጨማሪ ነግሮኛል። ይህንን ስነግርዎት በጣም አዝናለሁ፣ ያገኘሁት መረጃ ይህንኑ ነው የሚያሳይ ነው። ከዚህም ሌላ ያለኝ መረጃ ይህ እግዚአብሔር በእርስዎ ልባዊ ግብዣ ወደዚህ ከመጣ የእርስዎ ግዛት የተሻለና ሰላም የሰፈነበት እንደሚሆንም አረጋግጦልኛል። ከዚህ በተረፈ እርሱ በፍቅር የተሞላና ፣ እርሱ የሚፈልገው ለእርስዎ መልካሙንና የተሻለውን ነገር መሆኑን አስገንዝቦኛል።
«የሚገርመው ነገር እርሱ ከእርስዎ የተለየ መሆኑን በሚገባ አስረድቶኛል፣ ስለአባባሌ ይቅርታ አድርጉልኝና እጅግ ፍጹምና ምሉዕ የሆነ ንጉሥ እንደሆነ ዓይነት ይመስለኛል። ስለዚህ እርስዎ ስለእግዚአብሔር ምን ያስባሉ? ወደዚህ ይገባ ዘንድ መልካምና ከልብ የሆነ ፍቃድዎን መስጠት ይችላሉ? »
እንደዚህ የሚመስል አቀራረብ በሕይወታችን ውስጥ አልተለማመድንም? እግዚአብሔር እንድንወስንና በሙሉ ፈቃድ እንድናደርገው ይፈልጋል። ያ እንግዲህ እኛን በማክበርና መብታችንንም በመጠበቅ የፈጸመውና ትህትናውን ይበልጥ የሚያንጸባርቀው ባህርዩ ነው። እርሱ የመንግሥት ግልበጣ አያደርግም። የውስጣችንን ዙፋን ከፍቃዳችን ውጭ አይገለብጥም። ከዚያ ይልቅ የልባችንን በር እያንኳኳ ለመግባት ፈቃዳችንን ይጠይቃል። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ « እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፣ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፣ ወደርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር ዕራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።» ራእይ 3፥2ዐ በማለት ትህትና የተሞላውን ጥያቄ ለእያንዳንዱ ልብ ያቀርባል።
► | ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር |
► | ጥያቄ አለኝ |