×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
እግዚአብሔርን ማወቅ

መጽሐፍ ቅዱስን ለምን ልመን?

መጽሐፍ ቅዱስን ማን እንደጻፈ እና እንዴት እንደተፃፈ ተመልከቱ። ‘በቅዱሳን መጻሕፍት’ መካከል ልዩ የሚያደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው።

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በhabeshastudent.com

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ - መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በ40 ጸሐፊዎች በ1500 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው። ከሌሎች ሃይማኖታዊ ጽሑፎች በተለየ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ የእውነተኛ ክስተቶችን፣ ቦታዎችን፣ ሰዎችን እና ንግግሮችን ዘገባ ይዟል። የታሪክ ምሁራን እና የአርኪዎሎጂ ተመራማሪዎች ትክክለኛነቱን ደጋግመው አረጋግጠዋል።

የፀሐፊዎቹን የራሳቸውን የአፃፃፍ ስልቶች እና ስብእናዎች በመጠቀም እግዚአብሔር ማንነቱን እና እrሱን ማወቅ ምን እንደሚመስል ያሳየናል።

በአርባውም የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በተከታታይ የተገለጸ አንድ ማዕከላዊ መልእክት አለ - ሁላችንን የፈጠረው እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ግንኙነትን ይፈልጋል። እርሱን እንድናውቀው እና እንድናምነው ይጠራናል።

መጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን የሚሰጠን ብቻ ሳይሆን ሕይወትን እና እግዚአብሔርን ያስረዳናል። ሊኖረን ለሚችሉት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ባይሰጥም፣ በቂ መልስ ግን አለው። በዓላማ እና በርህራሄ እንዴት እንደምንኖር ያሳየናል። ከሌሎች ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን። ጥንካሬና ምሪትን ለማግኘት እና ለእኛ ባለው ፍቅር እንድንደሰት በእግዚአብሔር ላይ እንድንታመን ያበረታታናል። የዘላለም ሕይወት እንዴት ማግኘት እንደምንችልም መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል።

በርካታ የማስረጃ ምድቦች የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ ትክክለኛነት እንዲሁም መለኮታዊ ጸሐፊነት ይደግፋሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን የሚትችሉባቸው ጥቂት ምክንያቶች እነዚህ ናቸው።

አርኪኦሎጂ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ ትክክለኛነት ያረጋግጣል

የአርኪኦሎጂ ተመራማሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ ነገሥታትን፣ ከተማዎችን እና በዓላትን በተደጋጋሚ አግኝተዋል - አንዳንድ ጊዜ የታሪክ ጸሐፊዎች እንደዚህ ያሉ ሰዎች ወይም ቦታዎች አሉ ብለው ባላሰቡበት ጊዜ ጭምር። ለምሳሌ፣ የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ በቤተሳይዳ መጠመቂያ አጠገብ አንድ ሽባን እንደፈወሰ ይናገራል። ጽሑፉ ወደ መጠመቂያው የሚወስዱትን አምስት የእግረኛ መንገዶች እንኳን ይገልጻል። የአርኪዎሎጂ ተመራማሪዎች ከአምስቱ የእግረኛ መንገዶች ጋር ከምድር በታች አርባ ጫማ እስኪያገኙት ድረስ ምሁሩ መጠመቂያው ነበር ብለው አላሰቡም።1

መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በጣም ብዙ ታሪካዊ ዝርዝሮች አሉት፣ ስለዚህም በውስጡ የተጠቀሱት ሁሉም ነገሮች በአርኪኦሎጂ ገና አልተገኙም። ሆኖም ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ጋር የሚጋጭ አንድም የአርኪኦሎጂ ግኝት አልተገኘም።2

በአንፃሩ የዜና ዘጋቢ ሊ ስትሮቤል ስለ መጽሐፈ ሞርሞን እንዲህ ብሏል - “አርኪኦሎጂ በአሜሪካ ውስጥ ከረጅም ጊዜ በፊት ተከሰቱ ስለተባሉት ክስተቶች በመጽሐፈ ሞርሞን ላይ የተጻፈውን ማረጋገጥ በተደጋጋሚ አልቻለም። የሞርሞኒዝምን ጽሑፎች የሚደግፍ ማስረጃ ስለመኖሩ ለመጠየቅ ለስሚዝሶኒያን ኢንስቲትዩት መጻፌን አስታውሳለሁ። ነገር ግን የአርኪዎሎጂ ተመራማሪዎቻቸው ‘በአዲሲቱ ዓለም አርኪዎሎጂ’ እና በመጽሐፉ ውስጥ ባሉ ነገሮች መካከል ምንም ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌለ’ በማያሻማ ቃላት መልስ ሰጡኝ።” የአርኪዎሎጂ ተመራማሪዎች በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያሉትን ከተማዎችን፣ ሰዎችን፣ ስሞችን ወይም ቦታዎችን በጭራሽ አላገኙም።3

በአዲስ ኪዳን በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በሉቃስ የተጠቀሱት ብዙ ጥንታዊ ስፍራዎች በአርኪኦሎጂ ተገኝተዋል። በአጠቃላይ ሉቃስ ሰላሳ ሁለት አገሮችን፣ ሃምሳ አራት ከተማዎችን እና ዘጠኝ ደሴቶችን ያለ ምንም ስህተት ጽፏል።4

አርኪኦሎጂ እንዲሁ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶችንም አስተባብሏል። ለምሳሌ፣ ዛሬም ድረስ በአንዳንድ ኮሌጆች ውስጥ የሚሰጠው አንድ አመለካከት ሙሴ ኦሪትን (የመጀመሪያዎቹን አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን) መጻፍ እንደማይችል ይናገራል፣ ምክንያቱም ጽሁፍ በዘመኑ አልተፈጠረምና። ከዚያ የአርኪኦሎጂ ተመራማሪዎች ጥቁር ስቲልን አገኙ። "በላዩ ላይ ለየት ያሉ ቅርጽ ጽሁፎችን ነበሩበት ሲሆን የሃሙራቢ ዝርዝር ህጎችን ይዟል። ከሙሴ በኋላ ነበር? በፍፁም! ቅድመ-ሙሴ ነበር፤ ያ ብቻ አይደለም፣ ቅድመ-አብርሃም ነበር (ከክርስቶስ ልደት በፊት 2000 ዓ.ዓ. በፊት)። የሙሴን ጽሑፎች ቢያንስ በሦስት ምዕተ ዓመታት ይቀድማቸዋል።"5

አርኪኦሎጂ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪካዊ ትክክለኛነት በተደጋጋሚ አረጋግጧል።

አንዳንድ ዋና ዋና የአርኪዎሎጂ ግኝቶችን የሚዘረዝር ሰንጠረዥ ለማየት ይህንን ይጫኑ

የዛሬው መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው ከተጻፈው ጋር አንድ ነው።

አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ “በጣም ብዙ ጊዜ” ስለተተረጎመ በመተርጎም ሂደት ውስጥ ተቀይጧል የሚል ሀሳብ አላቸው። ትርጉሞቹ ከሌሎች ትርጉሞች እየተሠሩ ቢሆን ያ እውነት ሊሆን ይችል ነበር። ግን ትርጉሞች በሺዎች በሚቆጠሩ ጥንታዊ ቅጂዎች ላይ በመመርኮዝ በቀጥታ ከመጀመሪያው የግሪክ፣ የዕብራይስጥ እና የአረማይክ ምንጭ ጽሑፎች የተወሰዱ ናቸው።

የዛሬ ብሉይ ኪዳን ትክክለኛነት የተረጋገጠው እ.ኤ.አ. በ1947 በእስራኤል የዌስት ባንክን አካባቢ የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች “የሙት ባሕር ጥቅልሎች” ሲያገኙ ነበር። “የሙት ባሕር ጥቅልሎች” እኛ ካሉን ከማንኛቸውም ጽሑፎች በ1000 ዓመት የሚበልጥ የብሉይ ኪዳን ጥቅል ይዟል። በእጃችን ያሉትን ጽሑፎች ከእነዚህ ከ1000 ዓመታት በፊት ከተጻፉት ጋር ስናወዳድር 99.5% ስምምነት ተገኝቷል። 0.5% ልዩነቶቹ የጽሁፉን ትርጉም የማይለውጡ ጥቃቅን የፊደል ልዩነቶች እና የአረፍተ ነገር አወቃቀር ናቸው።

አዲስ ኪዳንን በተመለከተ የሰው ልጅ እጅግ አስተማማኝ የጥንት ሰነድ ነው።

ሁሉም ጥንታዊ ጽሑፎች የተጻፉት በቆዳ ላይ ነው፣ ይህም ብዙ የመቆየት ሕይወት አይኖራቸውም። ስለዚህ ሰዎች መልእክቱን ጠብቆ ለማሰራጨት እና ለሌሎች ለማድረስ የመጀመሪያ ቅጂዎችን በእጅ ተቀድተዋል።

የፕላቶን “ሪፐብሊክ” ጽሑፍ የሚጠራጠሩ ሰዎች ጥቂት ናቸው። በ380 ዓ.ዓ አካባቢ በፕላቶ የተፃፈ ጥንታዊ ምርጥ ጽሑፍ ነው። እኛ ጋር ያሉት የመጀመሪያዎቹ ቅጂዎች በ900 ዓ.ም የተቀዱ ሲሆን እርሱ ከፃፈው የ1,300 ዓመት የጊዜ መዘግየት አለው። አሁን ሰባት ቅጅዎች ብቻ ናቸው ያሉት።

የቄሳር “ጋሊክ ጦርነቶች” የተጻፉት ከ100-44 ዓ.ዓ. አካባቢ ነው። ዛሬ ያሉን ቅጂዎች እርሱ ከጻፈ ከ1000 ዓመታት በኋላ የተቀዱ ናቸው። አሥር ቅጅዎች አሉን።

ወደ አዲስ ኪዳን ሲመጣ ከ50-100 ዓ.ም. መካከል የተጻፈ ሲሆን ከ5,000 በላይ ቅጂዎች አሉ። ሁሉም የመጀመሪያው ከተፃፈ ከ50-225 ዓመታት ውስጥ የተቀዱ ናቸው። በተጨማሪም፣ ወደ ቅዱሳን ጽሑፎች ሲመጣ፣ ጸሐፍት (መነኮሳት) የመጀመሪያዎቹን ጽሑፎች ሲገለበጡ በጥንቃቄ ነበር። ሥራቸውን በትክክል አንድ መሆኑን ለማረጋገጥ ደግመው ደጋግመው ይፈትሹ ነበር። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በመጀመሪያ የጻፉት ከማንኛውም ጥንታዊ ጽሑፍ በተሻለ መንገድ ተጠብቆ ይገኛል። በቄሳር፣ በፕላቶ፣ በአርስቶትል እና በሆመር ጽሑፎች ላይ እርግጠኛ ከሆንነው በላይ ስለ ኢየሱስ ሕይወት እና ቃላት ስለምናነበው የበለጠ እርግጠኛ መሆን እንችላለን።

አዲስ ኪዳንን ከሌሎች ጥንታዊ ጽሑፎች ጋር ለማነፃፀር ይህንን ይጫኑ

ወንጌላት ስለ ኢየሱስ የሚናገሩትን የምናምንባቸው ተጨማሪ ምክንያቶች

ከአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች መካከል አራቱ እያንዳንዳቸው በኢየሱስ ሕይወት ላይ የራሳቸውን የሕይወት ታሪክ ጽፈዋል። እነዚህ አራቱ ወንጌላት ይባላሉ፣ የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያዎቹ አራት መጻሕፍት። የታሪክ ጸሐፊዎች የሕይወት ታሪክ አስተማማኝ መሆኑን ለመለየት ሲሞክሩ “ስለ ዚህ ሰው ተመሳሳይ ዝርዝሮችን የሚያመለክቱ ሌሎች ምንጮች ምን ያህል ናቸው?” ብለው ይጠይቃሉ።

ይህ እንዲህ ነው የሚሰራው። የፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ. ኬኔዲን የሕይወት ታሪክን እየሰበሰባችሁ እንደሆነ አስቡ። ቤተሰቡን፣ ፕሬዚዳንታዊ ቆይታውን፣ ሰውን ጨረቃ ላይ ሲያወጣ ግቡን እና የኩባን ሚሳይል ቀውስን አያያዙ የሚገልጹ ብዙ የሕይወት ታሪኮችን ያታገኛላችሁ። ኢየሱስን አስመልክቶ ስለ ህይወቱ ተመሳሳይ እውነታዎችን የሚዘግቡ በርካታ የሕይወት ታሪኮችን እናገኛለን? አዎን። ስለ ኢየሱስ እውነታዎች እና በእያንዳንዱ የሕይወት ታሪክ ውስጥ የት እንደሚያገኙ እነሆ።

  ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ
ኢየሱስ ከድንግል ተወለደ 1:18-25 - 1:27፣ 34 -
በቤተልሔም ተወለደ 2:1 - 2:4 -
በናዝሬት ኖረ 2:23 1:9፣ 24 2:51፣ 4:16 1:45፣ 46
ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠመቀ   3:1-15 1:4-9 3:1-22 -
የፈውስ ተአምራትን አደረገ 4:24፣ ወዘተ 1:34፣ ወዘተ 4:40፣ ወዘተ 9:7
በውኃ ላይ ተራመደ 14:25 6:48 - 6:19
አምስት ሺህ ሰዎችን በአምስት
እንጀራና በሁለት ዓሣ መገበ
14:7 6:38 9:13 6:9
ኢየሱስ ተራ ሰዎችን አስተማረ 5:1 4:25፣ 7:28 9:11 18:20
ከማህበረሰቡ ከተገለሉ ሰዎች ጋር ጊዜ አሳለፈ 9:10፣ 21:31 2:15፣ 16 5:29፣ 7:29 8:3
ከሃይማኖት ልሂቃኑ ጋር ተከራከረ 15:7 7:6 12:56 8:1 - 58
የሃይማኖት ልሂቃን እርሱን ለመግደል አሴሩ 12:14 3:6 19:47 11:45 - 57
ኢየሱስን ለሮማውያን አሳልፈው ሰጡት   27:1፣ 2 15:1 23:1 18:28
ኢየሱስ ተገረፈ 27:26 15:15 - 19:1
ተሰቀለ 27:26 - 50 15:22 - 37 23:33 - 46 19:16 - 30
በመቃብር ተቀበረ 27:57 - 61 15:43 - 47 23:50 - 55 19:38 - 42
ኢየሱስ ከሞት ተነስቶ ለተከታዮቹ ታየ 28:1 - 20 16:1 - 20 24:1 - 53 20:1 - 31

ከወንጌላት መካከል ሁለቱ የኢየሱስ የሕይወት ታሪኮች የተጻፉት ኢየሱስን በግል በሚያውቁ እና ከሦስት ዓመት በላይ አብረውት በተጓዙ በማቴዎስ እና በዮሐንስ ነው። ሌሎቹ ሁለቱ መጻሕፍት የተጻፉት የሐዋርያት የቅርብ ባልደረቦች በሆኑት በማርቆስና በሉቃስ ነው። እነዚህ ጸሐፊዎች ለሚያቀርቧቸው እውነታዎች ቀጥተኛ መረጃ ነበራቸው። በሚጽፉበት ጊዜ፣ ኢየሱስ ሲናገር የሰሙ፣ ሰዎችን ሲፈውስ እና ተአምራት ሲያደርግ የተመለከቱ በሕይወት ያሉ ሰዎች ነበሩ።

ስለዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን አራቱን ወንጌላት በቀላሉ የተቀበለችው በኢየሱስ ሕይወት ላይ ቀድሞውኑም ከነበረው የታወቀ እውነት ጋር ስለተስማሙ ነው።

እያንዳንዱ የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ እና የዮሐንስ ወንጌላት እንደ የዜና ዘገባዎች የጊዜውን ክስተቶች በእውነተኛ ክትትል፣ እያንዳንዳቸው ከራሳቸው አመለካከት ጽፈውት ይነበባል። መግለጫዎቹ ለእያንዳንዱ ጸሐፊ ልዩ ቢሆኑም፣ ግን እውነታዎቹ የሚስማሙ ናቸው።

ከወንጌላት በአንዱ ከተጻፈው በጥቂቱ ለማየት ይህንን ይጫኑ

ወንጌላት የተጻፉበት ምክንያት

ከኢየሱስ ሞት እና ትንሣኤ በኋላ በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ስለ ኢየሱስ የተጻፉ የሕይወት ታሪኮች አያስፈልጉም ነበር። በኢየሩሳሌም አካባቢ የሚኖሩ ሁሉ የኢየሱስ ምስክሮች ነበሩ፣ አገልግሎቱንም ጠንቅቀው ያውቃሉ።6

ሆኖም፣ የኢየሱስ ዜና ከኢየሩሳሌም ባሻገር ሲሰራጭ እና የአይን እማኞች በቀላሉ ተደራሽ በማይሆኑበት ጊዜ፣ ​​ስለ ኢየሱስ ሕይወት እና አገልግሎት ለሌሎች ለማስተማር የጽሑፍ ዘገባዎች ያስፈልጉ ነበር።

ስለ ኢየሱስ የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ፣ ይህ ጽሑፍ የሕይወቱን ማጠቃለያ ይሰጥዎታል - ከጭፍን እምነት ያለፈ

የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዴት እንደተወሰኑ

የጥንቷ ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን እንደተፃፈች ወዲያውኑ ተቀበለች። ጸሐፊዎቹ የኢየሱስ ወይም የቅርብ ተከታዮቻቸው ወዳጆች፣ ኢየሱስ የጥንት ቤተክርስቲያንን መሪነት በአደራ የሰጣቸው ሰዎች እንደሆኑ ቀደም ሲል ተጠቅሷል። የወንጌል ጸሐፊዎች ማቴዎስ እና ዮሐንስ ከኢየሱስ የቅርብ ተከታዮች መካከል ነበሩ። ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ የሐዋርያትን ዘገባ በማግኘት የቅርብ ባልደረቦች ነበሩ።

ሌሎቹ የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችም የኢየሱስ ህይወት ቀጥተኛ መረጃ ነበራቸው - ያዕቆብ እና ይሁዳ በመጀመሪያ በእርሱ የማያምኑ የነበሩ የኢየሱስ ግማሽ ወንድሞች ነበሩ። ጴጥሮስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ጳውሎስ ክርስትናን በመቃወም እና የሃይማኖት ገዥ መደብ አባል በመሆን ጀምሮ ግን ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ በማመን የኢየሱስ ቀናተኛ ተከታይ ሆነ።

በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት ዘገባዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የዓይን ምስክሮች በራሳቸው ካዩዋቸው ጋር አንድ ነበሩ።

ሌሎች መጻሕፍት ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ሲጻፉ ለቤተ ክርስቲያን ሐሰተኛነታቸውን ለመለየት አስቸጋሪ አልነበረም። ለምሳሌ፣ የይሁዳ ወንጌል የተፃፈው ይሁዳ ከሞተ ከረጅም ጊዜ በኋላ በ130-170 ዓ.ም በግኖስቲክ ኑፋቄ ነው። የቶማስ ወንጌል በ140 ዓ.ም አካባቢ የተጻፈ የሐዋርያትን ስም በተሳሳተ መንገድ የተሸከመ የሐሰተኛ መጻሕፍት ሌላ ምሳሌ ነው። እነዚህ እና ሌሎች የግኖስቲክ ወንጌሎች ከታወቁት የኢየሱስ እና የብሉይ ኪዳን ትምህርቶች ጋር የሚጋጩ ሲሆኑ ብዙ ጊዜ ብዙ ታሪካዊ እና መልክዓ ምድራዊ ስህተቶች ተገኝተውባቸዋል።7

በ367 ዓ.ም አታናሲዩስ 27ቱን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በይፋ ዘረዘረ (እኛ ዛሬ የምንጠቀመውን ዝርዝር)። ብዙም ሳይቆይ ጀሮም እና አውገስቲን ይህን ተመሳሳይ ዝርዝር አሰራጭተዋል። እነዚህ ዝርዝሮች ግን ለአብዛኞቹ ክርስቲያኖች አስፈላጊ አልነበሩም። በአጠቃላይ መላው ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ተመሳሳይ የመጻሕፍት ዝርዝር ዕውቅና ሰጥተው ይጠቀሙበት ነበር።

ቤተክርስቲያን ከግሪክ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገሮች ባሻገር እያደገች በመምጣቷ እና ቅዱሳት መጻሕፍትን መተርጎም አስፈላጊ በመሆኑ የተከፈሉ ኑፋቄዎች በራሳቸው ተፎካካሪ የቅዱሳት መጻሕፍት ብቅ ማለታቸውን ሲቀጥሉ ትክክለኛ ዝርዝር ማውጣቱ ይበልጥ አስፈላጊ ሆነ።

የታሪክ ምሁራን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ያረጋግጣሉ

በሚገባ የተጠበቁ የመጀመሪያዎቹን ጽሑፎች ቅጅዎች ብቻ ሳይሆን የአይሁድም ሆነ የሮማውያን ታሪክ ጸሐፊዎች ምስክርነትም አለን።

የናዝሬቱ ኢየሱስ ብዙ ተአምራትን እንዳደረገ፣ በሮማውያን እንደተገደለ እና ከሙታን እንደተነሳ ወንጌላት ይዘግባሉ። በርካታ የጥንት ታሪክ ጸሐፊዎች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ እና ስለ ተከታዮቻቸው የሚገልጸውን ዘገባ ይደግፋሉ-

የመጀመሪያው መቶ ዘመን የሮማ ታሪክ ጸሐፊ ቆርኔሌዎስ ታኪተስ (ከ55-120 ዓ.ም) ከጥንት እጅግ ትክክለኛ ታሪክ ጸሐፊዎች መካከል አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል።8 ከጽሁፎቹ ውስጥ በአንዱ … የሮም ንጉስ ኔሮ ክርስቲያኖች በተባሉት ላይ ታላቅ ስቃይ እንዳደረሰ... ክርስቶስ በጥብርያዎስ የግዛት ዘመን በአንዱ አውራጃችን በጴንጤናዊው ጲላጦስ እጅ ከፍተኛ ቅጣት እንደደረሰበት ይዘግባል .... "9

ፍላቪየስ ጆሴፈስ (ከ38-100 ዓ.ም) የተባለው የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ በአይሁድ ጥንታዊ ቅርሶች መጽሐፉ ውስጥ ስለ ኢየሱስ ጽፏል። ከጆሴፈስ “ኢየሱስ ጠቢብ የነበረ፣ አስገራሚ ነገሮችን ያከናወነ፣ ብዙዎችን ያስተማረ፣ ከአይሁዶችና ከግሪክ ሰዎች መካከል ተከታዮችን ያሸነፈ፣ መሲሕ ነው ተብሎ የታመነ፣ በአይሁድ መሪዎች የተከሰሰ፣ በጲላጦስ የተሰቀለ፣ እና ከሞት እንደተነሳ የታመነ ሰው እንደነበረ እንረዳለን።"10

ሱቶኒየስ፣ ታናሹ ፕሊኒ እና ታሉስ እንዲሁ ከአዲስ ኪዳን ዘገባዎች ጋር የሚስማማ ስለ ክርስቲያናዊ አምልኮ እና ስደት ጽፈዋል።

በእርግጠኝነት ለኢየሱስ የማያደላው የአይሁድ ታልሙድ እንኳ በሕይወቱ ውስጥ ስለተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ይስማማል። ከታልሙድ “ኢየሱስ ከትዳር ውጭ እንደተፀነሰ፣ ደቀ መዛሙርት እንደሰበሰበ፣ ስለራሱ የስህተት ቃላትን እንደተናገረ እና ተዓምራትን እንዳደረገ፣ ነገር ግን እነዚህ ተአምራት የአስማት እና የእግዚአብሔር አይደሉም እንደተባሉ እንማራለን።”11

ጥንታዊ የታሪክ ጸሐፊዎች በፖለቲካ እና በወታደራዊ መሪዎች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን፣ ከሩቅ የሮማ ግዛት አውራጃዎች በሚገኙ ረቢዎች ላይ አለማተኮራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ በጣም አስደናቂ ነው። ሆኖም የጥንት ታሪክ ጸሐፊዎች (አይሁዶች፣ ግሪኮች እና ሮማውያን) ምንም እንኳን ራሳቸው አማኞች ባይሆኑም በአዲስ ኪዳን ውስጥ የቀረቡትን ዋና ዋና ክስተቶች ያረጋግጣሉ።

ኢየሱስ በእውነት በወንጌላት ውስጥ ያለውን ነገር መናገሩ እና ማድረጉ ወሳኝ ነው?

አዎን። እምነት በእውነት ዋጋ እንዲኖረው በእውነታዎች ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። ምክንያቱም ይህ ነው። ወደ ለንደን በረራ እየወሰዳችሁ ከሆነ አውሮፕላኑ ነዳጅ የተሞላ እና ሜካኒካል አስተማማኝነት ያለው፣ አብራሪው የሰለጠነ እና በአውሮፕላኑ ውስጥ ምንም አሸባሪዎች እንደሌሉ እምነት ይኖራችኋል። እምነታችሁ ወደ አውሮፕላኑ አስገብቷችኋል። ነገር ግን ወደ ለንደን የሚያደርሳችሁ እምነታችሁ ሳይሆን የአውሮፕላኑ፣ የአውሮፕላን አብራሪው፣ ወዘተ አስተማማኝነት ነው። ባለፉት በረራዎቻችሁ መልካም ተሞክሮ ላይ መተማመን ትችላላችሁ። ያንን አውሮፕላን ወደ ለንደን ለማድረስ ግን አዎንታዊ ተሞክሯችሁ በቂ አይሆንም። ዋናው ነገር የእምነታችሁ ማረፊያ ነው - እምነት የሚጣልበት ነው?

አዲስ ኪዳን ትክክለኛና አስተማማኝ የኢየሱስ መልእክት ነው? አዎን። አዲስ ኪዳንን ማመን እንችላለን፣ ምክንያቱም እጅግ በጣም ተጨባጭ የሆነ ድጋፍ አለው። ይህ ጽሁፍ የሚከተሉትን ነጥቦች ነክቷል - የታሪክ ምሁራን ስምምነት፣ የአርኪዎሎጂ ተመራማሪዎች ስምምነት፣ አራቱ የወንጌል ታሪኮች የተስማሙ ናቸው፣ የዋናው ጽሁፍ ቅጅዎችን ማቆየቱ አስደናቂ ነው፣ በትርጉሞቹ የላቀ ትክክለኛነት አለ። ይህ ሁሉ ዛሬ የምናነበው ጽሑፍ የመጀመሪያዎቹ ፀሐፊዎች በትክክሉኛው ህይወት በትክክሉኛው ቦታ የፃፉትን እና የተለማመዱትን እንደሆነ ለማመን ጠንካራ መሠረት ይሰጠናል።

ከጸሐፊዎቹ አንዱ የሆነው ዮሐንስ በጥሩ ሁኔታ ጠቅለል አድርጎ ያቀርበዋል፣ "ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች አያሌ ታምራዊ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል።"12

በኢሜል ወደ እርስዎ ለሚመጣው የዮሐንስ ወንጌል ነፃ ጥናት እንድትመዘገቡ እንጋብዞታለን። ይህንን ይጫኑ

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) Strobel, Lee. The Case for Christ (Zondervan Publishing House, 1998), p. 132. (2) The renowned Jewish archaeologist, Nelson Glueck, wrote: "It may be stated categorically that no archaeological discovery has ever controverted a biblical reference." Nelson Glueck, Rivers in the Desert: History of Negev. Jewish Publication Society of America, Philadelphia, 1969, P. 176. (3) Strobel, p. 143-144. (4) Geisler, Norman L. Baker Encyclopedia of Christian Apologetics (Grand Rapids: Baker, 1998). (5) McDowell, Josh. Evidence That Demands a Verdict (1972), p. 19. (6) ሐ.ሥራ 2:22, 3:13, 4:13, 5:30, 5:42, 6:14, ወዘተ. (7) Bruce, F.F. The Books and the Parchments: How We Got Our English Bible (Fleming H. Revell Co., 1950), p. 113. (8) McDowell, Josh. The New Evidence that Demands a Verdict (Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 55. (9) Tacitus, A. 15.44. (10) Wilkins, Michael J. & Moreland, J.P. Jesus Under Fire (Zondervan Publishing House, 1995), p. 40. (11) Ibid. (12) ዮሐንስ 20:30-31


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More