ወራጅ ሳህኖች (3:59)
ስለ ኢየሱስ የበለጠ ለማወቅና እርሱ የሚሰጠዉን ለመቀበል። ከጭፍን እምነት ያለፈ ተመልከት
የቪዲዮው ጽሑፍ:
አንቺ። አይኖችሽን ተመልከቺ። እስቲ እያቸው። ህብር ቀለም። ውብ። ሁሉም በጣም ልዩ ናቸው። ሁሉም እኔ የፈጠርኳቸው ናቸው። ሁሉንም እኔ ፈጠርኩ። ፍጥረተ አለምን። አንቺንም። ማንነትሽህን አበጀሁ። እንከን የለሽ አረኩሽ። ውስብስብ። ዕለት በዕልትም ህይወትን ሰጠሁሽ። እወድሻሃለሁ።
ግን አንድ ነገር ሆነ። አታለልሽኝ። አላመንሽኝም። በደልሽኝ። ራስህሽን ከእኔ ለየሽ። ምንም እንኳ በህይወት ያልሽ ቢመስልሽም... ቀስ በቀስ እየሞትሽ ነው። ስለዚህ ሌላ ነግሮችን ፈልግሽ፣ የውስጥ ባዶነትሽን ለመሙላት። ግን አንዳቸውም አልረቡሽም። ይልቁንም ሞትሽን አፈጠኑት። ይልቁንም የበለጠ ለያዩን። ምን እየፈክሽ ነው? እኔ ሞትሽን አልፈልግም። ፈጥሬሻለው። እንዳትጠፊ። ታውቂኝ ዘንድ። እኔ ሞትሽን አልፈልግም። ፈጥሬሻለው። እንዳትጠፊ። ታውቂኝ ዘንድ።
ከእናንተም እንደ አንዱ ሆንኩኝ። ተሰባሪ ፍጥረት። ተፈተንኩኝ። ግን ፈፅሞ ሃጢአት አልሰራሁም። ልታደግሽ መጣሁ። ብዙ ሃጢአት አለብሽ። ደግሞም ቅጣት አላቸው። አንድ ሰው ሊሞት ግድ ነው - አንቺ ወይም እኔ። ስለዚህ በደልህሽን ሁሉ ወሰድኩ። ህይወቴን ለአንቺ ስል ሰጠሁ። በአንቺ ምትክ እኔ ሞትኩኝ። ምክንያቱም እወድሻለሁ።
ከዛም -- ከሞት ተነሳሁ። እኔ መንገድ፣ እውነት እና ህይወት ነኝ። ኢየሱስ እባላለሁ። ልኮንንሽ ሳይሆን ዳግም ህይወትን ልሰጥሽ መጣሁ። በእኔ ላይ ተደገፊ። ይቅር እልሻለው። ህይወትንም እሰጥሻለሁ። እወድሻለሁ። ይህን ሁሉ ያደረኩት ከአንቺ ጋር ህብረት ይኖረኝ ዘንድ ነው። ትከተይኛለሽ?