×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የእግዚአብሔር ህልዉና

እግዚአብሔር ማነው?

እግዚአብሔር ማነው? ምን ይመስላል? ስድስት የእግዚአብሔር ባሕርያት

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

1. እግዚአብሔር ማነው? ሊታወቅ ይችላል::

ታላቁንና በፈጠራ ችሎታው ተደናቂ የሆነውን የሥነ-ፍጥረት ፈጣሪ እግዚአብሔርን ልናውቀው እንችላለን፡፡ በግል እንድናውቀው ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንድንፈጥር ይጋብዘናል፡፡ ስለ እርሱ ማወቅ ብቻ ሳይሆን እርሱን ራሱን በቅርብ ልናውቀው እንችላለን፡፡

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፤ ኃያልም በኃይሉ አይመካ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ ነገር ግን የሚመካ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸው” ይላል እግዚአብሔር፡፡ (ኤር 9፡23-24)

2. እግዚአብሔር ማነው? ልንቀርበው እንችላለን::

እግዚአብሔር እንድናነጋግረውና የራሳችንን ጉዳይ እንድናወያየው ይጋብዘናል፡፡ ዝግጅትም አያስፈልግም፤ ጨዋ መሆን፤ ሥነ-መለኮታዊ አካሄድ ወይም ቅዱስ መሆን አያስፈልግም፤ እንዳለን ከነማንነታችን ስንቀርበው ፍቅር ከተላበሰ ባሕርይው የተነሳ ይቀበለናል፡፡

“እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ
በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው” (መዝ 145፡18)

3. እግዚአብሔር ማነው? ፈጣሪ ነው::

እግዚአብሔር በመናገር ማለት በቃል ብቻ ነገሮችን ወደ መኖር ያመጣቸዋል፡፡ ሕዋው ውስጥ ያሉትን የከዋክብት ክምችት(galaxy) እና ሕይወት ያላቸውን የፈጠረ እርሱ ነው፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በዚህ ዘመን ላሉት ችግሮች መፍትሔ ሊያመጣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው፤ኃይሉን እንድናውቅና በእርሱ እንድንተማመን ይፈልጋል፡፡

“ጌታችን ታላቅ ነው& ኃይሉም ታላቅ ነው
ለጥበቡም ቁጥር የለውም” (መዝ 147፡5)

“ረዳቴ ከወዴት ይምጣ
ረዳቴ ሰማይንና ምድርን ከሠራ
ከእግዚአብሐየር ዘንድ ነው”(መዝ 121፡1,2)

4. እግዚአብሔር ማነው? ይቅር ባይ ነው::

በኃጢአት እንወድቃለን፤ አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሔር መንገድ ሳይሆን በራሳችን መንገድ እንሠራለን፡፡ እግዚአብሔርም ይህን ያያል፤ ያውቃልም፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ሰዎችን በኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል፡፡ ሆኖም ከእርሱ ጋር ግንኙነት ከፈጠርንበት ጊዜ ጀምሮ ምሕረት ያደርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ ለኃጢአታችን ዕዳ ከፈለ፡፡ ከመቃብር ተነስቶ ይቅርታ/ምሕረት እያደረገልን ነው፡፡

“እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ፅድቅ ነው እርሱንም በእግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተሰረያ አድርጎ አቆመው” (ሮሜ 3፡22,25)

5. እግዚአብሔር ማነው? ታማኝ ነው::

ሃሳቡንና ስሜቱን እንደሚገልጽልህ ሰው እግዚአብሔርም ስለራሱ በግልጽ ይነግርሀል፡፡ ሁል ጊዜ እርሱ ታማኝ ነው፡፡ ከሰው የሚለየው በዚህ ነው፡፡ ስለ ራሱ ወይም ስለ እኛ የሚናገረው እውነትና አስተማማኝ ነው፡፡ እርሱ የሚናገረው ከስሜታችን ከሃሳባችንና ከግንዛቤአችን ይልቃል፤ በታማኝነቱና በትክክለኛነቱ በቃል ኪዳኑ መደገፍ እንችላለን፡፡ እርሱ የሚናገረውን የሚፈፅም አምላክ ነው፡፡ በቃሉ እንይዘዋለን፡፡

“የቃልህ ፍች ያበራል
ሕፃናትንም አስተዋይ ያደርጋል
ሕግህ ለእግሬ መብራት
ለመንገዴ ብርሃን ነው”(መዝ 119፡130,105)

6. እግዚአብሔር ማነው? ሁሉን የሚችል ነው፡፡

በሁሉም ነገር መቶ በመቶ(100%) ትክክል መሆን እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ትክክለኛ ነው፡፡ ጥበቡ ወሰን የለውም፡፡ ስለ አንድ ነገር ሁለንተናውን ያውቃል፡፡ የጀርባ ታሪኩንና የወደፊቱን ስለ አንድ ነገር መረጃ አንሰጠውም፤ ምክር አንሰጠውም፤ አንድ ነገር እንዲሰራ አናባብለውም፤ እርሱ ያደርጋል፡፡ ችሎታ ስላለው፤ ሃሳቡም ቅንና ንፁሕ ስለሆነ ፡፡ እግዚአብሔርን ካመነው አይሳሳትም፤ ደግሞም አያታልለንም፤ ሁል ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ነገር እንደሚሠራ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን እንችላለን፡፡

“አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም” (መዝ 25፡3)

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More