ጥያቄ፡ ትምህርተ ስላሴ ምንድነው፣ ስሉስ ቅዱስ?
መልሳችን፡ እኔና እናንተ የምንኖረው በስሉስ-መጠነ ልክ ዓለም ውስጥ ነው። ሁሉመ ቁሳዊ አካላት የተወሰነ ቁመት፣ ወርድ እና ትልቀት አለው። አንዱ ሰው ሌላውን ሊመስል ይችላል ወይንም ባሕርዩ የሌላውን ሊመስል ይችላል እንዲያውም ንግግሩም ቁርጥ የሌላውን ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ሰውየው ልክ እንደሌላው ሰው ላይሆን ይችላል። ሁለቱም የራሳቸው ማንነት ያላቸው ሰዎች ናቸው።
ሆኖም ግን እግዚአብሔር፣ በዚህ በስሉስ መጠነ ልክ ከተገደበ ፍጥረተ-ዓለም ውጪ ነው። እርሱ መንፈስ ነው። ከእኛም ይልቅ ድንበር የለሽ በሆነ መጠን ውስብስብ ነው።
ወልድ ኢየሱስ ከአብ ልዩ ነው። ደግሞም አንድ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ እግዚአብሔር ወልድ፣ ስለ እግዚአብሔር አብ እና ስለ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይናገራል። ግን አንድ እግዚአብሔር ብቻ አለ ብሎም አፅንኦት ይሰጣል።
የሂሳብን ቀመር ብንጠቀም፣ 1+1+1=3 አይነት አይደለም። 1X1X1=3 ነው። እግዚአብሔር አሃዱ ስሉስ አምላክ ነው።
በአንድነት ሦስትነት፣ በሦስትነት አንድነት የሚገለጥ አሃዱ ስሉስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር የሚገልጥልን እንዲህ ነው። እግዚአብሔር ሦስት ስብዕና ቢኖረውም አንድ አምላክ ነው። አንዳንዶች ሰብዓዊ ተምሳሊት ሊሰጡት ይሞክራሉ። ለምሳሌ የውሃን ውሁድ H2O ይወስዱና፣ በረዶና እንፋሎት (የተለያየ ቅርፅ ቢኖራቸውም፣ ሁሉም ውሃ ናቸው)ይላሉ። ሌሎቹ ደግሞ እንቁላልን ይወስዱና ቅርፊት፣ አስኳልና ውሃውን ይወስዱና ሦስቱም አንድ እንቁላል ናቸው ይላሉ። ይህ ግን እግዚአብሔር የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ያስመስላል ጉዳዩ ግን እንደዚያ አይደለም።
እግዚአብሔር ወልድ (ኢየሱስ) ፍፁም አምላክ ነው። እግዚአብሔር አብ ፍፁም አምላክ ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ፍፁም አምላክ ነው። ሆኖም አንድ አምላክ ነው። በእኛ ዓለም፣ በእኛ ሰብዓዊ ልምምድ፣ ስላሴን መረዳት እጅግ ከባድ ነው። ሆኖም ገና ከጅማሬው እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለፀው በዚህ መንገድ ነው። በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁጥር 26 የተጠቀሱትን የብዙ ቁጥር መግለጫዎች ልብ በሉ። እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።
ምንም እንኳን ሁሉንም ያካተተ ባይሆንም፣ እግዚአብሔር በስላሴነት አንድ መሆኑን የሚገልጡ ጥቂት የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች እነሆ፡-
► | ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር |
► | ጥያቄ አለኝ |
የግርጌ ማስታወሻ: (1) ዘዳግም 6:4 (2) ኢሳይያስ 45:5 (3) 1 ቈረንቶስ 8:4 (4) ማቴዎስ 3:16-17 (5) ማቴዎስ 28:19 (6) ዮሐንስ 10:30 (7) ዮሃንስ 14:9 (8) ዮሃንስ 12:45 (9) ሮሜ 8፡9 (10) ማቴዎስ 1:20 (11) ሉቃስ 1:35 (12) ዮሃንስ 14:16-17,23