×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የእግዚአብሔር ህልዉና

እግዚአብሔርን ማን ፈጠረው?

እግዚአብሔር እንዴት እንደሆነ ያብራራል…

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

አንድ ነገር ወደ መኖር ከመጣ በሌላ ነገር የተፈጠረ መሆን አለበት። መጽሐፍ ደራሲ አለው። ሙዚቃ የሙዚቃ አርቲስት አለው። ድግስ አዘጋጅ አለው! የሚጀምሩ፣ ጅምር ያላቸው ነገሮች ሁሉ ለመነሻቸው ምክንያት አላቸው።

አጽናፈ ሰማይን አስቡ። ሳይንቲስቶች በአንድ ወቅት አጽናፈ ሰማይ ሁል ጊዜም ያለ መጀመሪያ ይኖር ነበር የሚለውን “የተረጋጋ ሁኔታ” ንድፈ ሐሳብን አጥብቀው ይዘው ነበር።

የኮስሞሎጂ ማስረጃ አሁን “አቢይ-ፍንዳታ” የሚባለው አጽናፈ ሰማይ የተፈጠረበት ጊዜ እንደሆነ ያስረዳል። የእኛ የቦታ-ጊዜ-ቁስ-ኃይል አጽናፈ ሰማይ የተለየ እና ነጠላ ጅምር ነበረው።

ሁል ጊዜ ስላልነበረ እና ወደ መኖር ስለመጣ (ነጠላ ጅምር ስለነበረው)፣ አንድ ሌላ እውነታ የፈጠረው ወይም ያመጣው መሆን አለበት።1

በተፈጥሮ ውስጥ የምናያቸው ነገሮች ሁሉ መጀመሪያ አላቸው። እግዚአብሔር ግን በተለየ ምድብ ውስጥ ነው፣ እናም እንደዚያ መሆን አለበት። እግዚአብሔር ከተፈጠረ ከማንኛውም ነገር ሁሌም የነበረ በመሆኑ ከፍጡራንና ከሰው ልጆች እና ከሚኖሩ ነገሮች ሁሉ የተለየ ነው። እግዚአብሔር በነገሮች ላይ ጥገኛ አይደለም፣ እርሱ ራሱን የቻለ፣ በራሱ ብቁ ነው። እናም መጽሐፍ ቅዱስም እግዚአብሔርን የሚገልጸው እና እግዚአብሔርም ራሱን የገለጠው እንደዚህ ነው። እግዚአብሔር ለምን እንዲህ ሆነ?

አጽናፈ ሰማያችን በሌላ መንገድ ሊብራራ አይችልም። ራሱን መፍጠር አይችልም። ሁልጊዜም አልነበረም። ራሱ በተፈጠረ ሌላ ነገር ሊፈጠር አይችልም። ለምን?

አጽናፈ ሰማይ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ነው ብሎ እግዚአብሔር ደግሞ በተራው በሌላ አምላክ ነው የተፈጠረው ብሎ መከራከር ወጥነት የለውም። አርስቶትል እንደተከራከረው ለሁሉም ነገር ምክንያት የሆነ እርሱ ግን ምክንያት የሌለው አካል መኖር አለበት (ወይም ሁሉን የሚያንቀሳቀስ ራሱ ግን የማይነቃነቅ አካል) መኖር አለበት ። ለምን? ምክንያቱም የማያልቅ የምክንያቶች ሰንሰለት ካለ በአጠቃላይ ሂደቱ በፍፁም ሊጀመር አይችልም።2

ስለለእግዚአብሔር ሕልውና ተጨማሪ ማስረጃ ይፈልጋሉ? ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ፡ እግዚአብሔር አለ?

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) Kenneth Richard Samples; Connections 2007; Quarter 3; www.reasons.org (2) Ibid.


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More