×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የእግዚአብሔር ህልዉና

እግዚአብሔር አለ ?

እግዚአብሔር አለ ? እግዚአብሔር በእርግጥ ስለመኖሩ ስድስት ቀጥተኛ ምክንያቶች አሉ።

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በማሪሊን አዳምሰን

ስለ እግዚአብሔር መኖር ማስረጃ የሚያሳይህን ሰው አትወድም? ያለ ጡንቻ መጠምዘዝ mመን አለብህ በሚል ትግል ሳይሆን በቀጥታ ማረጋገጫ በያሳይህ ደስ አይልህም? ከዚህ ቀጥሎ ግልፅ በሆነ መንገድ የእግዚአብሔርን መኖር የሚያረጋግጡ ምክንያቶች ቀርበዋል።

በመጀመሪያ ልብ አድርግ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር መኖር ተቃዋሚ ከሆነ ምንም አይነት ምክንያት አያሳምነውም። በጨረቃ ላይ ሰው መራመዱን ለማይቀበል ሰው ምንም አይነት ማስረጃ ይህን አስተሳሰቡን አይለውጥም። በጨረቃ ላይ የጠፈርተኞች ፎቶግራፍ፤ ከጠፈርተኞች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፤ ከጨረቃ ላይ የመጣ ድንጋይ ወዘተ ዋጋ የላቸውም። ሰውዬው ሰው ወደ ጨረቃ ሊሄድ አይችልም የሚል አቋም ስላለው።

ስለ እግዚአብሔር ህልውና አንዳንድ ሰዎች በቂ ማስረጃ እያላቸው ይህንን እውነት እንደማይቀበሉ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል።1 “በፍፁም ልባችሁ ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ”።2 ስለ እግዚአብሔር ህልውና መረጃ ከመፈለግህ በፊት እግዚአብሔር ቢኖር ላውቀው እፈልጋለሁ? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ከዚህ በኃላ የሚከተሉትን ምክንያቶች አስተውል።

1. እግዚአብሔር አለ? የምድራችን(ፕላኔት) ውስብስብነት ሆን ብሎ ነድፎ የፈጠራትና የሚያስተዳድራት ፈጣሪ መኖሩን ይጠቁማል።

ተዘርዝረው የማያልቁ የእግዚአብሔር ንድፍ ሥራዎች ቢኖሩም ጥቂቶቹን እነሆ!

ምድር መጠኗ ፍፁም ነው። የምድር ስበት እስከ 50 ማይል ድረስ በአብዛኛው በናይትሮጅንና በኦክስጅን ጋዝ የተሸፈነ ከባቢ አየር እንዲኖረን አስችሉላል። የምድር መጠን እነደ ሜርኩሪ አነስተኛ ቢሆን ኖሮ ምድር ከባቢ አየር ባልኖራት ነበር፡ እንደ ጁፒተር ምድር መጠኗ ትልቅ ቢሆን ኖሮ ከባቢ አየር ሃይድሮጂን ይሆን ነበር።3 መሬት እስካሁን ከታወቁት ፕላኔቶች ሁሉ ለተክሎች እና ለእንስሳትና ለሰው ሕይወት ተስማሚ ከባቢ አየር ያላት ብቸኛ ፕላኔት ናት።

ምድር ከፀሐይ በትክክለኛ ርቀት ላይ ትገኛለች ምድር ትንሽ ከፀሐይ ብትርቅ ሁላችንም በብርድ ባለቅን ነበር። ምድር ወደ ፀሐይ ትንሽ ብትቀርብ ኖሮ ደግሞ ሁላችንም ተቃጥለን ባለቅን ነበር። ምድር አሁን ካለችበት በክፍልፋይ(fraction) ለውጥ ብታደርግ በምድር ላይ ሕይወት አይኖርም፡ አይታሰብምም። ምድር በፀሐይ ዙሪያ በሰዓት 67,000 ማይል በምሕዋርዋ (axis) ስትሽከረከር ቦታዋን ሳትለቅና ለምድር ገጽታ(surface) ትክክለኛውን ሙቀትና ቅዝቃዜ እየሰጠች ነው።

ጨረቃ ትክክለኛ መጠን ያላትና ለስበቷ በሚስማማት ርቀት ትገኛለች። ጨረቃ የውቅያኖስ ውሃ አንድ ቦታ እንዳይተኛ ሞገድ ትፈጥራለች ግዙፍ ውሃዎች አህጉራትን እንዳያጥለቀልቁ ታደርጋለች።4

ውሃ ቀለም፣ ሽታና ጣዕም የሌለው ነገር ነው ግን ያለ ውሃ ሕይወት የለም። ተክሎች፣ እንስሳት እና ሰዎች የተሰሩት ከውሃ ነው። የሰው አካል ሁለት ሶስተኛው(2/3) ውሃ ነው።የውሃ ባሕርያት ለሕይወት ተስማሚ ነው። ውሃ የመፍያና የመርገያ ነጥቡ ባልተልመደ ሁኔታ ከፍተኛ ነው። ውሃ ሙቀቱ የሰውነት ሙቀትን በ98.6 ዲግሪ ፋራናይት በማቆየት በሚለዋወጥ የአየር ጠባይ ውስጥ እንድንኖር ያስችላል።

ውሃ ሁሉን ሊያሟሟ ይችላል፡ ይህ ባሕርይው በሺህ የሚቆጠሩት ኬሚካሎችን በማሟሟት ወደ ጥቃቅን ደም ስሮቻችን እንዲገቡ ያደርጋል።5

ውሃ በኬሚካሉ ባህሪዩ ገለልተኛ ነው(chemically neutral)። የኬሚካሎችን ማንነት ሳይለውጥ ምግቦች& መድሃኒቶች& ማዕድናት ሟምተው ሰውነታችን እንዲጠቀምባቸው ያደርጋል።

ውሃ ልዩ ባሕርይ አለው። የስበት ባህርይን በመጣስ ውሃ በተክሎች ውስጥ ሽቅብ ሊሄድ ይችላል። ለከፍተኛ ዛፎች እንኳን ሕይወት ሰጪና አልሚነት ያለው ምግብ ያቀርባል።

ውሃ የሚረጋው ከላይ ወደታች በመሆኑ የረጋው ውሃ እየተንሳፈፈ ክረምት(winter) ወራት ዓሶች በውሃ ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ።

97% የሚሆነው የምድር አካል የሚገኘው በውቅያኖስ ውስጥ ነው። የውቅያኖስን ውሃ ጨውነት በማስወገድ ንፁሕ ውሃ ለምድር በዝናብ መልክ የሚሰጥ ሥርአት(ሲስተም) አለ። ትነት ከውቅያኖስ ውሃ ጨው በማስወገድ ደመና ይፈጥራል። ደመናው በንፋስ እየተገፋ በምድር ላይ ላሉት በዝናብ መልክ ለተክሎች፣ ለእንስሳትና ለሰዎች ይደርሳል። ይህ ስርአት በቀጣይነት በአገልግሎት ላይ የዋለውን(recycle) ነገር መልሶ የመጠቀም ሥርአት ነው።6 በዚህ ሥርዓት ዘላቂነት ያለው ሕይወት በምድር ላይ ይኖራል።

የሰው ጭንቅላት/አእምሮ በአንድ ጊዜ ብዙ መረጃዎችን የማስተናገድ አስደናቂ ችሎታ አለው። አእምሮህ የምታያቸውን ቀለሞች በዙሪያህ ያለውን የአየር ሁኔታ ምድር ስትረግጥ በእግሮችህ ላይ ሚሰማህን ጫና፤ በዙሪያህ ያሉትን ድምፆች፣ የአፍህን ድርቀት፣ያስተናግዳል። አእምሮህ ስሜትህን፣ ሃሳብህን፣ ትውስታህን ሁሉ ያስተናግዳል። ይህን ሁሉ እያደረገ የሰውነትህን ሥራዎች ማለት እንደ እስትንፋስ፣ የዐይን ሽፋሽፍት እንቅስቃሴ፣ የረሃብ ስሜትና የእጆችህን እና የጡንቻዎችህን እንቅስቃሴ የመከታተል ችሎታ አለው።

የሰው አእምሮ በሰከንድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን መልዕክቶች ሊያስተናግድ ይችላል።7 ይህ የመለየትና የማጣራት ሥራ ነው። በዙሪያህ ላሉ ነገሮች ትኩረት ለመስጠት የሚያስችልህ አእምሮህ ከሌሎች ብልቶች በተለየ መንገድ ነው፡ የሚሠራው። የአመንክዩ፣ የማመዛዘን፣ የስሜት፣ የማለም፣ የማቀድ፣ከሰው ጋር ግንኙነት መፍጠርና ውሳኔ የመስጠት ችሎታ አለው።

ዓይን ሰባት ሚሊዮን ቀለማትን የመለየት ችሎታ አለው። በሚያስደንቅ ሁኔታ በአንድ ጊዜ 1.5 ሚሊዮን መልዕክቶችን ለማስተናገድ ይችላል።8 ዝግመተ-ለውጥ(evolution) በአካል ላይ በሚያተኩር የለውጥ ትንታኔ ላይ ያተኩራል። ሆኖም ዝግመተ-ለውጥ ስለ ዓይን ወይም ስለ አንጎል ጅማሮ ወይም ሕይወት የሌለው ቁስ አካል መቼ ሕይወት እንዳገኘ ሊያስረዳ አይችልም።

2. እግዚአብሔር አለ? ለሥነ ፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ የነበረው - መነሻው ምንድነው?

ይህ ስነፍጥረት(universe) በአንድ ፍንዳታ እንደተፈጠረ የሳይንስ ምሁራን ያምናሉ። ይህ ልዩ መነሻ ለሁሉም ፍጥረት መፈጠር ምክንያት ሆኖአል ይላሉ። ለጠፈር መፈጠር፣ ለጊዜ አቆጣጠር መነሻ እንኳ ይህ ፍንዳታ(Big Bang) ምክንያት እንደሆነ ጭምር ይናገራሉ።

የስነ ፈለክ ፊዚክስ ምሁር ሮበርት ጃስትሮው(Robert Jastrow) ስለ ቁስ አካል እንጂ ስለእግዚአብሔር ማወቅ አይቻልም ብሎ የሚያምነው እንዲህ ብሎአል “የስነ-ፍጥረት( universe) ዘር በመጀመሪያ ክስተት ላይ የተመሠረተ ነው። እያንዳንዱ ኮከብ፣ ፕላኔት፣ ማንኛውም ሕይወት ያለው ሁሉ የተገኘው በፍንዳታው ምክንያት ነው። በአንድ ብልጭታ ሥነ ፍጥረት ተፈጠረ። ያንን ማን እንዳደረገው ልናውቅ እንችልም።”9

በፊዚክስ የኖብል የፈጠራ ሥራ ሽልማት ተሸላሚ የሆነው ስቲቨን ወይበርግ(Steven Weinberg) እንዲህ ብሏል። “በፍንዳታው ጊዜ የሥነ ፍጥረት( universe) ሙቀት ከመቶ ሺህ ሚሊዮን ዲግሪ ነበር። ሥነ-ፍጥረት በብርሃን ተሞልቶ ነበር።”10

ሥነ-ፍጥረት ከጥንት ከጠዋቱ መነሻ መጀመርያ ነበረው። ታደያ ያስጀመረዉ ማነው? ሳይንቲስቶች ለዚህ ድንገተኛ ፍንዳታና ብርሃን በቂ ገለጻ ሊሰጡ ግን አልቻሉም።

3. እግዚአብሔር አለ? ሥነ-ፍጥረት በተመሳሳይ የተፈጥሮ ህግ ይተዳደራል። ለምን?

የመሬት ስበት(gravity) አይለወጥም በጠረጴዛ ላይ የምናቆየው ትኩስ ቡና ግን ይቀዘቅዛል እንዲሁም ምድር በ24 ሰዓት ውስጥ ትሽከረከራለች የብርሃን ፍጥነት ከምድር ወይም ከጠፈር አይለዋወጥም።

የማይለወጠውን የተፈጥሮን ሕግጋትና ሥርዓት ለምንድነው እንዲህ ለይተን የምናውቀው? ሥነ-ፍጥረት እንዲህ በስርዓት የታጀበ ለምን ይሆን?

“ታላላቅ ሳይንቲስቶች በዚህ ተደንቀዋል። በሂሳብ ስሌት የሚገዛውን ይቅርና በሕግጋት የሚመራውን ሥነ-ፍጥረት እንኳ መረዳት ያዳግታል። በምናባችን ባልተጠበቀ ሁኔታ በየጊዜው የሚለዋወጥ ሥነ-ፍጥረት ማየት ይቻላል፣ወይም ከመኖር ወዳለመኖር እንዳመቺነቱ ብቅ-ጥልቅ የሚል ሥነ-ፍጥረት።”11

በኳንተም ኤሌክትሮዳይናሚክስ(quantum electrodynamics) የኖብል ሽልማት ተሸላሚ የሆነው ሪቻርድ ፌይንማን(Richard Feynman) እንዲህ ብሏል “ተፈጥሮ ሂሳባዊ ስሌት መሆኗ ያልተፈታ ሚስጥር(mystery) ነው ሕግጋት መኖራቸው እንደ ተአምር ነው።”12

4. እግዚአብሔር አለ? ዲ.ኤን.ኤ(DNA) ለአንድ ሕዋስ መረጃ ይሰጣል፤ ባህሪውን ይመራል።

ማንኛውም ትምህርትና ስልጠና በዓላማ ይዘጋጃል። የማስተማሪያ መፅሀፍ(manual) የሚያዘጋጅ ሰው የሚያዘጋጀው በዓላማ ነው። በሰውነታችን ውስጥ በእያንዳንዱ ሕዋስ(cell) ውስጥ አነስተኛ የኮሚፒውተር ፕሮግራም የሚመስል መመሪያ መኖሩን ታውቃለህ? እነደሚታወቀዉ የኮምፒውተር ፕሮግራም በአንድና በዜሮ ነው የሚሰራው (01)። ይህ አይነት የቁጥር አቀማመጥ 11001010101000 ኮምፒውተሩ ምን መሥራት እንዳለበት ይነግረዋል። በእኛ ሕዋስ ዲ.ኤን.ኤ(DNA) ውስጥ ያለው የመረጃ ስልት(code) ተመሳሳይነት አለው። ሳይንቲስቶች በምሕጻረ ቃል በሚጠሩአቸው አራት ኬሚካሎች የተሠሩ ናቸው።እነርሱም ኤ(A)ቲ(T)ጂ(G) እና ሲ(C) ናቸው። በሰው ህዋስ ውስጥ ያላቸው አቀማመጥ CGTGTGACTCGCTCCTGAT… አይነት ነው። በእያንዳንዱ ሰው ሕዋስ (cell) ውስጥ ወደ ሦስት ቢሊዮን የሚሆኑ የፊደል ፐሮገራሞች አሉ። ህዋሱን ምን ማድረግ እንደሚገባው የሚነግሩ ማለት ነው።

ለምሳሌ የሞባይል ስልክህ ሲነካ ቢፕ የሚል ድምጽ እንዲያወጣ ማድረግ ይቻላል እንደዚሁም ሁሉ ባለሦስት ሚሊዮን ፊደል ዲ.ኤን.ኤ(DNA) መመሪያ ለሕዋሱ ይሰጣል። መመሪያው ደግሞ የተሟላ ነው።13

ይህ የሚያስደምመው ለምንድነው? ይህ የመረጃ ፕሮግራም በሰው ሕዋስ ውስጥ እንዴት ተዘረጋ? እነዚህ ተራ ኬሚካሎች ብቻ ሳይሆኑ የሰው አካል እንዴት መገንባት እንዳለበት መመሪያ የሚሰጡ ናቸው።

ይህንን የተቀነባበረ መረጃ የባዩሎጂ ሳይንስ ሊያሰረዳን አይችልም። ሆን ብሎ አንድ ሰው ካላቀነባበረው ይህን ዓይነት መመሪያ ልታገኝ አትችልም።

5. እግዚአብሔር አለ? አዎን እግዚአብሔር አለ። ምክንያቱም ይከታተለናል። ወደ እርሱ እንድንቀርብ ይፈልጋል፣ መንገድም ያዘጋጃል።

አንድ ጊዜ በእግዚአብሔር መኖር አላምንም ነበር። እንደ ማናቸውም(atheists) በእግዚአብሄር መኖር የማያምን ሰው የሰዎች በእግዚአብሔር ማመን ያስጨንቀኝ ነበር። ለምንድነው በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎች ለማስተባበያ ሥራ ይህን ያህል ጊዜና ጉልበት የሚያጠፉት? ይህን እንድናደርግ የሚያደርገን ምንድነው? በግሌ በሐዘኔታ ነበር ይህን አደርግ የነበረው። ተስፋ ቢስ በሆነው ነገር በማመን የተታለሉ ምስኪኖችን ለመርዳት ነበር ጉልበቴን አጠፋ የነበረው። እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላም ምክንያት ነበረኝ። ከአማኞች ጋር ስከራከር ወይም ስፈትናቸው ሊያሳምኑኝ ይችሉ እንደሆን የሚል ተስፋም በሃሳቤ ነበር። ጥረቴ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጉዳይ ለመላቀቅ እና የአማኞችን መሳሳት ካረጋገጥሁላቸው አጀንዳው የቀረ ይመስለኝ ነበር። እኔም በነፃነት ሕይወቴን እቀጥላለሁ ብዬ አስብ ነበር። ግን ያላስተዋልሁት አንድ ነገር ነበር። የእግዚአብሔር ጉዳይ ዘልቆ የያዘኝ ምክንያቱ አምላክ ራሱ በአጀንዳነት ከእኔ ጋር ጉዳይ በመያዙ ነው። እግዚአብሔር ሊታወቅ ይፈልጋል። የፈጠረንም እንድናውቀው ነው። በዙሪያችን ስለመኖሩ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ደርድሯል። በማያወላዳ ሁኔታ የመኖሩን ጉዳይ በፊታችን ዘርግቷአል። ከእግዚአብሔር ሕልውና ማምለጥ በማልችልበት ሁኔታ ሁሉም ነገር ተቀምጧል። ስለ እግዚአብሔር መኖር እውቅና በሰጠሁ ቀን “ይሁን በቃ አሸንፈኸኛል” አልሁት በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎች (atheists) አማኞችን ሲያዩ ያስጨንቃቸዋል። የዚህ ዋነኛ ምክንያት እግዚአብሔር ስለሚያሳድዳቸው ነው።

ይህን ደግሞ የተለማመድሁት እኔ ብቻዬን አይደለሁም። ማልኮልም ሙገርጅ(Malcolm Muggeridge) የሶሻሊስት ፍልስፍና ደራሲ “ከእኔ ፍለጋ ባሻገር የሚያሳድደኝ መኖሩን ተረድቼአለሁ።” ሲ.ኤስ.ሊዊስ(C.S. Lewis) እንዲህ አለ “ሌሊቱን ሁሉ ለሰከንድ እንኳን ከሥራዬ ፋታ ሳገኝ ልገናኘው የማልፈልገው ጨካኙ ሲቀርበኝ አየዋለሁ። እጅ ሰጠሁ እግዚአብሔር እግዚአብሔር መሆኑን አመንሁ። ተንበርክኬ ፀለይሁ፤ በዚያች ሌሊት ምናልባት በመላው እንግሊዝ ሀገር አንድ ሐዘንተኛና እልከኛ ሰው ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሰ አስባለሁ።”

በመቀጠልም እግዚአብሔርን በማወቁ ሌዊስ “በታላቅ ደስታ ተደነቅኩኝ” የሚል አንድ መጽሐፍ ጻፈ። እኔም ራሴ ስለ እግዚአብሔር መኖር እውቅና ከመስጠት በስተቀር ሌላ የምለው ነገር አልነበረኝም። በእግዚአብሔር ከተማረክሁ በኃላ በቀጣዩ ወራት ለእኔ ባለው አስደናቂ ፍቅር ተነካሁ።

6. እግዚአብሔር አለ? ከሁሉም ይልቅ የእግዚአብሔርን ለእኛ መገለጥ የምናየው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ለምን ኢየሱስ? እስቲ የዓለምን ሃይማኖቶች ተመልከቱ የቡድሃ(Buddha)፣ መሐመድ(Muhammad)፣ ኮንፊየሽያስ(Confucius) እና ሙሴ(Moses) ራሳቸውን ያስተዋወቁት በአስተማሪነት ወይም በነቢይነት ነው። ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካከለ ማንም አልነበረም። የሚደንቀው ኢየሱስ ግን አምላክነቱን በይፋ ገለጸ። ኢየሱስን ከሌሎች የሚለየው ይህ ነው። “እግዚአብሔር አለ። የምታዩትም እርሱን ነው።” አለ ስለሰማያዊ አባቱ ኢየሱስ ሲናገርም ከእርሱ በርቀት ሳይሆን ከሰው ዘር በተለየ ሁኔታ በቅርበት ነበር። ኢየሱስን “ያየው ሁሉ አባቱን አይቷል። በእርሱ ያመነም በአባቱ አምኗል” አለ።

ኢየሱስ እንዲህ አለ “እኔ የአለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም”።14 የእግዚአብሔርን ማንነት በያዘ ባህርያት ራሱንም ገለጸ ማለትም የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ማለት፣ ሰዎችን ከኃጢአት ነፃ ማውጣት፣ የተትረፈረፈ ሕይወት ብሎም በገነት ዘላለማዊ ሕይወት መስጠትን ያጠቃልላል። ሌሎች ሰዎች በትምህርታቸው ትኩረት እንዲሰጡ ሲያደርጉ ኢየሱስ ግን ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ ያደርግ ነበር። ኢየሱስም አለ “ቃሌን ተከተሉ እውነትን ታገኛላችሁ”። ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም”።15

መለኮታዊ ለመሆኑ ኢየሱስ የሰጠው ማረጋገጫ ምንድነው? ሰዎች የሚያደርጉትን ያደርግ ነበር። ኢየሱስ ታምራት ሠራ። ዓይነ ስውራንን፣ ሽባዎችን፣ ደንቆሮዎችን ፈወሰ። ሙታንንም አስነሳ። በቁስ ላይ ስልጣን ነበረው። ከአየር ምግብ በመፍጠር በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን መገበ፤ በውሃ ላይ ተራመደ፤ለወዳጆቹ የተነሳውን ማዕበል ፀጥ አደረገ። ሰዎች በሁሉ ቦታ ይከተሉት ነበር። ምክንያቱም ተአምራት እየሠራ ፍላጎታቸውን ያረካ ስለነበር ነው። ኢየሱስም. “የምለውን ባታምኑ ስለ ሥራው እመኑኝ።”16 አላቸው።

እግዚአብሔር ጨዋና ፍቅር መሆኑን እኛ ደግሞ ምንም እንኳን ራስ ወዳድና ጉድለቶች ቢኖሩብንም ሊያቀርበንና ግንኙነት ከእርሱ ጋር እንዲኖረን መፈለጉን ኢየሱስ አሳየን። ምንም እንኳን ሃጢአተኞችና ቅጣት የሚገባን ብንሆንም ከፍቅሩ የተነሳ እግዚአብሔር የተለየ ዕቅድ ለእኛ እንዳለው ኢየሱስ ገለጸ። እግዚአብሔር ሥጋ ለብሶ በእኛ ፋንታ ኃጢአታችንን ተቀበለ። ምናልባት ፌዝ ይመስላል። ምናልባት ብዙ አባቶች ልጃቸውን ለማዳን በካንሰር በተመታ ልጃቸው ቦታ ለመሆን ፈቃደኛ ይሆኑ ይሆናል። እግዚአብሔርን የምንወደው ግን አስቀድሞ ስለወደደን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በደንብ ይነግረናል።

ምህረት እንድናገኝ ኢየሱስ በእኛ ፋንታ ሞተ። ከዓለም ሃይማኖቶች እግዚአብሔር እጁን በክርስቶስ አማካይነት ብቻ ዘርግቶ ከሰው ልጅ ጋር ግንኙነት ሲፈጥር እናያለን። በኢየሱስ ውስጥ መለኮታዊ የፍቅር ልብ ፍላጎታችንን እያሟላ ወደ ራሱ ሲያቀርበን እናያለን። በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ዛሬ አዲስ ሕይወት አለን። እግዚአብሔር “በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ”17 አለ። ይህ በሥራ ላይ ያለ እግዚአብሔር ነው።

ለማወቅ ከፈለግህ ኢየሱስን ፈትሸው። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”18

እግዚአብሔር እንድናምንበት አያስገድደንም። ከፈለግን ግን ለመኖሩ በቂ ማስረጃ ሰጥቶናል። በምድርና በፀሐይ መካከል ያለው ርቀት፣ የውሃ የኬሚካል ባሕርያት፤ የሰው አንጎል ዲ.ኤን.ኤ(DNA)፤ በእግዚአብሔር የሚያምን የሰው ብዛት፤ ስለ እግዚአብሔር መኖር እንድንወስን ለልባችንና ለአእምሮአችን ፋታ የማይሰጥና የሚቆረጣጥም ሁኔታ አለ። የሚያስደንቀው በክርስቶስ ኢየሱስ እንድናውቀው የእግዚአብሔር ፈቃደኝነት ነው።

ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘትና ከእርሱ ጋር የግል ህብረት መጀመር ብትፈልግ አሁን ትችላለህ።

ይህ ያንተ ፈቃደኛነት ነው። በግዳጅ አይደለም። ከእግዚአብሔር ይቅርታ ለማግኘትና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ብትፈልግ ምሕረት እንዲያደርግልህና ኢየሱስ ወደ ሕይወትህ እንዲገባ በመጋበዝ። በቀጥታ እዚሁ ለማድረግ ትችላለህ “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ።”19 ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆንህና በቃላት ማስቀመጡ ካስቸገረህ እንዲህ ልትል ትችላለህ።

“ኢየሱስ አመሰግንሃለሁ ለሃጢአቴ በመሞትህ ለሕይወቴ የኃጢያት ይቅርታን እፈልጋለሁ አሁኑኑ ይቅርታ እንድታደርግልኝ ወደ ሕይወቴ እንድትገባ እጠይቅሃለሁ። በእርግጠኛነት ላውቅህ እፈልጋለሁ አሁን ወደ ሕይወቴ ግባ ስለ ኃጢአቴ በመስቀል ላይ ስለሞትክልኝ አመሰግንሃለሁ። አሁን ልቤን ከፍቼ አዳኜና ጌታዬ አድርጌ እቀበልሃለሁ። ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ስላልከኝና የዘላለም ሕይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። በሕይወቴ ዙፋን ላይ ሆነህ ግዛኝ። አንተ የምትፈልገው አይነት ሰው አድርገኝ። ልትገናኘኝ ስለፈለግህ አመሰግንሃለሁ። አሜን።”

ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖርህ ግንኙነት ዘላቂነት እንዲኖረው ኢየሱስ ይፈልጋል። አማኞችን በተመለከተ “እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለም አይጠፉም፤ ከእጄ ማንም አይነጥቃቸውም።”20 ይላል።

እግዚአብሔር በእርግጥ አለ። እነዚህን ማስረጃዎች በማገናዘብ አንድ ሰው ፍቅር ስለ ሆነው እግዚአብሔር ማወቅ ይችላል። የቅርብና የግል ግንኙነት ከእርሱ ጋር ሊፈጥር ይችላል። ስለ ኢየሱስ መለኮታዊነት፣ ስለ እግዚአብሔር መኖር ወይም ተመሳሳይ ጥያቄዎች ካሉህ በሚቀጥለው አድራሻ ልትገናኘን ትችላለህ።

 ኢየሱስን ወደ ሕይወቴ እንዲገባ ጋበዝኩት (ተጨማሪ ሀሳቦች)
 ኢየሱስን ወደ ሕይወቴ ልጋብዘው እሻለሁ ፡ ስለዚህ ጉዳይ የበለጠ ብታስረዱኝ
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) ሮሜ 1:19-21 (2) ኤር 29:13-14 (3) R.E.D. Clark, Creation (London: Tyndale Press, 1946), p. 20 (4) The Wonders of God's Creation, Moody Institute of Science (Chicago, IL) (5) Ibid. (6) Ibid. (7) Ibid. (8) Hugh Davson, Physiology of the Eye, 5th ed (New York: McGraw Hill, 1991) (9) Robert Jastrow; "Message from Professor Robert Jastrow"; LeaderU.com; 2002. (10) Steven Weinberg; The First Three Minutes: A Modern View of the Origin of the Universe; (Basic Books,1988); p 5. (11) Dinesh D'Souza, What's So Great about Christianity; (Regnery Publishing, Inc, 2007, chapter 11). (12) Richard Feynman, The Meaning of It All: Thoughts of a Citizen-Scientist (New York: BasicBooks, 1998), 43. (13) Francis S. Collins, director of the Human Genome Project, and author of The Language of God, (Free Press, New York, NY), 2006 (14) ዮሐ 8:12 (15) ዮሐ 14:6 (16) ዮሐ 14:11 (17) ኤር 31:3 (18) ዮሐ 3:16 (10) ራእይ 3:20 (20) ዮሐ10:27-29


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More